ትግራይና ጣሊያን (ይሄይስ አእምሮ)

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |

የነገሮች መመሳሰል እንደገረመኝ እኖራለሁ፡፡ “ታሪክ ራሱን ይደግማል” መባሉም ትክክል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ላስታውስ እፈልጋለሁ፡፡ የውጫሌ ስምምነት ለምን እንደሆነ አላውቅም አሁን ትዝ አለኝ፡፡ በተለይ አንቀጽ 17፡፡
አንቀጽ 17 የውጫሌ ስምምነት ብዙ መዘዝ ያመጣች ናት፡፡ የአማርኛና የጣሊያንኛ ይዘቷ መለያየቱ ነበር ኢትዮጵያንና ጣሊያንን ብዙ ዋጋ ልታስከፍል የቻለችው፡፡ ለምን ትዝ እንዳለኝ አሁን ገባኝ፡፡ የአማራው ክልል ፕሬዝደንት አሜሪካ ገብተዋል፡፡ የአቀባበሉን ሥነ ሥርዓት እየተመለከትኩ ሳለ ነው ያቺ ነገረኛ አንቀጽ ትዝ ያለችኝ – ነፃ መሆናቸው ገርሞኝ፤ ምልባትም ከወያኔ ፈቃድ ሳያስፈልጋቸውና መቀየጃ ገመድ ቢጤ እግራቸው ላይ ሳይታሰር መሄዳቸው አስደንቆኝ፡፡
ጣሊያንና ትግራይ በብዙ ነገር ይመሳሰሉብኛል፡፡ ነገር ግን የትግራይ ጭካኔና ዐረመኔነት ከጣሊያን ጋር በፍጹም አይወዳደርም፡፡ ጣሊያን በዘርም ሆነ በቀለም ከኢትዮጵያ ጋር ዝምድና እንደሌላት ይያዝልኝ፡፡ ትግራይ ግን በዘርም፣ በሃይማኖትም፣ በቋንቋም፣ በሥነ ልቦናም፣ በኢኮኖሚም፣ በባህልም፣ …. ከኢትዮጵያውያን ጋር እጅግ እንደሚመሳሰሉና በብዙ ነገሮች እንዲያውም አንድ እንደሆኑ አስቡልኝ፡፡ እናም ቢያንስ ጣሊያኖች በግብረ ሶዶማዊ የቆሸሸ “የወንጀል ምርመራ” በቁም የመግደያ ሥልትና አሰቃቂ የእስረኞች አያያዝ ሲታሙ አልሰማሁም፡፡ ቢያንስ ጣሊያኖች እስረኞችን በርሀብና በምድር ቤት ውስጥ ሊነገር የማይችል የስቃይ ዓይነት ሲያንገላቱ እንደነበር የሚገልጽ ነገር ተጽፎ አላነበብኩም፡፡ ጣሊያኖች ጨዋ ጠላቶች ነበሩ፡፡ ጭካኔያቸው ለከት ነበረው፡፡ ሲገድሉ እንኳን በርህራሄ ነው፡፡ ሰዎች ነበሩና!
አንቀጽ 17 ነገረኛ ነበረች፡፡


“ኢትዮጵያ ለውጭ ጉዳይ ዲፕሎማሲዋ ጣሊያንን ልታማክር ትችላለች፡፡” የአማርኛው ይዘት፡፡
“ኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ግንኙነቷን በጣሊያን በኩል ታከናውናለች፡፡” የጣሊያኛው ይዘት፡፡
ወደኛው ጎዶች ላምጣው፡፡
በግልጽ ተጽፎ የማይነበበው የሕወሓት አንቀጽ እንዲህ ይላል – “ሁሉም የኢትዮጵያ ክልሎች (ወያኔ የጠፈጠፋቸው ማለት ነው) የውስጥም ሆነ የውጭ ግንኙነታቸውን ለማከናወን የትግራይ ሪፓፕሊክን ዕውቅናና ፈቃድ ማግኘት አለባቸው፡፡” የወያኔ ህገ መንግሥት አንቀጽ 11 ፡፡
የሚገርም መመሳሰል፡፡
በቀደመው የወያኔ ዘመን ትግራይ የፈለጋትን ዕቃና ገንዘብ ሁሉ ከክልሎች ስታፍስ ቆየች፡፡ የክልል መሪዎችን ልክ እንደቤት አሽከርና ገረድ በመቁጠር ስትፈልግም አስራ እየገረፈችና በሌሎች እስረኞች ላይ የምትፈጽመውን ብልግና ሁሉ ሳይቀር እየፈጸመችባው ሚስቶቻቸውንም ጭምር እየደፈረች ስትጫወትባቸው ኖረች፡፡ መሪዎቹ በቀን ስንቴ መብላት እንዳለባቸው፣ የትኅትናን ድምበር ለጣሰው የቃላት አጠቃቀሜ ይቅርታ ይደረግልኝና ስንቴ መሽናትና መፍሳትም እንዳለባቸው ስንቴ መተንፈስ እንዳለባቸው… ከትግራይ በቀጥታ በስልክና ሊቆጣጠራቸው አጠገባቸው ከተቀመጠ ትግሬ ወያኔ ትዕዛዝ እየተቀበሉ ራሳቸውን አዋርደው ሕዝባቸውንም አዋረዱ፡፡ ትግሬዎች አማራ ሆነው፣ ትግሬዎች ኦሮሞ ሆነው፣ ትግሬዎች ሃዲያ ሆነው፣ ትግሬዎች ወላይታ ሆነው፣ ትግሬዎች ጉራጌ ሆነው …. አማረ፣ ደቻሳ፣ ዋንታሞ፣ ሻመና፣ ዘበርጋ…. በሚሉ ስሞች ኢትዮጵያን ዳር እስከዳር ጋጧት – እንደጅብ ሠፍረውባት አመሸኳት፡፡ ጅብ እምብርት ያለው መሆኑን በነሱ እምብርት-አልባነት እስክናረጋገጥ ድረስ ሀገሪቱን በርሀብ አንጀታቸው ወረዱባት፡፡ የፈለጉትን መሬትና ንብረት ወደ ትግራይ አሸጋገሩ፡፡ ማይማ ወያዎችና ጀሌያቸው የቁጥርን ምንነን ማወቃቸውን እስክናረጋገጥ ድረስ በቁጥሮች እንኳ ሣቅንባቸው፡፡ ሚሊዮንንና ቢሊዮንን እንደ አምስትና አሥር ቁጥሮች አውርደው ተራ ሲያደርጓቸው “ወይ ማይምነት!” ብለን ተሣለቅንባቸው፡፡ “እገሌ የተባለው ወዲ ሐጎስ ሦስት ቢሊዮን ዶላር ዘረፈ፤ እገሌ የተባለው ወዲ አህፈሮም 10 ቢሊዮን ብር ሠረቀ…” መባልን ስንሰማ እኛ ራሳችንም የቁጥር ማይማን መሆናችንን እስክንረዳ ገረመን፡፡ ይሄ ይሄኛው ሆዳምነት እንኳን ምንም ማለት አይደለም – ደንቆሮ ጆሮ ብቻ ሣይሆን የጥጋብና እርካታ መለኪያም ስለሌለው የነሱ ለየት ቢልም ግዴለም ይሁን፡፡ ሕዝቧን ሰማይና ምድር ሊሰሙት በሚሰቀጥጣቸው ስቃይ ፍዳውን ማብላታቸው ግን ከይቅርታም በላይ ነው – ይህ ነው አብሮ የማያኗኑረው፡፡ አሁን ያ ሂደት እየቀረ ይመስላል፡፡ ስንት የሚያስቅና የሚያስገርም፣ ደም የሚያስለቅስና በትውልዶች መሀል ግርዶሽ ሆኖ እስከወዲያኛው የሚዘልቅ ነገር ስንታዘብ ቆየን፤ ወይ ጊዜ ደጉ! ይህን ሁሉ ያደረጉት ግና እነሱ ብቻቸውን እንዳይመስልህ፡፡ የኛ ኃጢኣት፣ የውጭ ጠላቶቻችን ቁሣዊ፣ አኮኖሚያዊና የመረጃ እገዛ፣ የኛ አለመተባበርና እንዲያውም መገፈታተር፣ ሌላም ሌላም…
… እንዲህ ነበርን፡፡ የወደፊቱን ደግሞ ልናይ ነው፡፡ ግን ግን ሁሉም ይህን እውነት ይገንዘብ – እግዚአብሔር በመንበሩ አለ!! ብዙ ያሳየናል ገና – በቃ፡፡ “ለለአሃዱ በበምግባሩ” እንዲል መጽሐፉ፡፡ yiheyisaemro@gmail.com

2 Responses to ትግራይና ጣሊያን (ይሄይስ አእምሮ)

 1. እኔም በጸሐፊው ሀሳብ እስማማለው ወያኔ ጊዜ ቀንቷት ደርግን አሸንፋ አዲስ አበባ ብትገባም ለ27 ዓመት ማንኛውንም ነገር እንደፈለጉ ሲያዙና ሲፈልጡ ቆይተዋል፡፡ሆኖም ግን እነዚህ ቁጥራቸው እዚህ ግባ የማይባሉ ጎጠኞችና ዘረኞች በ80 ሚሊዮን ህዝብ ላይ እንዲቀልዱ ያስደረጉን ጥቂት ሆዳም ኦሮሞዎች፣አማራዎች፣ደቡቦች፣ሶማሌዎች፣ሐረሪዎች፣ጋምቤላዎች፣አፋሮችና ቤኒሻንጉሎች ናቸው፡፡እንደ ዶ/ር አብይ ፍልስፍና ጊዜው የይቅርታ በመሆኑ አብረን ተደምረን እየተጓዝን ቢሆንም እኔ በበኩሌ ከህወሀት ጅቦች ባልተናነሰ ሁኔታ አገራችንን ለዚህ ያበቁትን ሆዳሞች ነው ሁሌም የምኮንነው፡፡አሁንም ጸሐፊው እንዳሉት ከጣሊያን በባሰ ሁኔታ በቀኝ ግዛት አገዛዛ ከያዙን የቀን ጅቦች የተላቀቅን በመሆኑ ይህ ነጻነታችን ወደ ኃላ እንዳይመለስ ነቅተን መጠበቅ አለብን፡፡

  dagnu
  December 4, 2018 at 2:58 am
  Reply

 2. I wouldnot be surprised if PM Abiy himself is the President of Tigrai since noone really knows who the President of Tigrai is.For 20+ years Dr. Abiy was speaking only Tigrigna at his work place daily to impress his TPLF masters.At the time Most of his close co-workers believed he was Tigre -TPLF member just by judging from his actions and the people he hanged around with , TPLF members were his close personal associates who he always spent his time with. At the time Dr. Abiy’s coach Meles Zenawi was being named one of the top 25 most influential Africans. Meles Zenawi influenced Ethiopia(except Tigrai) and Somalia into a hell-whole while Abiy influenced himself into getting a Colonel post.After Abiy climbed his ranks he went close to OPDO
  officials doing TPLF dirty work. According to wikipedia From 2010 until recently for 7 + years Abiy’s whereabout is not known.There are many speculations even some say at the time Abiy was working for the current Vice President of Tigrai Dr Debretsion’s espionage division.Was Abiy involved in top secret espionage mission that even wikipedia doesn’t know where he was since 2010 until recently?If so is the mission over or is he still serving the TPLF?In today’s Ethiopia majority of TPLF Tigrayans live a life full of luxury and privileges while the rest is subjected to more and more misery.Even General Kinfe from METEC was arrested because he was about to retire without giving Azeb Mesfin full authority for METEC. It was an inside TPLF quarrel between Azeb and General Kinfe over METEC nothingelse. The other charges are just for a show to make General Kinfe not dare try to takeover METEC from Azeb . Azeb learnt from her experience with effort that she will not let anyone return to fire her as Sebhat Nega did to her when Meles died. When she took over effort from Sebhat Negga she was under the impression Sebhat retired for good, only for Sebhat to return to effort to fire her. She wasn’t going to let that happen again that is why Azeb made sure this guy General Kinfe gets thrown in jail to guarantee there is no chance of him returning to METEC.

  If General Kinfe let’s Azeb takeover everything willingly, he is offered to retire with full benefits in Tigray, the safest place to live in Sub Sahara Africa given the person is a Tigre, for non Tigre Ethiopian Tigrai is the least safest place to live. In whole of Tigrai there is not a single sane person beggar.The only beggars you meet in Tigrai are very few mentally ill people .You go to other parts of Ethiopia beggars are everywhere you cannot even compare it with Tigrai, this shows Meles Zenawi’s Moto” Tigrai eskitlema lelaw yidma is in practice.”

  Mufarit
  December 4, 2018 at 5:14 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.