/

አሰግድ ተስፋዬ እየታሰበ ነው

1 min read

(ዘ-ሐበሻ)  የቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ቡድን ተጫዋች የነበረው አሰግድ ተስፋዬ ልክ የዛሬ ዓመት በዛሬው ዕለት ከልምምድ መልስ በመታጠቢያ ቤት ውስጥ ወድቆ በአርባ ሰባት ዓመቱ በድንገት ሕይወቱ ያለፈው:: ሥርዓተ ቀብሩም በነጋታው በቅድስት ሳህሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል::


አሰግድ ተስፋዬ በ1962 ዓ.ም. በድሬዳዋ ከተማ ነበር የተወለደው። እድገቱም በዚያው በድሬዳዋ ከተማ ልዩ ስሙ ደቻቶ በሚባለው አካባቢ ሲሆን፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን፣ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ወጣት ቡድን፣ ለድሬዳዋ ጨርቃጨርቅ ቡድን፣ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድን፣ ለኢትዮጵያ መድን ቡድን እና ለኢትዮጵያ ቡና ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች ነበር።

ታዳጊ ወጣቶችን በእግር ኳስ በማሠልጠን አገሪቱ ስመ-ጥር ተጫዋቾች እንድታፈራ ሳይታክት በመሥራት ላይ የነበረ ሲሆን፣ በቅርቡም ሲያሠለጥናቸው የነበሩ ታዳጊዎችን ወደ ሰሜን አሜሪካ በመውሰድ የልምድ ልውውጥ አድርጎ እንደነበር የታሪክ መዝገቡ ይመሰክራል። አሰግድ ባለትዳርና የአንድ ልጅ አባት ነበር።

አሰግድ ያረፈበት አንደኛ ዓመት በተለያዩ ዝግጅቶች በዛሬው ዕለት እየታሰበ ይገኛል:: ነፍስ ይማር::

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.