//

ማንዲንጎ አፈወርቅና እና ፍቅርአዲስ ነቅአጥበብን እናመሰግናለን!!

1 min read

(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ አቆጣጠር ጥር 1994 ዓ.ም ኢኦትዮጵያ ውስጥ በማሳትማት መዲና ጋዜጣ ላይ ቤተሰቦቹ ተገኔ እያሉ የሚጠሩትን እኛ ደግሞ ማዲንጎ አፈወርቅ በሚለው ዝነኛ ስሙ የምናወቀውን ይህን ድምጻዊ ቃለምልልስ ሳደርግለት ራሱን ያስገረመ ጥያቄ ጠይቄው “ይህን መረጃ ከየት አመጣኸው?” ሲል አስገርሜዋለሁ::

ይህን ዘገባ በቪድዮ ለማየት እዚህ ይጫኑ

ጥያቄው “ጎንደር እያለህ ከፍቅር አዲስ ጋር ምን ትሰሩ ነበር?” ይላል::

ማዲንጎ “በርግጥ ጦሩ ቤት እያለች እሷ 603ኛ ኮር እኔ ደግሞ 4ኛ መካናይዝድ በሚባል ምድብ ቤት ውስጥ ጦሩ ቤት እንሰራ ነበር” አለኝ::
መስማት የምፈልገውን ስላልነገረኝ ቀጠል አደረኩና “ጦሩ ቤት እያላችሁ አንዳንድ ጊዝሬ ፍቅር አዲስ የቀረችበት መድረክ ላይ በመጋረጃ ተሸፍነህ የሷን ዘፈን አስመስለህ ትዘፍን አልነበር?” ስል ጠየኩት::
ማዲንጎ በረዥሙ ሳቀና “ይሄን ነገር ከየት እንዳገኘኸው ገርሞኛል:: በመጋረጃ ተከልዬ ዘፍኜ አላውቅም:: ግን የሷን ድምጽ በጣም እወደው ስለነበር አስመስዬ እዘፍን ነበር” አለኝ::

ይህን ያነሳሁት ዛሬ ሁሉት ምርጥ ድምጻውያን ባህርዳር ላይ ሄደው ከቤኒሻንጉል ጉምዝ እና ከኤሊባቡር ለተፈናቀሉት ወገኖች ያደረጉትን መልካም ተግባር ለሕዝብ ለማሳወቅና በዚያውም ለማመስገን አንድ ዘገባ ስለሰራሁ ነው:: በቅድሚያ ድምጻውያኑን በመጠኑም ቢሆን ላስተዋውቃችሁ::

8 የሙዚቃ አልበሞችን ሠርታለች:: 2007 ዓ.ም ሊሰናበት ጥቂት ቀናት ቀናት ሲቀሩት የመጨረሻውንና “ምስክር” የተሰኘውን የሙዚቃ አልበሟን ለሕዝብ አቅርባለች::

ጎንደር ቆላድባ ነው ተወልዳ ያደገችው:: በልጅነቷ ዋና ትወድ ነበር:: ሮያል ከተባለ መጽሔት ጋር ባደረገችው ቃለምልልስ
” በጣም ፈጣን ነበርኩ:: ልጅነቴን ሳስታውስ ድርማ ወንዝን አልረሳም:: ‘ወንዝ ውስጥ ገብተሽ እንዳትቀሪ እባክሽን አትዋኚ” እየተባልኩ እከለከል ነበር:: ግን መዋኘቴን አልትወም ነበር:: ዋኝቼ ስወጣ ፊቴ አመድ መስሎ እንዳያጋልጠኝ ገበያ ሄጄ የቅቤ ቅጠል እፈልግ ነበር:: እኛ ሃገር ቅቤ የሚጠቀለለው በቅጠል ነው:: ቅቤ የተጠቀለለበትን ቅጠል ለቅመን ስናበቃ ዋኝተን ስንጨርስ በዛ የቅቤ ቅጠል ፊታችንን አውዝተን ነበር ወደ ቤት የምንገባው” ትለናለች ስለ አስተዳደጓ::

“በልጀነቴ በጣም ፈጣንና አስቸጋሪ ልጅ ነበርኩ:: የዛኑ ያህል ደግሞ በጣም ሰራተኛ ልጅ ነበርኩ” የምትለው ፍቅራአዲስ ሙዚቃን የጀመረችው በቆላ ድባ ኪነት ውስጥ ነበር::

“በኪነጥበብ ሙያ ለመታወቅ አጋጣሚ የሚባል ነገር የለም:: ማንም ሰው በአጋጣሚ በኪነጥበብ ሙያ ሊታወቅ አይችልም:: በተለይ በድምጻዊነት ለመታወቅ የተፈጥሮ ስጦታ የግድ አስፈላጊ ነው:: በደርግ ጊዜ ድምጽ ላላቸው ሰዎች ለመታወቅ የነበረው አጋጣሚ ጥሩ ነው:: ቀበሌ ጀምሮ የተለያየ ደረጃ ያላቸው የኪነት ቡድኖች በየክፍለሃገሩ በብዛት ነበሩ:: እነዚህ የኪነት ቡድኖች መኖር ለመነሻነት ጥሩ ነው:: ለምሳሌ እኔን ብትወስዱ ከቀበሌ ኪነት ተነስቼ ወታደር ቤት ሙዚቃ ክፍል ገባሁ:: በ እነዚህ የሙዚቃ ክፍሎች መሥራቴ ልምድ ለማዳበር አግዦኛል” የምትለው ፍቅራዲስ ከደራሲና ከድምጻዊ አበበ ብርሃኔ ጋር በጋብቻ ተሳስራ ትኖራለች::

ፍቅር አዲስ በጎንደር ቆላ ድባ በምትኖርበት ጊዜ ድንች, ቆሎ ትሸጥ እነበርና ይህ ሥራዋ ለሰዎች መልካም እንድታስብ እንዲሁም አሁን ለደረሰብችት ስኬት መሰረት እንደሆናት ትናገራለች:: በ1989 ዓም ሳብ በለው በተሰኘው ሙዚቃዋ የምትታወቀው ፍቅራዲስ በተለይ ለ እናቶች ልዩ ክብር አላት:: ለ እናቷም ዘፈን ዘፍናላት ዘፈኑን ሳታዳምጠው በማለፏ ሁልጊዜ ትጸጸታለች::

ነሐሴ 10 ቀን 1970 ዓመተ ምህረት ጎንደር ደብረታቦር ከተማ ከ እናቱ ሃገርነሽ ዋሴና ከአባቱ አፈወርቅ መንግስቱ ተወለደ:: አባትና እናቱ ተገኔ የሚል ስም ቢያወጡለትም ሕዝብ የሚያውቀው ማዲንጎ በሚለው ስሙ ነው:: “ስያሜ አጣሁላት” በሚለው ዘፈኑ ከሕዝብ ጋር የተዋወቀው ማዲንጎ ባህርዳር ለረዥም ጊዜ ሙዚቃ ሲሰራ ያዩት ሰዎች ናቸው አንተ አዲስ አበባ ብትመጣና ብትሰራ ይሳካልሃል ብለው ያመጡት:: እንዳሉትም አልቀረም ማዲንጎ በላፎንቴን; በኦሪዮን በራዝ ማታዝ ክለቦች ብቃቱን አሳይቶ በሕዝብ ዘንድ ተወደደ::

ማዲንጎ የኤፍሬም ታምሩ ዘፈኖች አድናቂ ሲሆን ባለፈው ዓመት በሚኒሶታ የሙዚቃ ኮንሰርቱን ሊያቀርብ ሲመጣ ለረዥም ሰዓት አውርተን ሰውን ለመርዳትና ከሰው ጋር ለመኖር የሚሞክር መልካም ሰው እንደሆነ ተረድቻለሁ::

ባለፈው ሳምንት መሐሪ ደገፋው ከአሜሪካ 30 ሺ ብር ልኮ ነበር:: ትናንት እሁድ ደግሞ ድምጻዊት አምሳል ምትኬ ዛሬ ደግሞ ድምፃዊ ማዲንጎ አፈወርቅና ድምፃዊ ፍቅርአዲስ ነቃጥበብ; አቤሴሎም ቢሆነኝና ድምፃዊ ሰሎሞን ደምሌ ከቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል የተፈናቀሉትን ወገኖች ለመርዳት ባህርዳር በመገኘት ጎብኝተዋቸው አጋርነታቸውን አሳይተዋል::

ዛሬ ጠዋት በአውሮፕላን ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳር የተጓዙት ፍቅራዲስና ማዲንጎ ለተፈናቃዮቹ የገንዘብ እርዳታ ከማድረጋቸውም በላይ በዘላቂነት እንዲቋቋሙም የሙዚቃ ኮንሰርት ለማዘጋጀት ቃል ገብተዋል::

ሁለቱ ድምጻውያን ተፈናቃዮቹን ከማጽናናታቸውም በላይ ማድረግ የሚችሉትን ሁሉ እንደሚያደርጉ ነግረዋቸዋል:: ተፈናቃይ ወገኖቻችንም በድምጻዊያኑ ድርጊት እጅግ መደሰታቸውን ገልጸዋል::

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.