የተለቀቀው የአትሌት ጌጤ ዋሚ ቪዲዮ ብዙዎችን አሳዘነ

Filed under: News Feature,ስፖርት,የዕለቱ ዜናዎች |

(ዘ-ሐበሻ) ጀግናዋ አልትሌት ጌጤ ዋሚ ለ18 ዓመታት ያህል በጓደኞቿ መተት እንደተደረገባት የሚያሳይና ቪዲዮ በማህበራዊ ድረገጾች ከተለቀቀ በኋላ ብዙዎችን አሳዘነ።

አትሌቷ ለ18 ዓመታት የተደረገባት መተት ጤናዋን እና የምትወደው ትዳሯን እንድታጣ እንዳደረጋት፤ ታላላቅ ዓለም አቀፋዊ ውድድሮች ላይ እግሮቿን እንደሚይዛት፤ ደብረብርሃን ላይ የሰራችው ሆቴል እንዲያስጠላትና የራሷ እንዳይመስላት፤ የ11 ዓመት ልጇ የ እርሳ እንዳትመስላት እንዳደረጋት ለመምህር ግርማ ስትናገር ቪዲዮው ያሳያል።

ይህን ዜና በቪድዮ ለማየት እዚህ ይጫኑ

ጌጤ * በ 2000 Sydney Olympic በ 10,000 ሜ ብር፤ በ2000 Sydney Olympic በ 5,000ሜ ነሃስ፤ በ 1996 Atlanta Olympic በ 10,000 ሜ ነሃስ ለሀገሯ እና የማጣች ብርቅርዬ አትሌታችን ናት በተጨማሪም በ 1999 World championship Seville ላይ የተካሄደውን ወርቅ በማምጣት በ2001 Edmonton ላይ ነሃስ ለሃገሯ አስመስግባለች::

ያስገኘች ጀግና አትሌት ስትሆን አሁን ያለችበት ሁኔታ በቪዲዮ ከተለቀቀ በኋላ ብዙዎችን አሳዝኗል።

7 Responses to የተለቀቀው የአትሌት ጌጤ ዋሚ ቪዲዮ ብዙዎችን አሳዘነ

 1. የጀግናዋ አትሌት ጌጤ ዋሚ መታመም ልቤን ነካኝ። ያችን የመሰለች የሀገር ኩራት እንዲህ አእምሮዋን ስታ ስትሰቃይ ማየት ለማንም ኢትዮጵያዊ ሀገር ወዳድ የሚያሳዝን ከመሆኑም በላይ ገበናዋን አደባባይ አውጥቶ ለህዝብ እንዲታይ ማድረግ ደግሞ እጅግ በጣም ያማል።ለመሆኑ አንድ ሰው ችግሩንና በሽታውን ለእምነት አባቱ ቀርቦ ቢናገርና ጸሎት ቢደረግለት፤ እውነት እንደተባለውም ፈውስ ቢያገኝ በማይክ እያስለፈለፉና በቪዲዮ እየቀረጹ በፌስቡክና በዩቲዩብ ሚስጥሩን ገሀድ ማውጣት ተገቢ ነውን? ዛሬ በየቤተ እምነቱ የሚገኙ ብልጣ ብልጦች በተለያየ ምክንያት በወገኖቻችን ላይ የሚከሰትን የአእምሮ ቀውስና ህመም መተት፣ አጋንንትና ቡዳ ከሚባል ኋላ ቀር እምነት ጋር እያገናኙ ለራሳቸው ዝናና ሀብት ማፍሪያ በማድረግ በሰው ህይወት ላይ ሲጫወቱ እንዴት ሃይ የሚል ይጠፋል? እንዲያው ይሄ ህዝብ የስንቱ መቀለጃ ይሁን? እስቲ እውነተኛ የሀይማኖት አባቶችና የስነ አእምሮ ሀኪሞች በዚህ ላይ ሃሳብ ስጡበት።

  Gedif
  May 24, 2018 at 11:11 pm
  Reply

 2. It is true all Ethiopian runners they follow evil sprite to win not only Gete other runners also their own friend did evil sprite that takes the talent(power) from one to anther.If you take the legend runner Haile there is a place he is going for this evil sprite every body knows, he also restricted to go to rural church b/c he buried skin of Haynes in his foot.

  Truth
  May 25, 2018 at 8:10 am
  Reply

 3. Betam Betam yasazinal.Egziabiher mihret yawridilat.

  Getch
  May 25, 2018 at 10:10 am
  Reply

 4. Min Yedereg Sew Tenegerew ..Lesew Atsged Tebale..sew gin ke duryewoch ser aytefam…minim madreg aychalm.

  Dawit
  May 25, 2018 at 1:57 pm
  Reply

 5. ሰው ተዋርዶ ሰይጣን ክብር ያገኘበት ዘመን
  Daniel Kibret, Friday May 25, 2018

  የቤተ ክርስቲያናችን የገድላትና የተአምራት መጻሕፍት ሲጻፉ፣ የሰዎቹን ክብር በሚጠብቅ መንገድ ካልሆነ በቀር ችግር ደርሶባቸው ተአምር የተደረገላቸውን ሰዎች የተጸውዖ ስም አይገለጡም፣ ወይም የክርስትና ስማቸው ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ሰዎቹን በስማቸው መጥራት ቢያስፈልግ እንኳን ለዝርዝር ማንነታቸው በማይመች ስም ይገለጣሉ፡፡ ይህ ሁሉ የሚደረግበት ዋናው ምክንያት የሰውን ልጅ ሰብአዊ ክብር(Human dignity) ለመጠበቅ ነው፡፡ እነርሱ ቢያልፉም እንኳን ልጅና ልጅ ልጅ ይኖራልና፡፡
  እኅታችን ጌጤ ዋሚ ‹ሩጫን በሚከለክሉ በአጋንንት› ተያዘች ተብሎ የተለቀቀባትን ቪዲዮ ስመለከት በእምነት ስም የሚነግዱ ሰዎች የደረሱበትን ሞራላዊ ኪሣራ አየሁት፡፡ ከመጀመሪያው ሰይጣንን እየቀዱ ለገበያ ማዋል በየትኛውም የቅዱሳን ሕይወት ውስጥ የማናየው ነው፡፡ መቼም ሰይጣን እንደዚህ ዘመን በክብር መድረክ ያገኘበት ጊዜ የለም፡፡ ከዚህም አልፎ ልጅ፣ ቤተሰብ፣ ወዳጅ፣ ዘመድ፣ ዓለም አቀፋዊ ተክለ ሰብእና ያላትን አትሌት በዚያ ዓይነት ክብርን በሚነካ ሁኔታ እያሰቃዩ በቪዲዮ ማሳየት ፈጽሞ የእግዚአብሔርን ክብር መግለጥ ሊሆን አይችልም፡፡ ሰውነትን ማዋረድ እግዚአብሔርን ማዋረድ ነውና፡፡ አስፈላጊ ነው ካለች እርሷ ራሷ ትንገረን እንጂ ይህንን የመሰለ ቪዲዮ እንኳን ሌላው እርሷም ልታሳየን የተገባ አይደለም፡፡
  ሃይማኖት ታረደ ደሙን ውሻ ላሰው
  ከንግዲህ ልብ ልብ አልተገናኘም ሰው
  እንደተባለው ሆኖብን ነው እንጂ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የቅድስና ሕይወትስ በሰውነት ክብር ላይ የሚቀልድ አልነበረም፡፡ የአንድን ሰው ‹ፈዋሽነት› ለማሳየት የሌላን ሰው ዝና፣ ክብርና ሰብአዊ መብት መከስከስ በምንም መልኩ ጸጋ እግዚአብሔርን አያመለክትም፡፡ የወንድማቸውን ክብር ለመጠበቅ ያልፈጸሙትን ፈጸምን ብለው መከራ የተቀበሉት የነ አባ መቃርስ፣ የነ እንባ መሪና፣ የነ ሙሴ ጸሊም፣ ቤተ ክርስቲያን፤ ለራሳቸው ክብር ሲሉ የወገኖቻቸውን ክብር በሚደፈጥጡ ‹አጥማቂዎች› ሲቀለድባት ማየት ያማል፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስም የጳጳሳትን ዝውውር ከሚመለከት ይልቅ እንዲህ ያሉ ነገሮች ሕግና ሥርዓት እንዲኖራቸው ቢያደርግ መልካም ነበር፡፡ ማን ያጥምቅ? የተጠማቂዎች ሰብአዊ ክብር፣ የተጠማቂዎችን መረጃ የመጠቀም መብት፣ በአደባባይ ራቁትን መቆምና ራቁትን ፎቶ የመነሣት ጉዳይ፣ የምስክርነት አሰጣጥ ሥነ ምግባር፣ የሴቶችና የሕጻናት መብቶች፣ የአካል ጉዳተኞችና የአእምሮ ሕሙማን መብቶች፣ ወዘተ ሕግና ደንብ የሚያስፈልጋቸው ናቸው፡፡ ያ ካልሆነ ግን ገና ከዚህ የከፋም እናያለን፡፡

  Gedif
  May 25, 2018 at 5:42 pm
  Reply

 6. ይህ ምስክርነት ነው ድንቅ ስራውን መስክሩ አውሩ በአደባባይ ደስ ብሎናል በመምህር ግርማ ላይ የእግዚአብሔር ማዳንን ስላየን አሜን አሜን ይውጣ ይነገር ማዳኑ እልልልልልልልልል!!!

  ራሄል
  May 28, 2018 at 5:45 am
  Reply

 7. betam yasaznal

  hassen ali
  May 29, 2018 at 4:07 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.