አንድነት ለኢትዮጵያ ህልውና ወሳኝ ነው፤ መበታተን ጥቃት ነው!

1 min read

——ዓለም አቀፍ የህብረት ጥሪ———

 

አክሎግ ቢራራ (ዶ/ር)

ዶር ዐብይ አህመድ ጠ/ሚንስትር ከሆኑበት ጊዜ ወዲህ የሚካሄደው ትግል፤ በአንድ በኩል መሰረታዊ ለውጥን በሚደግፉ፤ በሌላ በኩል ይህን ለውጥ በሚቃወሙ፤ ጥቅማቸው በተነካ፤ ግዙፍ ገቢና ኃብት ሰርቀው፤ ዘርፈውና ደብቀው “ሕገ መንግሥቱ ይከበር” በሚል ተንኮለኛና ከእውነቱ የራቀ ስልት በሚጠቀሙ (Restore and maintain the past at any cost)ኃይሎች መካከል ነው። ቢያንስ የየካቲት “አብዮት” ክተካሄደበት የዛሬ አርባ አራት ዓመት ወዲህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰብአዊ መብቶቹና ነጻነቱ ተከብረው እንደ ልቡ ለማሰብ፤ ለመንቀሳቀስ፤ ከቤቱ ወጥቶ ለመግባት እየቻለ ነው። የዛሬ ስድስት ወር አይን ለአይን ለመተያየትና ለመነጋገር ቀርቶ መሳሪያ ተጠቅመው ለመገዳደል ይፈልጉ የነበሩ ክፍሎች ጭምር በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያም ባይሆን በአንድ አዳራሽ ለጋራ አገርና ለአንድ ህብረብሄር ህዝብ ፍትህ መወያየት መጀመራቸው ሁሉንም ያኮራል። ለሁሉም ተስፋ ይሰጣል።

ዋናው ተግዳሮት ምንድን ነው?

ከላይ ያቀርብኩት አስፈላጊና ወቅታዊ መብትና ነጻነት ጋሬጣ የሆነባቸው ኃይሎች ግን ለውጡ ሊያስከትለው የሚችለው እንደምታ (Scenario/Consequence) አስደንግጧቸዋል። ሆነ ተብሎ የታቀደና የተቀነባበረ ግጭት በመካሄድ ላይ ይገኛሉ። ኢላማውና ዓላማው ምንድን ነው ብየ ራሴን ስጠይቅ የማገኘው መልስ፤ ተስፋ የሰጠው መሰረታዊ ለውጥ ስር እንዳይሰድ፤ አገር አቀፍ እንዳይሆን፤ ለውጡን ሕዝቡ በባለቤትነት ይዞት ተቋማዊና ባህላዊ እንዳይሆን ታስቦ ነው የሚል መልስ አቀርባለሁ። ይኼን ስኬታማ ለማድረግ፤ በገፍ ከአገርና ከሕዝብ የተዘረፈውን ብዙ ቢሊየን ዶላር እየቸረቸረ ወንድምን ከወንድም ጋር ለማጋጨት ያልተቆጠበ ሴራና ግጭት የሚያደርግ ወይንም የሚያደርጉ ኃይሎች በጀርባ መኖራቸው የሚካራክር ሆኖ አላገሁትም።

የግጭቶና “የሽብርተኛነት” ስራዎች ጠንከር እያሉ የሄዱባቸው ምክንያቶች ብዙ ቢሆኑም፤ ከእነዚህ መካከል ሊጠቀሱ የሚገባቸው፤

 •   ለውጡ ስር ነቀል ይሆናል የሚል ጥርጣሬና ስጋት መኖሩ፤
 •   ሜቴክ የተባለው የሊቦችና የዘራፊዎች ድርጅት ልክ እንደ ደሮ ብልት እየተቆራረጠ በውስጡ የነበረው ጉድ

  እየተጋላጠ መሄዱና ከፍተኛ ዘራፊዎች መያዛቸው፤

 •   በብዙ ቢሊየን ዶላር የሚገመተውን የተዘረፈ ኃብት ማና እንደዘረፈውና የት እንደተደበቀ ክትትል የሚደረግበት ሁኔታ አመች መሆኑና ኃብቱ የተደበቀባቸው አገራት “የመተባበር ፈቃደኛነት እያሳዩ በመሄድ ላይ ናቸው” የሚል ዘገባ መሰማቱ፤
 •   ባለፉት ሶስት ዓመታት ብቻ ከ1,000 በላይ የሚገመቱ ወገኖቻችንን፤ በተለይ ወጣቶችን የጨፈጨፉት ግለሰቦችና በቅርቡ ደግሞ በጎንደር አማራውን፤ በቤኒ-ሻንጉል ጉሙዝ ኦሮሞውን በገፍ የጨፈጨፉት ግለሰቦችና ከጀርባቸው ሆነው ትእዛዝ የሰጡት “ሃይሎች” (Crimes Against Humanity) የቅርብ ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑ መታወቁ፤ ሕዝቡ እነዚህ ጨካኞች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው እያለ ጩኸት ማሰማቱ፤
 •   በዐማራውና በኦሮሞው ሕዝብ መካከል ያለው ሕዝባዊ ግንኙነት እየጠነከረ መሄዱ፤
 •   ህወሓት የፈጠረውና የተከለው የፍርሃት ድባብ ፈጽሞ እየተናደ መሄዱ ይገኙበታል።

  የግጭቶች ሴራንና ስራን አፍራሽነትና አድካሚነት በዚህ ሃተታ በዝርዝር ለማቅረብ አልችልም፤ አስፈላጊም ሆኖ አላገኘውም። በአጭሩ ግን በየመን የሚካሄደው ጦርነት የስንት ህጻናትን፤ እናቶችን፤ ሽማግሌዎችን ህይወት እንደቀሰፈው፤ ስንት ቤቶችና ንብረቶች እንደወደሙ፤ ስንት ከተሞችና መሰረተ ልማቶች እንደፈረሱ ማየት በቂ ምሳሌ በሆነ ነበር። በሶርያ የሚካሄደው ጦርነት ከፍተኛ እድገት አሳይታ የነበረችው አገር እንዴት ኋላ ቀርና ጥገኛ እንድትሆን እንዳደረጋት፤ ስንት የአገሪቱ ህጻናት፤ እናቶችና ወላጆች ከአገራቸው ተሰደው መጠለያና መኖሪያ እንዳጡ ያሳያል። የዚህች አገር ወርቃማ ቅርሶች ወደመዋል። በደቡብ ሱዳን የሚካሄደው የእርስ በእርስ ጦርነት ብዙ ሚሊየን ዜጎች እንዲሰደዱ፤ ህጻናትና ሴቶች እንደ ከብት እየታጎሩ “ለዘመናዊ ባርነት” እንዲዳረጉ አድርጓል። ወጣት ወንዶች “ወታደር ሆነው” የራሳቸውን ወገን እንዲገድሉ ተደርጓል። በዝምባብዌ የተካሄደው ምርጫ ግልጽነት፤ ነጻነትና ሃላፊነት የጎደለው ስለሆነ መንግሥቱን የሚደግፉ ወታደሮች በራሳቸው ወገን ላይ እየተኮሱ ብዙዎችን አቁሰለዋል፤ የሞቱም አሉ ተብሎ ይነረገራል። በእነዚህ አገሮች የሚካሄደውን እልቂት ያየና ለህሊናው የሚገዛ ግለሰብ በኢትዮጵያ ግጭት አጥፊ መሆኑን ሊገነዘብ ይችላል።

ሰላም፤ ፍቅር፤ አብሮ መኖር፤ መደጋገፍ፤ የሌላውን መብት ማክበር፤ ጥቃቅን ልዩነቶችን እንደ ተፈጥሮ ባህል መቀበል፤ ከሁሉም በላይ የአገርን ዘላቂ ጥቅም፤ ግዛታዊ አንድነት፤ ሉዐላዊነትና ነጻነት ለጋራ ጥቅም ሲሉ ማስቀደም መተኪያ የሌላቸው እሴቶች ናቸው።

የፌደራል ስርዓት አስፈላጊነት ሊያከራክረን አይችልም። አከራካሪው ምን አይነት የፌደራል ስርዓት እንጅ፤ የሌላውን መብት ሙሉ በሙሉ እስካከበረና እስካስከበረ ድረስ፤ እያንዳንዱ አካባቢ የራሱን አስተዳደር በራሱ ልምድና ባህል፤ በመረጣቸው ሃላፊዎች የማሳተዳደር መብቱ መጠበቅ አለበት። የዚህ ዝርዝር በውይይት፤ በድርድር፤ መብትንና ሃላፊነትን ሚዛናዊ ባደረገና አገር አቀፍ ግንኙነትን (አብሮነትን) በሚያጠናክር ሁኔታ ሊቀየስ ይችላል። “ሕገ መንግሥቱ አልተከበረም” የሚሉ ክፍሎች የትኛው የሕገ መንግሥት ክፍል አልተከበረም የሚለውን ጥያቄ የመመለስ ግዴታ አለባቸው። የጥቂቶችን የመመዝበር፤ የጥቂቶችን የጭካኔ እርምጃ የመውሰድ መብት የሚያስተናግደውን አገዛዝ ከሆነ የሕዝቡን አመጽ፤ የክፈለውን መስዋትት፤ የሚመኘውን ተስፋና ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ንቀውታል ማለት ነው። ዛሬ የሚካሄደው ለውጥ የሕዝብ እንጅ የጥቂት መሪዎች አይደለም። ስለሆነም፤ በማነም ኃይል ሊገለበጥ አይችልል።

እንደ ልብ የትም ቦታ መኖር፤ እንደ ልብ መናገር፤ መጻፍ፤ መተቸት፤ መሰብሰብና መንቀሳቀስ፤ እንደ ልብ ሳይፈሩ መኖር፤ እንደ ልብ የትም ቦታ የግል ኑሮን ለማሻሻል መሞከር፤ እንደ ልብ ወጥቶ መግባት ወዘተ የዜግነት መስፈርቶች ናቸው። ዲሞክራሲም ማለት ይኼው ነው። እነዚህ ብርቅየ እሴቶች ለኢትዮጵያ ሕዝብ የአየር፤ የውሃ፤ የምግብ ያክል አስፈላጊ መሆናቸውን ታሪካችን ያሳያል። ባለፉት ሶስት ዓመታት ብቻ፤ ለእነዚህ እሴቶችና መሰረታዊ መብቶች፤ ለእውነተኛ የዘውጎችና የዜጎች እኩልነት፤ ለፍትህ-ርትእ ፍላጎት ምክንያት፤፤ በተለይ በዐማራውና በኦሮሞ ክልሎች ከ 1,000 በላይ ንጹህ ወጣቶች በአልሞ ተኳሾችና በሌሎች የህወሓት መራሹ ኃይሎች ተጨፍጭፈዋል። ቁጥራቸው በቅጡ የማይታወቅ ወገኖቻችን አሁንም በድብቅ እስር ቤቶች እየተሰቃዩ መሆናቸው በስፋት ይነገራል። የሞቱትን፤ የቆሰሉትን፤ አካል ስንኩል የሆኑትን፤ የተሰደዱትንና የደረሱበት የማያታወቀውን ኢትዮጵያዊያን ቁጥር ለማወቅ አይቻልም።

ይህ ሁሉ ግፍና በደል ተካሂዶ፤ ዛሬ በጠ/ሚንስትር ዶር ዐብይ አህመድ የሚመራው መንግሥትና ለውጥ ከጥላቻና ከቂም በቀል በላይ እናስብ፤ አብሮነትን፤ አብሮ መኖርን፤ አብሮ ማደገን፤ ፍትህን፤ የዲሞክራሲ መሰረቶችን እናስቀድም በሚሉ መርሆዎች ሕዝብን፤ በተለይ ወጣቱን ትውልድ እየቀሰቀሰ ነው። ሰሞኑን ወደ ሰሜን አሜሪካ በመምጣት ከአማራውና ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር ውይይት የሚያደርገው፤ በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራው ቡድንም ያጠናከረው የለውጡን ወሳኝነትና አስፈላጊነት ነው። ይህን በሚመለከት አቶ አብራሃ በላይ በDecember 2, 2018 የጻፋውን ምክር ልጠቅስ እፈልጋለሁ።

“በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው ቡድን ዋሽንግተን ዲሲ በተካሄደው ስብሰባ ብዙ ነገር አብራርቷል። የአማራ ህዝብ ፍላጎት በገለጹ ቁጥር ለሀገራችን ለኢትዮጵያ ያላቸው በጎ ራዕይ በፅኑ መሰረት ላይ የተገነባ መሆኑ የሚያከራክር ሆኖ አልተገኘም። ልዑካኑ ተራ በተራ ሲናገሩ በፊት ካሰለቹን ሰዎች እጅጉን የተለዩ፣ ብሩህ ተስፋ የሰነቁ፣ በሳል ሰዎች እንደሆኑ ያስታውቃሉ። ‘ውስጥ ለውስጥ በትዕግስት የተካሄደው እጅግ መራራ ትግል በድል የተጠናቀቀው ዶ/ር አብይ አህመድ መሪያችን ሆነው ሲመረጡ ነው’ ሲሉ ገዱ፣ ህዝቡም በደመቀ ጭብጨባ አስተናግዷቸዋል።”

የዐማራውና የትግራይ ሕዝብ፤ በተለይ ኩታ ገጠም የሆኑት አካባቢዎች ሕዝብ፤ ከጥንት ጀምሮ በልዩ ልዩ መንገዶች የተሳሰረ ግንኙነት ያለው ሕዝብ ነው። በአብሮነት የታወቀ ልምድ ያለው ሕዝብ ነው። ከታሪክ አንጻር ሲታይ፤ አማራውም ሆነ ትግራዩ የተለየ መብት፤ የተለየ ጥቅም አለኝ ብሎ አያውቅም ነበር። ይህ ልዩነት የተከሰተውና ስርዓታዊ የሆነው መለስ ዜናዊና ቡድኑ የፖለቲካ ሥልጣኑን ከመያዛቸው በፊትና በተለይ ከዚያ በኋላ ነው። ይህ ግጭትን ፈጣሪ፤ ሕዝብን ከፋፋይ የፖለቲካ ሂደት መቆም አለበት።

አቶ አብራሃ በላይ እንዳስቀመጠው፤ “የነ ገዱ የትግል መንፈስ ሲፈተሽ፣ ትግራይ ውስጥ ካለው ሁኔታ በእጅጉን ይለያል። የእነ ዶ/ር ደብረጽዮን አካሄድ የትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያዊ ወገኑ ጋር ከማቀራረብ ይልቅ ማራራቅን፣ የተካረረ ጥላቻና ግጭቶች መፍጠርን የቀን ተቀን የትግል አካል አርገውት ይገኛሉ። እንደ የአማራው ልዑካን የኢትዮጵያ ትንሳኤ ሊታያቸው ቀርቶ፣ የኢትዮጵያ መፈራረስ የዘገየባቸው መስለዋል።” ኢትዮጵያ ብትፈራርስ ዋጋ የሚከፍለው የትግራይ ህዝብ ጭምር መሆኑን የረሱት ይመስላል።

page2image63168576page2image63166080page2image63167808

ከዐማራው፤ ከኦሮሞውና ከሌላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይልቅ “የሱዳን ሕዝብ ይቀርበናል” የሚለው የህወሓቶች ብሂል ከእውነቱ የራቀ ከመሆኑም በላይ እብደት ነው። ያራርቃል እንጅ አያቀራርብም። ይህ ማለት ከኢትዮጵያ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የለንም ለማለት ከሆነ የክህደት ክህደት ነው።

ጥላቻውን ለማጠናከር የተሰነዘረ አባባል ስለሆነ፤ ለጥላቻው ቦታ ባንሰጠው መልካም ነው። “እዚህ ላይ ለትግራይ ህዝብ መብት መከበር እየታገላችሁ ያላችሁ በተለይ ዓረና እና ትዴት ከፍተኛ ኃላፊነት አለባችሁ። ግንኙነታችሁ ኢትዮጵዊነትን ለማስከበር እየታገሉ ካሉት ጋር ግንባር ፈጥሮ ህዝብን እና አገርን መታደግ ለነገ የማይባል የታሪክ ግዴታ ሆኗል።”

ይህ ጥሩና ወቅታዊ ምክር ነው።

በተመሳሳይ፤ በዐማራውና በኦሮሞው ሕዝብ መካከል እንደ ገና የተፈጠረውና በመታደስ ላይ ያለው መልካም ግንኙነት ለኢትዮጵያ ዘላቂነትና ለመላው ሕዝቧ፤ የትግራይን ሕዝብ ጨምሮ ወሳኝ ስለሆነ በበለጠ ደረጃ መጠናከር አለበት።

በአጠቃላይ ሲመረመር፤ በዘውግ ሆነ በኃይማኖትና በሌላ ግለሰብን፤ ቤተሰብን፤ ዘውግንና ሌላውን ከቀየው ማባረር፤ ማሳደድ፤ መግደል፤ መሬቱን መንጠቅ፤ ቤቱንና ሌላውን ንብረቱን ማውደም ወንጀል ብቻ ሳይሆን ለአገር ደህንነትና ዘላቂነት መቅሰፍት ነው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ለማለት ይቻላል፤ ግጭት፤ ንትርክ፤ ጭቅጭቅ፤ የእርስ በእርስ ጦርነት፤ የሥልጣን ሽሚያ፤ ስግብግብነትና ሌብነት፤ በዘውጎች የማንነት ጥያቄ እያመካኙ መነገድ፤ ዘር፤ ብሄርና ኃይማኖት ቆጣሪነት፤ ቸርቻሪነትና በረባ ባልረባው እያመካኙ ግጭቶችን ቆስቋሽነት ሰልችቶታል። ሕዝቡ የሚፈልገው ራእይ፤ ተልእኮና የልማት ትኩረት ይህን አለመሆኑን ከፍተኛ መስዋእት እየከፈለ አሳይቶናል። የወደፊት ትኩረቱ ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ከድህነት፤ ከኋላ ቀርነትና ከጥገኝነት ዑደት (Vicious Cycle) ነጻ ወጥቶ ሃብታም፤ ጠንካራና ፍትሃዊ የሆነችን አገር መገንባት ነው። ይህች የተፈጥሮ ኃብት ያላት አገር ለሁሉም በቂ ናት። አትበቃንም ብለን የፈረድንባት ስግብግቦችና ራስ ወዳዶች እኛው የራሷ ልጆች ብቻ ነን።

ይኼን መሰሉን አድካሚና አድቃቂ የፖለቲካ ሂደት ባለፉት አስርት ዓመታት እያየን ሰላማዊ ሰልፍና ሌላ አምቢተናነት ስናሳይ ቆይተን ነበር። የኢትዮጵያ ሕዝብ በገንዘብ፤ በሰው ህይወትና በሌላ የከፈለውን ዋጋ በሂሳብ ለማስቀመጥ አይቻልም(The Social, economic, political and environmental costs are simply huge and incalculable). የማይካደው ሃቅ ግን ኢትዮጵያና የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፍተኛ ዋጋ ከፍለዋል፤ የአገራችን እድገት ተበክሎ ቆይቷል። በአጭሩ ያለፈውን ግዙፍ ስህተት ለመድገም መፈናፈኛ ቀዳዳ የለንም። የተኘውን አዲስ እድል ለማኮላሸት የሚፈልጉ ኃይሎች እንዲንቀሳቀሱ መፍቀድም የለብንም። ከፈቀድን ግን በታሪክ ተጠያቂዎች መሆናችን አይቀርም። የአሁኑ የለውጥ እድል የመጨረሻችን ይሆናል የሚል እምነት አለኝ። ስለሆነም፤ ይህን የማይገኝ እድል አናባክነው።

ይህ ሃላፊነት የመንግሥት ብቻ አይደለም፤ የሁላችንም ነው።

ተራው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከግልና ከቤተሰብ ኑሮው ውጭ “ነገ እከሌን ላጥቃ፤ እከሌን ልግደል” እያለ ሲያልም አያድርም። ይህን የሚያደርጉት ለሕዝብ ኑሮ ደንታ የሌላቸው፤ በአብዛኛው የፖለቲካ ጥመኞችና የቀን ጅቦች ናቸው። እነዚህ ኃይሎች የፖለቲካ ስልጣንንና ከዚህ የሚገኘውን የገንዘብና ሌላ የኢኮኖሚ ጥቅም አምላኪዎች ስለሆኑ፤ ሰላምና እርጋታ ይጎዳናል የሚል ስሌት ይከተላሉ። ግጭቶች በየቦታው ሲከሰቱ ከጀርባ ሆኖ ማን እንደሚቀሰቅሳቸው፤ ማን የመሳሪያና የገንዘብ ድጋፍ እንደሚሰጣቸው ምርመራና ጥብቅ ክትትል መደረግ ይኖርበታል። ቀስቃሺዎቹ ችላ ከተባሉ ሴራቸውን በስፋትና በጥልቀት ይቀጥሉበታል። የሰላም፤ እርጋታና አብሮነት ትግል ድንበር የለውም፤ ዘውግና መደብ አይለይም። ሁላችንም አጋርና ተባባሪ መሆን አለብን።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የደህንነት፤ የፌደራል ፖሊስና መከላከያ ተቋማት፤ ፍርድ ቤቶችና ሌሎች ትኩረታቸውና ዋናው ስራቸው ሰላምና እርጋታ በመላው ኢትዮጵያ ስኬታማ እንዲሆን ማድረግ ነው። ሆኖም፤ እነዚህ ተቋማት ሙሉ በሙሉ ከሰርጎ ገቦች ካልጸዱና የሕግ አስከባሪ ሚናቸውን ለመወጣት ካልቻሉ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ ይሆናል።

ዛሬ የሚካሄደው፤ በአብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚደገፈው፤ ወደ መሰረታዊ ለውጥ ለማምራት ከፍተኛ እድል ያለው ለውጥ ከመጀመሩ

በፊት የውጭና የውስጥ ታዛቢዎች ያቀርቡት የነበረው ዘገባ ኢትዮጵያ “የመፈራረስና የእርስ በርስ ግጭት” ከሚከሰትባቸው፤ እንደ ሶሪያ፤ የመን፤ ኢራክ፤ ሶማልያ፤ አፍጋኒስታን፤ ደቡብ ሱዳንና ሌሎች ተመሳሳይ የመፈራረስ እድል ከገጠማቸው አገሮች መካከል አንዷ ትሆናለች የሚል ነበር። ይህ አለመሆኑ ብቻ እኛን ሊያስደስተንና ሊያኮራን ይገባል። ከእርጋታ፤ ከሰላም፤ ከብሄራዊ መግባባት፤ ችግሮችን በውይይት ብቻ ከመፍታት፤ ከሕግ የበላይነት፤ ከአብሮነት የሚገኘው ጥቅም ከትሪሊየን ዶላር ገቢ በላይ ነው። ላወቀበትና አስተዋይ ለሆነ ግለሰብ ወይንም ቡድን፤ አገር በብዙ መቶ ትሪሊየን ዶላር አይገዛም። አገር ከሌለ ሰብአዊ መብት፤ ነጻነት፤ ዲሞክራሲ ወዘተ አይታሰብም። ሰላምና እርጋታ ስኬታማ ከሆኑ ዲሞክራሳዊ ስርዓት የመገንባቱ እድል ከፍ ያለ ይሆናል።

ሌብነት፤ ሙስና፤ ዘውጋዊ አድልዎ፤ የአገርን ኃብት ማሸሽ፤ አፈና፤ የዘር ማጥፋት፤ ግድያና ሌሎች ጠንቆች ስር መስደዳቸው ከቀጠለ ዲሞክራሲ አይታሰብም። እነዚህ ጠንቆች የግጭት መንስኤና መጋቢ ናቸው። የኢትዮጵያ ወጣት ትውልድ በገፍ መስዋእት ሆኖ ህብረተሰቡን በማንቀሳቀስና ግፍና በደል ያደከመው ሕዝብ “የጨቋኞችና የጅቦች ዘመን በቃኝ” በሚል መፈክር የተነሳባት ኢትዮጵያ ተመልሳ ወደ ነበረችበት አሰቃቂና ግፈኛ ስርዓት ትመለሳለች የሚል ፍርሃትና ስጋት የለኝም። ሕዝብ የጠላው መንግሥት ሊመለስ አይችልም። ኢትዮጵያ ከስህተታቸው የተማሩና የሚማሩ፤ ደፋር፤ አስተዋይ፤ አገር ወዳድ፤ ሕዝብና ፍትህ አፍቃሪ መሪዎችን በመፍጠር ላይ ትገኛለች። ራሷን እያደሰች ነው ለማለት እደፍራለሁ። ጠ/ሚንስትር ዶር ዐብይ አህመድ የዚህ አዲስ አመራር ሞዴል ወይንም ተምሳሌት ናቸው። የሕዝብ ትግል የፈጠራቸውና በሕዝብ የተደገፉ መሪ ናቸው።

ግን፤ ጠ/ሚንስትሩ ስው መሆናቸውን አንርሳ፤ ሁሉን ተግዳሮት በአንድ ጊዜ ሊለውጡት አይችሉም።

በየትኛውም አገር መሰረታዊ ለውጥ ሲካሄድ ግጭቶች መከሰታቸው አይቀርም። ግጭቶቹን የሚያባብሱት ኃይሎች ህወሓቶች ብቻ አይደሉም። የእነሱ ተባባሪዎች የሆኑ ልዩ ልዩ ኃይሎችና ሆዳሞች አሉ። ቁም ነገሩ ግን፤ እነዚህ ግጭቶች ስር እንዳይሰዱ፤ እንዳይስፋፉና ለውጡን እንዳይበክሉት ማድረግ የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ግዴታ ነው። ምክንያቱም ግጭት አድካሚና አውዳሚ ነው። ማንንም አይምርም።

የግጭቶችን አክሳሪነት በሊብያ፤ በየመን፤ በጎረቤት ሶማልያ፤ በሶርያ፤ በኢራክ፤ ለአስርት ዓመታት ጦርነት በሚካሄድባት አፍጋኒስታን፤ “ነጻነት” ተቀዳጀሁ በምትለው በደቡብ ሱዳን ስንመለከት ቆይተናል። የእርስ በእርስ ሆነ ሌላ ጦርነት ያመክናል፤ የተሰራውን መሰረተ ልማት፤ ኢንዱስትሪና ሌላ ያወድማል። የዜጎችን ህይወት ይቀስፋል። ስደተኛ፤ ለማኝና ጥገኛ ያደርጋል። ግጭት ድንበር የለውም። ህጻን፤ ሽማግሌ፤ ሴት፤ ወንድ፤ ዘውግ፤ ሃብታም፤ ደሃ፤ መደብ፤ ኃይማኖት አይለይም። እነዚህን አገሮች መልሶ ለማቋቋም አስርት አመታትና ብዙ ትሪሊየን ዶላር ኢንቨስትመንት ይጠይቃል። አንዳንድ የወደሙ ታሪካዊ ቅርሶች ሊተኩ አይችሉም። ፖል ኮሌየር የተባለው ኢኮኖሚስት ባደረገው ጥናት መሰረት የእርስ በእርስ ጦርነት(Civil conflict and war triggers irreversible damage/የማይመለስ ዋጋ ያስከፍላል)።

የፖለቲካ ስልጣኔንና ከዚህ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለውን የኢኮኖሚ ምዝበራየን ለምን ተነጠኩ የሚለው ህወሓት ዱሮ ተቃዋሚ (ዛሬ ተፎካካሪ ተብሎ የሚጠራውን) ክፍልና ሌሎችን ንጹህ ኢትዮጵያዊያን በውሸት መረጃ ጨፍጭፏል፤ አስሯል፤ ገርፏል፤ አካለ ስንኩል አድርጓል፤ እናቶችን፤ ልጃገርዶችን አዋርዷል፤ እንዲሰደዱ አድርጓል። ድርጅታዊ ምዝበራ አካሂዷል። የአገራችንን ዘላቂ ጥቅምና ብሄራዊ ደህንነት፤ ዳር ድንበር፤ የባህር በር ንዷል፤ ክዷል። ሕዝቧ እርስ በእርሱ እንዲጋጭ አድርጓል። ይህ እንዲቀጥል ይፈልጋል የሚሉ ክፍሎች አሉ። ሃላፊነትና ተጠያቂነት አለበት ማለት ነው።

ኢትዮጵያ ሁለት መንግሥታት የሏትም። ታዛቢዎች እንደሚሉት ከሆነ፤ ይህ ቡድን ልክ የራሱ “የተለየ መንግሥት፤ የተለየ ምሽግ፤ የተለየ ኃይል፤ የተለየ አቅም” እንዳለው አድርጎ ራሱን በመገመት ዛሬ፤ በየቦታው፤ የሰበሰበውን ብዙ ቢሊየን ዶላር ኃብት እየተጠቀመ አገራችን ኢትዮጵያ ሰላምና እርጋታ እንዳይኖራት፤ የሕዝቡ ዋና ትኩረት ወደ ብሄራዊና አካባቢያዊ ግንባታ ስራ እንዳይዞር እያደረገ መሆኑ በሰፊው ይነገራል።

ይኼ የፖለቲካ ሂደት ለትግራይ ሕዝብ አያዋጣም፤ የሚያዋጣው አማራጭ ሰላማዊ ለውጡን መደገፍ ብቻ ነው። ከፍተኛ ትኩርትና ጥረት መደረግ ያለበት ነገሮችን በማባባስ ዙሪያ አይደለም። እርቅና ሰላም እንዲሰፍን ያልተቆጠበ ጥረት በማድረግ ዙሪያ ነው። በተለይ፤ በማህበረሰባዊ ሜዲያና በሌላ የሚደረገው አስቀያሚ ወቀሳ፤ መወነጃጀል፤ የግጭት ቅስቀሳ፤ ስድብና ዛቻ በአስቸኳይ መቆም አለበት።

ብዙ ኢትዮጵያዊያንን ያስቆጣው የቅርብ እልቂት፤ የኦሮሞ የፊደራል፤ የአካባቢ ፖሊሶችና ሌሎች ወንድሞቻችን መደበኛ ስራቸውን ሲሰሩ የተደረገው ግድያ ነው። ይህ ክስተት፤ ግጭቱን ከፍ ለማድረግ የተሞከረ ህገ-ወጥ፤ የወንበዴና የሽብርተኛ ስራና ሴራ ነው ለማለት ያስደፍራል። ሕግ አስከባሪዎች የነፍሰ ገዳዮች ኢላማ ከሆኑ ማን በሰላም ለመኖር ይችላል፤ ማን ሕግን ያስከብራል? ማን የአገሪቱን ደህንነት ይንከባከባል?

ይህ አዲስ አል-ሸባብ መሰል“ሽብርተኛነት” ከአሁኑ ካልተገታ እየተስፋፋ እንደሚሄድ ማጤን ያስፈልጋል።

ጠ/ሚንስትር ዶር ዐብይ የተቻላቸውን እያደረጉ ነው። ስለዚህ፤ እኛ በአገር ቤትና በውጭ የምንኖር ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ ድርሻችን የዘነጋን ይመስለኛል። ሰላምና እርጋት በመላው ኢትዮጵያ እስካልተረጋገጠ ድረስ፤ ስራችን ገና አላለቀም። ዓለም አቀፍ ትብብር ያስፈልጋል የምልበት ምክንያት፤ በጠ/ሚንስትር ዶር ዐብይ ታታሪነት፤ ብልህነትና አዋቂነት የሚመራው ለውጥ እንዳይቀለብስ ድርሻችን እንወጣ ለማለት ነው።

page4image63143104page4image63143488page4image63142912page4image63141568page4image63140608

የተሰረቀውንና ከአገር የሸሸውን ግዙፍ ኃብት በሚመለከት፤ በአገር ቤት ያለውን የሰላምና የእርጋታ አስፈላጊነትና የህወሓትና አጋር ግለሰቦችን/ቡድኖችንና ሌሎችን አፍራሽነት፤ ሽብርተኛነትና ሰላማዊ ለውጡን አልቀበልም ባይነት ማጋለጥ አስፈላጊ ነው።

ይህን ለማድረግ የሚቻልባቸው ልምዶችና ዘዴዎች አሉ። ከእነዚህ መካከል፤

ሰላማዊ ሰልፍ ለምን አስፈለገ?

የመጀመሪያው ትኩርታችን መሆን ያለበት፤ ሰላማዊ ለውጡ ለኢትዮጵያ ህልውናና ለመላው ሕዝቧ ደህንነትና ልማት አስፈላጊና ወሳኝ መሆኑን በድምጻችን፤ በጽሁፋችንና በስብሰባዎቻችን ማስተጋባት ነው። በማንኛውም ንጹህ ኢትዮጵያዊ ግለሰብ ወይንም ዘውግ ላይ እንደ ገና ግፍና ጭካኔ እንዳይደገም በማጤንና ባለፉት ሶስት ዓመታትና በቅርቡ የተጨፈጨፉት ሰማእታት እንዳይረሱና አሁን የሚካሄደው ለውጥ እንዳይቀለበስ በማሰብ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቀነባበረ የድጋፍ ዘመቻ ማካሄድ አስፈላጊ ነው። በተጨማሪ ልናደርጋቸው የምንችለው፤

 •   እያንዳንዳችን ጥላቻን ከራሳችንና ከቤተሰባችን መቅረፍ፤
 •   በዘውጎች መካከል ውይይትና መተማመን ለመፍጠር ጨዋነት የተሞላበትና ያልተቆጠበ ጥረት ማድረግ፤
 •   የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪካዊ ወንድማማችነት/እህትማማችነት ጠንካራ መሆኑንና የትግራይ ሕዝብ ሆነ ሌላው በማንኛውም ኢትዮጵያ የመኖር፤ ኃብት የመያዝና ሌላ ሰብአዊ መብት እንዳለው እናስተጋባ፤
 •   የሕዝብ ለሕዝብ ውይይት እንዲካሄድ ያልተቆጠበ ጥረት እናድርግ፤
 •   ባለፉት ዓመታት የተፈጸሙ ወንጀሎችን–የነፍስ ግድያ፤ የዘር/ብሄር ማጥፋት፤ ዜጎችን ማሰቃየት፤ ግለሰቦችን አካለ ስንኩል ማድረግ፤ የአገሪቱን ግዙፍ ኃብት መስረቅና ከአገር ማሸሽ፤ ሰላምና እርጋታ እንዳይኖር በየቦታው ግጭቶችን መቀስቀስ ወዘተ– ኢትዮጵያንና መላውን ሕዝቧን ስላደሙት፤ እነዚህ ወንጀሎች በመረጃ ተደግፈው፤ አግባብ ባለው በተባበሩት መንግሥታት የወንጀል ፍርድ ቤት ክስ እንዲቅርብባቸው እንረባረብ፤ ባለሞያዎችን እንቀስቀስ፤ እናስተባበር፤ ድጋፍ እንስጣቸው፤
 •   ግጭቶች እንዲቆሙ ያልተቆጠበ ጥረት እናድርግ፤
 •   ትምህርታዊውይይቶችንናሰሚናሮችንበሃገርቤትናበውጭሃገርእናካሂድ።

  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
  የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነትና እኩልነት ይከበር! December 6, 2018

page5image63136576page5image63138304

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.