ፑሽ አፕ በደንብ ሥራ

Filed under: News Feature,ነፃ አስተያየቶች |


መንግስቱ አሰፋ

በንጉሠ ነገሥቱ የመጨረሻ ዘመነ ንግሥና ኮረኔል አጥናፉ አባተ ወታደሮችን ወደ አዲስ አበባ ጠርተው የደመውዝ ጭማሪ እንዲጠይቁ አስደረጉ። ጥያቄው ተቀባይነት አግኝቶ ወታደሩ ወደ ካምፑ ይመለሳል። የንጉሠ ነገሥቱ ሥልጣናቸው በአመፅ እና ተቃውሞ እየደከመ ባለበት ብዙም ሳይቆይ ኮረኔል አጥናፉ ተመሳሳይ ጥያቄ ያለው ወታደር ወደ ንጉሠ ነገሥቱ አምጥተው እንዲያነጋግሩኣቸው አደረጉ። በዚህ ሰዓት ወታደሩ ፍላጎቱን አገኘ፦ ሥልጣን።

ያ ወታደር ደርግ ነበር። ቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ከሥልጣን አውርደው እሥር ቤት ከተቱኣቸው። እራሳቸው መምግሥት ሆነው እርፍ አሉ።

ኮረኔል አጥናፉም በደርግ ማዕከላዊ ኮሚቴ (ሸንጎ) የተወሰነውን የንጉሠ ነገሥቱ የመጨረሻ እጣ ፈንታ ፈርመው ያጸደቁት ሰው ናቸው። እንዲገደሉ የፈረሙት እሳቸው ናቸው።

የመንግሥቱ ኃይለማሪያም እጅግ የቅርብ ሰው እንደሆኑ የሚታወቁት ኮረኔል አጥናፉ የሴራ ፖለቲካው ግን እሳቸውንም በመንግሥቱ እጅ አስበላቸው።
የሴራ ፖለቲካ ታሪካችንን ሞልቶታል። ከእውቀት እና የሐሳብ ፍጭት ይልቅ ሴራ እና አሻጥር እጅግ የሚገልጸው የሀገራችን ፖለቲካ ዛሬም ክፉ እንድናስብ ያስገድደናል።
የሴራ ፖለቲካን ስለምናውቀው፣ ስለጎዳን እንዳይደገም እንጂ ሐገርን ስለማንወድ አይደለም። ይልቁንም ስለምንወዳት፣ ስለምንሳሳላት እና ክፏን ላለመስማት ነው። ታሪክ እራሱን ደግሞ እንደገና ሌላ ሸፍጥ እንዳይውቅጠን ነው። ዋጋ እንዳንከፍል ነው። እንዳንባላ ነው።
ታዋቂው ጸሐፊ Mark Twain እንዲህ ብሎነበር።
“If there is one thing we learn from history is that we don’t learn from it”.

የዛሬውን ትዕይንት ዝም ብዬ ማለፍ አልቻልኩም። ተሳስታችኋልና Push Up እንሥራ ብሎ ፈሊጥ የለም። ድክሞሃል ማለት ነው። Military is known for its most strict chain of commands. “እግረመንገዳች” ብሎ ነገር የለም። የOperation ሹም ያለው ክፍለጦር “እግረመንገዴን” ብሎ ከነትጥቁ በርህ ላይ ከች አይልም።
ራስህን ፈትሽ። ቀዳዳውን ድፈነው። ያልበሰለውን ባቄላ አታኝከው፤ ትፋው።

የመንግሥትን ጠንቻ ?ለማጠንከር በድንብ Push Up ሥራ። በድርድር ጠረጴዛ በዝረራ እንድታሸንፍ በIdeolgue ራስህን ዙሪያ ገባ ሙላ፣ ቀልጣፋ እና ጥራት ያለው ፖሊሲ ቀርፀህ ሕዝብን ለማገልገል Strategist ይኑርህ። Watchdogህ በተጠንቀቅ ይቁሙልህ።

Militant Democracy ታክቲካሊ ሀገርን ሊታደግ እንደሚችል በሕልም ይገለጥልህ። ይሄ ምኜቴ ነው።

አንተ እኮ ብለሃል ….”ወታደር ስለሆንኩም ነው መሠለኝ”…
በቃ ወታደርም፣ ቢሮክራትም፣ ኢንተልጀንስ ባልሙያም ሁን…አገልግል።

ደግሞ እኮ የረሳሁልህ እንዳይመስልህ..አርቲስቶችን ሰብስበህ እንዳሰለጠንካቸው። “አንድ የሚናገር የአርት ነገር ቢኖርው ነው” ብዬ ነበር። ትክክል ነበርኩ ፥ ተውነኽዋል ዛሬ። ጸዴ ነበር! ??

Push Up ሥራ በድንብ!

ወጣት ስለሆንክ ነው መሠለኝ “አንተ” ብለህ አናግረው እያለኝ ነው።

በል እኔም ቦርጬ በየጧቱ እያመለጠኝ ነው Push Up ልሥራ።
Abbichuu Nagaa Nagaa

2 Responses to ፑሽ አፕ በደንብ ሥራ

 1. So disgraceful not only to those politicians of “heroes of change” much more to the country itself!
  Allowing an anarchist group of military men/women to enter into his office and then telling the people that he punished them by making them do push up whereas it seems that they made him do it is terribly shameful ! What is more disgraceful is the way the palace (the PM) tried to do kind of crisis management (the terrible damage already done) with a very dishonest/cowardly justification.

  T. Goshu
  October 11, 2018 at 5:46 am
  Reply

 2. የማይቀለድበት ቦታ ባይቀልድ ጥሩ ነው፡፡

  Kuni
  October 11, 2018 at 10:03 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.