//

ድንገት ያረፉት የደደቢቱ ዋና አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ አስከሬን እየተመረመረ ነው

1 min read

(ዘ-ሐበሻ) የደደቢቱ ዋና አሰልጣኝ ንጉሴ ደስታ ትላንት ምሽት በገጠማቸው ድንገተኛ ህመም ማረፋቸውን ተከትሎ አስከሬናቸው በምኒልክ ሆስፒታል እየተመረመረ መሆኑ ታወቀ::

ምሽት 06:00 ገደማ ከጓደኞቸቻው ጋር በነበሩበት ሰአት በተሰማቸው የህመም ስሜት ወደ ጎፋ ጤና ጣብያ ተጉዘው ህክምና ካደረጉ በኋላ የህመም ስሜቱ ሲባባስ ለድጋሚ ህክምና ሀሌሉያ ሆስፒታል ሲደርሱ ህይወታቸው ማለፉን ከክለቡ የቅርብ ሰዎች ሰምተናል። የአሰልጣኙ አስከሬን ለምርመራ ምኒልክ ሆስፒታል የሚገኝ ሲሆን ምርመራው ከተጠናቀቀ በኋላም ለስርዓተ ቀብር ወደ ማይጨው ይሸኛል ተብሏል።

ሶከር ኢትዮጵያ ኔት እንደዘገቡ የቀድሞ የምድር ጦር ተጫዋች የነበሩት አሰልጣኝ ንጉሴ በመከላከያ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ደደቢት እና ወልዲያ አሰልጣኝነት የሰሩ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በድጋሚ በተመለሱት ደደቢት ከ2010 ጀምሮ በመስራት ላይ ይገኙ ነበር። 

ክለቡ ዛሬ በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከአርባምንጭ ከተማ ጋር የ25ኛ ሳምንት ጨዋታውን የሚያደርግ ቢሆንም በአስደንጋጩ ዜና ምክንያት ወደ ሌላ ጊዜ እንደሚሸጋገር ታውቋል።

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.