//

ድምጻዊ መሐሪ ደገፋው ልደቱን በማስመልከት ከቤኒሻንጉል ጉምዝ የተፈናቀሉትን ወገኖች ‘ሰርፕራይዝ’ አደረጋቸው

1 min read

(ዘ-ሐበሻ) ሁለት የሙዚቃ አልበሞችን በግሉ አንድ አልበም ደግሞ በጋራ ሰርቷል:: ከ7 የማያንሱ ነጠላ ዜማዎችንም አበርክቷል:: በሃገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተጨንቀው ስለሕዝብ ከሚያቀነቅኑት ቴዲ አፍሮ ፣ ብርሃኑ ተዘራ ፣ ፋሲል ደሞዝ ፣ ሃጫሉ ሁንዴሳ ፣ መስፍን በቀለ ፣ ጃምቦ ጆቴ ጋር ይመደባል:: ወልቃይት አማራ መሆኑን ለመታገል አንድ ዜማ ሰርቷል:: ለፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብም በራሱ አነሳሽነት ዘፈን ለቆላቸዋል:: ሰሞኑን ዶ/ር ዓብይ አህመድ በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች ስለተፈናቀሉት ወገኖች “በውጭም ሃገር በሃገር ውስጥም ወገኖቻችን ተሰቃይተው እንዴት ይችሉታል?” በማለት ከመናገራቸው በፊት “አመመኝ” የተሰኘ የወገኖቹን ስቃይ ያስታወሰበትና ይህ ስቃይ እንዲያበቃ የለመነበትን ነጠላ ዜማ ለቋል:: ድምጻዊ መሐሪ ደገፋው::

ይህን ዜና በቪዲዮ ለማየት እዚህ ይጫኑ

ከወራት በፊት የኦሮሞ ወገኖቻችን ከሶማሌ ክልል ሲፈናቀሉ እነ ሃጫሉ ሁንዴሳ የሙዚቃ ኮንሰርቶችን በማዘጋጀት ለወገኖቻችን በፍጥነት ደርሰዋል:: ከቤንሻንጉል እና ከኤሊባቡር ተፈናቅለው በባህርዳር አንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ ለተጠለሉ ወገኖች አንድም ለህዝብ ተቆርቋሪ ነኝ የሚል አርቲስት አልደረሰላቸውም ፣ የት ወደቃችሁ አላላቸውም እየተባለ በሚነገርበት ወቅት መሐሪ ደገፋው ድንገት ተከስቷል::

ድምጻዊው በዛሬው ዕለት የልደት በዓሉን እያከበረ ይገኛል:: ልደቱን በማስመልከትም ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ተፈናቅለው ባህርዳር ውስጥ በሚገኝ አንድ ቤተክርስቲያን ውስጥ ተጠልለው ለሚገኙት ወገኖች 30 ሺህ ብር ለግሷል::

“ልደቴን ድል ባለ ድግስ የማክበር ልምዱ የለኝም:: ከዚህ ቀደም ልደቴን ሳከብር የማደርገው ለራሴ ስጦታ ገዝቼ ሻማ እያበራው እመቤቴ ማርያምን እየለመንኩ ነበር:: የዘንድሮውን ልዩ የሚያደርገው ግን ከቤኒሻንጉል ጉምዝ የተፈናቀሉ ወገኖቼን እያሰብኩ በመሆኑ ተደስቻለሁ” ብሎናል በስልክ ባነጋገርነው ወቅት::

ጎንደር ደብረታቦር ከተማ ማህደረ ማርያም ተወልዶ ያደገው ድምጻዊው መሐሪ ደገፋው ሙዚቃን ከታላላቅ ወንድሞቹ ተምሮ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት አራት ኪሎ ምኒልክ ትምህርት ቤት ውስጥ ነበር ክህሎቱን አዳብሮ በባንድ መዝፈን የጀመረው::

ወደ አሜሪካ ከመጣ በኋላም በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ባሉ ክለቦች ለጥቂት ጊዜያት ከሰራ በኋላ በተለያዩ ስቴቶች እንዲሁም በ አውሮፓና በአውስትራሊያ እየተዘዋወረ ሥራዎቹን በማቅረብ እንዲሁም ተጨማሪ ስራ እየሰራ ሕይወቱን ይመራል::

“ኢትዮጵያውያን ከየትም ቦታ መፈናቀል የለባቸውም:: ባሉበት ቦታ ሁሉ ሁሉን እንደሃገራቸው ቆጥረው ተቆጥረውም መኖር አለባቸው:: ከሶማሊ ክልል ለተፈናቀሉት ኦሮሞዎችም ሆነ አሁን በቤኒሻንጉልና ከሌሎቹም ቦታዎች የሚፈናቀሉ ወገኖቻችን ጉዳይ ሁሌም ያመኛል::” የሚለው ድምጻዊው መሐሪ ደገፋው በልደቱ ቀን ማድረግ የሚችለውን የአቅሙን ከቤኒሻንጉል ለተፈናቀሉ ወገኖች ማድረጉ እንዳስደሰተውና ወደፊትም በሚችለው መንገድ እንደሚደግፍ ቃል ገብቷል::

በዚህ አጋጣሚም ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የተፈናቀሉትን ወገኖች እስካሁን ለረዱ ኢትዮጵያውያን ምስጋናውን ያቀረበው መሐሪ በተለይ የባህርዳር ሕዝብ፣ የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች፣ ግሎባል አልያንስ፣ የወልቃይት አማራ ኮሚቴ አባላትን አመስግኑልኝ ብሎናል::

2 Comments

  1. God bless you Mehari. You and a few other musicians are more than just a musician. You, Tedy, Gigi, Fasil, and a few others have expressed your love to our beloved country through your talent. Thank you for standing on the side of history.

  2. Amhara yetefenakelew keageru keGojjam enji Kebenishangul Gumuz yemibal lib weled ager aydelem. Benishangul gumuz bihere enji ager ayidelem. Yih begilts metawek alebet. Qenu sideres ayidelem benishangul Gumuz, Sunan yesherefat meretim beitif timtalech!!!

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.