/

“በጨዋታው በርካታ ለጎል የሚሆኑ እድሎችን አግኝተን የነበረ ቢሆንም ተጨዋቾቼ አልተጠቀሙበትም”

1 min read

ትላንት ጅማ አባ ጅፋርን 2 ለ ምንም ያሸነፈው የግብፁ አልሃሊ ክለብ አሰልጣኝ ሞሃመድ ዩሱፍ በርካታ ግቦችን ባለማግባታቸው መቆጨታቸውን ገለፁ፡፡

አህራም ኦንላይን እንደዘገበው ከጨዋታው በኋላ መግለጫ የሰጡት አሰልጣኙ ‹‹ያገኘነው ውጤት ጥሩ ቢሆንም ከቀጣዩ የመልሱ ግጥሚያ በፊት ማለፋችንን ለማረጋገጥ በርከት ያሉ ግቦችን እንደምናገባ ተስፋ አድርጌ ነበር፡፡›› ብለዋል፡፡ ጨምረውም ‹‹በጨዋታው በርካታ ለጎል የሚሆኑ እድሎችን አግኝተን የነበረ ቢሆንም ተጨዋቾቼ አልተጠቀሙበትም›› በማለት አስረድተዋል፡፡ የዚህ ጨዋታ የመልስ ግጥሚያ በሚቀጥለው ሳምንት በአዲስ አበባ ይካሄዳል፡፡

በካይሮ የሚኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን በስታዲየሙ በመገኘት ለጅማ አባጅፋር ስፖርት ክለብ ድጋፋቸውን ሰጥተው የነበረ ሲሆን የጅፋር ተጫዋቾች በውጤቱ ደስተኛ እንዳልሆኑና አዲስ አበባ ላይ ውጤቱን ለመቀየር እንደሚጥሩ መግለጻቸውን ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ችለናል::

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.