ሁለት ኢትዮጵውያን አትሌቶች ከአበረታች እጽ ጋር በተያያዘ ከሃገራዊና አለማቀፋዊ ውድድሮች ታገዱ

Filed under: News Feature,ስፖርት |

አትሌት ብርቱኳን አደባ እና አትሌት እዮብ አለሙ ለ4 ዓመታት ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ ውድድሮች ላይ እንዳይሳተፉ ታገዱ:: 

ዜናውን በቪዲዮ ለማየት እዚህ ይጫኑ

የወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ሁለቱ አትሌቶች የተከለከለ መድኃኒት በመጠቀም የህግ ጥሰት በመፈፀማቸው ነው የኢትዮጵያ ብሄራዊ የፀረ አበረታች ቅመሞች ጽህፈት ቤት ውሳኔ የተቀጡት::

አትሌት ብርቱኳን አደባ በሪሁን በሻንጋይ ዓለም አቀፍ ማራቶን ውድድር ላይ “ኤግዞጂንየስ ስቴሮይ” የተባለ የተከለከለ መድሃኒት መጠቀሟ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ህዳር 13 2016 በተደረገባት ምርመራ ሲረጋገጥ በዚህ የተነሳ  ለ4 ዓመታት ማንኛውም ውድድር ላይ እንዳትሳተፍ ታግዳለች:: 

አትሌት እዮብ አለሙ ወልደጊዮርጊስም በቻይና ሎንግኮው በተካሄደ የማራቶን ውድድር ላይ ኢ.ፒ.ኦ የተባለ የተከለከለ አበረታች መድኃኒት መጠቀሙ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ጥቅምት 29 2017 በተካሄ ምርመራ የታወቀበት ሲሆን  ለተከታታይ 4 ዓመታት ከማንኛውም አትሌቲክስ ውድድር ላይ እንዳይሳተፍ እድግ ተወስኖበታል። ሁለቱም አትሌቶች ለቀጣይ 4 ዓመታት በሀገር አቀፍ፣ ዓለም አቀፍና በሌሎችም ማናቸውም ስፖርታዊ ውድድሮች ላይ አይሳተፉም::

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የተከለከለ መድኃኒት በመጠቀም የህግ ጥሰት የፈፀመውን አትሌት አሊ አብዶሽን ለ4 ዓመታት ሀገራዊም ይሁን ዓለማቀፋዊ ውድድሮ ማገዷ ይታወሳል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.