153 ታጣቂዎች በምእራብ ጎንደር ተያዙ

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

በምዕራብ ጎንደር ዞን ጭልጋ ወረዳ በትናንትናው ዕለት ጥቃት ከፈጸሙ ታጣቂዎች መካከል 153ቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ጣምያለው ገለጹ።

ዋና አስተዳዳሪው ‹‹በቅማንት ብሔር ስም በህቡዕ ተደራጅተው የሚነግዱ›› ያሏቸው ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የአንድ ሰው ሕይወት ማለፋ፤ 8 ሰዎች መቁሰላቸው፤ 39 ቤቶች መቃጠላቸው፤ 50 ቤቶችና 9 ወፍጮ ቤቶች መዘረፋቸው ተገልጿል።

“ጌታቸው አሰፋን አንቆ ይዞ አልሰጥም ያለው ሕወሓት በቅማንት ስም የአማራውን ክልል ለማበጣበጥ ሰፊ በጀት መድቦ እየሰራ ይገኛል:: ከነዚህም መካከል አንዱ ኦኤን ኤን እና ኦኤምኤን በተሰኙ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች በቅማንት ስም የሚነግዱ የወያኔ ተላላኪዎችን በማስቀረብ የሚያደርገው ሴራ አንዱ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በሕቡዕ ታጣቂዎችን በመላክ የአማራ ክልልን ሰላም መንሳት ነው::” በማለት አስተያየታቸውን የሰጡት አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የጎንደር ነዋሪ በቅማንት ብሔር ስም በህቡዕ ሲታኮሱ ከተያዙት ውስጥ አብዛኞቹ የቅማንት ተወላጆች አለመሆናቸውንና ተልከው የመጡ መሆናቸውን ነግረውናል::

ሕወሓት ታላቋን ትግራይ ለመገንባትና ትግራይን ከቤኒሻንጉል ጉምዝ በካርታ ለማገናኘት የቅማንትን ሕዝብ ለመጠቀሚያነት ይፈልገዋል ሲሉ በአንድ ወቅት የጎንደር ሕብረት ሊቀመንበር የነበሩት አቶ አበበ ንጋቱ ማስታወቃቸውን መዘገባችን ይታወሳል::

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.