በራያ አላማጣ የትግራይ ልዩ ኃይል 4 ሰላማዊ ሰዎችን ገደለ

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

(ዘ-ሐበሻ) በግድ ወደ ትግራይ ክልል ተጠቃለናል ማንነታችን ይመለስ በሚል የራያ ሕዝብ እያነሳ ያለው ተቃውሞ ተጋግሎ እየቀጠለበት ባለበት በዚህ ወቅት በዛሬው ዕለት የትግራይ ልዩ ኃይል በራያ አላማጣ አራት በሰላማዊ መንገድ ጥያቄያቸውን እያቀረቡ ያሉ ወጣቶችን በጥይት ገደለ:: የከተማው ወጣቶች ወደ አደባባይ ወጥተው የትግራይ ልዩ ኃይል ከተማቸውን ለቆ እንዲወታ እየጠየቁ ነው::

 የራያን የማንነት ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ከመፍታት ይልቅ ወደ ኃይል ወስዶታል የተባለው የትግራይ ክልል መንግስት በዛሬው ዕለት በአላማጣ መትረየስ ጭምር መጠቀሙን የአካባቢው የዓይን እማኞች ገልጸዋል:: የቆሰሉና የሟቾች ቁጥር በርካታ ቢሆንም ለጊዜው ማወቅ የተቻለው የአራቱን ብቻ ነው ሲሉ እማኞቹ ገልጸዋል::

በአደባባይ ሰላማዊ ተቃውሞ ሲያደርግ የነበረው የአላማጣ ሕዝብ መትረየስ ጭምር የታጠቀውን የትግራይ ልዩ ኃይል በወንጭፍ ለመመከት የአልሞት ባይ ተጋዳይ እንቅስቃሴ ለማድረግ ሞክሯል ሆኖም ግን ጥይትና ወንጭፍ ባለመጣጠናቸው የራያ ሕዝብ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰበት ነው የሚሉት እማኞቹ በዋጃ አቅጣጫ ነገሩን ለማብረድ በሚል መከላከያ ቢገባም መከላከያው በትግራይ ተወላጆች የሚመራ በመሆኑ ከትግራይ ልዩ ሃይል ጋር በመደረብ ሕዝቡን በመደብደብ ላይ መሆኑን እነዚሁ የአካባብቢው ነዋሪዎች ክስ አቅርበዋል::

ግጭቱ የየተፈጠረው በማንነት ጥያቄ ዙሪያ ሊደረግ የታሰበ ህዝባዊ ስብሰባ በክልሉ የጸጥታ ሀይሎች ከተከለከለ በኋላና ለሕወሓት አባላት ግን ስብሰባ በመፈቀዱ የተነሳ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ ነው። በአላማጣ ከተማ የራያ ማንነት ጥያቄ በዛሬው ዕለት እንደገና ሊያገረሽና ወጣቱም አደባባይ እንዲወጣ ያደረገው በዶ/ር አድሃና ኃይሌ ሰብሳቢነት በአላማጣ እየተደረገ ባለው ስብሰባ የተነሳ ነው የሚሉት አስተያየት ምንጮች ስብሰባውም በጭቅጭቅ መበተኑን የራያ ተወካጅ የሆኑ የሕወሓት አባላትም :የራያ ወጣቶች የማንነትና የመብት ጥያቄ የኛም ጥያቄ ነው” በማለታቸው ተነግሯል::

የአላማጣ ወጣቶች ዶ/ር አድሃና ኃይሌ በቅርቡ ራያ ማለት የከብት ስም ነው ማለቱን በዛሬው ተቃውሟቸው ላይ አንስተውት እንደበር የሚጠቅሱት እማኞቹ አላማጣ ከተማ በጭስ, እሳት ታፍናለች; ሕዝብ ራሱን ከትግራይ ልዩ ኃይል ለመቆጣጠር መንገዶችን በ እንጨትና በድንጋይ መዝጋቱን; የጥይት ድምጽ በብዛት እንደሚሰማ ገልጸውልናል::

የራያ ማንነት ጥያቄን ለማዳፈንና በገንዘብ ትግሉን ለማዳከም ሕወሃት በአዲስ አበባ የራሱን “ራያ ትግራዋይ ነው” የሚል ቡድን በአዲስ አበባ እያደራጀ መሆኑን ይህንንም እየሠራ ያለው ጌታቸው ረዳ መሆኑን የራያ ማንነት አስተባባሪዎች ክስ እያቀረቡ ነው::

5 Responses to በራያ አላማጣ የትግራይ ልዩ ኃይል 4 ሰላማዊ ሰዎችን ገደለ

 1. ወያኔ፥በተስፋፊነት፥በያዛቸዉ፥የአማራ፥ግዛቶች፥ንፁሃን፥ያልታጠቁ፥ዜጎችን፥መግደል፥
  መቀጠሉ፥ለዶክተር፥አብይ፥መንግስት፥ያለዉን፥ንቀት፥ያሳያል፥፥ ዶክተር፥አብይ፥ወይ፥
  ንፁሃንን፥የጨፈጨፋ፥የትግሬ፥ወንጀለኞችን፥ለፍርድ፥አቅርብ፥ካልቻልክ፥ደግሞ፥
  40ሚሊዬን፥አማራ፥እንዲታጠቅና፥ወገኖቹን፥ነፃ፥እንዲያወጣ፥ፍቀድለት፥፥

  ወገኖቻችን፥በወልቃይትና፥ራያ፥የሚጨፈጨፉት፥እስከመቼ፥ነዉ? አረመኔዉ፥የትግሬ፥መንግስት፥የራያና፥ወልቃይት፥አማራዎችን፥ማጥቃቱን፥እስከቀጠለ፥ድረስ፥
  ጎንደር፥ወሎ፥ጎጃምና፥ሽዋ፥ወያኔን፥በኢኮኖሚ፥አንቆ፥መቅጣት፥አለበት፥፥ወገኖቻችንን፥እየገደሉ፥
  የአማራን፥ጤፍና፥ማሽላ፥መብላት፥የለባቸዉም፥፥

  Abel
  October 21, 2018 at 9:24 pm
  Reply

 2. We will advise the Tigray region to diseplaced Amharas out of Tigray region by force!!!

  Goasha
  October 21, 2018 at 11:35 pm
  Reply

 3. Goasha,

  That does not worry us at all. There are many Tigrians
  who live in Amara cities than Amaras who live in Tigrai.
  Go ahead and advise your Aremene government and
  let us see who will be the loser.

  There was a time when Amaras and Tigrians used to live
  side by side with peace, love and harmony. That changed
  when the greedy TPLF stole Amara lands.

  Abel
  October 23, 2018 at 12:09 am
  Reply

 4. አህዮች ይቅር በአሁን ስአት በኢኮኖሚ አንቃቹ ልትይዙን ይቅር 10 ተጋዮች እያሉን እንካን ያልተንበረከከ ህዝብ አንድ 50 ስው መዋጋት የሚችል እንደገና ተማርካቹ የምትለቀቁ እንዳይመስላቹ አንዴ እና ለመጨረሻ መሆኑን አውቃቹ ወያነ የሰጣቹ ሰላምና ልማት ብታጣጥሙት ይበጃል ካልሆነ እጣፋንታቹ ጉራ ሳይሆን ሌላ ነው

  ገሬ
  October 25, 2018 at 3:50 am
  Reply

  • ገሬ:አንተ፥ቆርቆሮ፥ራስ፥ወያኔ! ኢትዮጲያዊ፥መንግስት፥እሆናለሁ፥ብለህ፥ስትመጣ፥ህዝብ፥
   እና፥ወታደር፥ደርግን፥ስለጠላ፤ብቻ፥ከፍቶ፥አስገባህ፥እንጅ፥እንዳንተ፥ያለዉ፥ለማኝ፥
   ቤተ፥መንግስት፥አይገባም፥ነበር፥፥አሁንም፥በህዝብ፥አመፅ፥ተገፍትረህ፥ወድቀህ፥
   መቀሌ፥ሄደህ፥ተሸሽግሃል፥፥ምንም፥ለማድረግ፥አቅም፥የለህም፥፥እናንተ፥የምታዉቁት፥ያልታጠቁ
   ፥ህፃናትንና፥ሴቶችን፥መግደል:ብቻ፥ነዉ፥፥ፈሪ፥ሁላ!

   እስኪ፥ወንድ፥ከሆንክ፥አለቆችህን፥በመኪና፥አሣፍረህ:በአሁኑ፥ስዓት
   ወደ፥አዲስ፥አበባ፥መሰመር፥ላካቸዉ፥፥ መንገድ፥ላይ፥ምን፥እንደሚጠብቅህ፥ታይ፥ነበር!
   ጉሮሮህ፥ሲታነቅ፥እንደልማድህ፥አንበጣህን፥መብላት፥ትጀምራለህ፥:
   ቆሻሻ፥ወያኔ!

   Abel
   October 26, 2018 at 12:23 am
   Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.