/

የቴዲ አፍሮ የኮንሰርት ትኬት ፎርጂድ ተሰራ

1 min read


(ዘ-ሐበሻ) ከዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ የሙዚቃ ኮንሰርቱን ለአዲሱ ዓመት ዋዜማ ለማቅረብ ፍቃድ አግኝቶ በኋላም ለአዲሱ ዓመት ዋዜማ መንግስት አዳራሹን ይፈልገዋል በሚል ኮንሰርቱ ለአንድ ሳምንት የተራዘመበት ቴዲ አፍሮ የቡራዩ እልቂት እንደተከሰተ “ወገኖቼ እየሞቱ አሁን መዝፈን አልችልም” በማለት ኮንሰርቱን ማራዘሙ ይታወሳል:: : (ይህን ዜና በቪዲዮ ለማየት እዚህ ይጫኑ)

በተለይም ይህ የተሰረዘው ኮንሰርት ትኬት ተሽጦ ያለቀ በመሆኑ; ትኬት የገዙ ሰዎችን ፍላጎት ለመሙላት ድምጻዊው ከዚያም በኋላ ኮንሰርቱን ለማድረግ አቅዶ የነበረ ቢሆንም በአዲስ አበባ ባለው አለመረጋጋት ሳቢያ የኮንሰርት ፈቃድ ሳያገኝ መቅረቱን ዘ-ሐበሻ እየተከታተከ ሲዘግብ ቆይቷል::

በሚሊዮን ብሮች የወጣበት ይኸው ኮንሰርት ጥቅምት 24, 2018 በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ እንዲካሄድ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፈቃድ የሰጠ ሲሆን ተሽጦ አልቋል የተባለው የቴዲ አፍሮ ኮንሰርት ትኬት በፎርጂድ መታተሙና ፎርጂድ ትኬቱም እየተሰራጨ መሆኑ ስለተደረሰበት ከዚህ ቀደም ትኬት የገዙ ወገኖች ከነገ ጀምሮ በሚኒሊየም አዳራሽ በመገኘት ትኬታቸውን እንዲያስቀይሩ ጥሪ ቀርቧል::

በከተማው ፎርጂድ የኮንሰርት ትኬቶች በመሠራጨታቸውም ሕዝቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተጠይቋል::

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.