/

የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን ከወልዋሎ ጋር ላለበት ጨዋታ መቀሌ ሲደርስ ደማቅ አቀባባበል አቀባበል ተደረገለት

1 min read

የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን ከወልዋሎ ጋር ላለበት ጨዋታ መቀሌ ሲደርስ ደማቅ አቀባባበል አቀባበል ተደረገለት:: 

የጎንደሩ ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ከወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርስቲ ጋር ለመጫዎት ከአንድ አመት በኅላ ነው ወደ መቀሌ  ያመራው:: ላለፈው አንድ ዓመት የአማራና የትግራይ ክልል ክለቦች የሚገናኙባቸው የፕሪምየርሊግ ጨዋታዎች በገለልተኛ ሜዳዎች ሲደረጉ መቆየታቸው የሚታወስ ሲሆን የሁለቱ ክልሎች ክለቦች እርስ በ እርስ ር የሚገናኙባቸውን ጨዋታዎች በሜዳቸው ለማስተናገድ ፍቃደኝነታቸውን በክልሉ ባለስልጣናት በኩል ጭምር ማሳወቃቸውን ዘ-ሐበሻ ሲዘግብ ነበር::

የወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ክለብ ደጋፊዎች እና የመቀሌ ነዋሪዎች እንኳን ደህና መጣችሁ በሚሉ ባነሮችን ጭምር በመያዝ የፋሲል ከነማ ቡድንን የተቀበሉት ሲሆን  ነገ እሁድ ታኅሳስ 28 ቀን 2011 09:00 የሚደረገው ጨዋታ በሰላም ተጀምሮ እንዲያልቅ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል::

1 Comment

  1. Peace be with my people there never been hate between people’s but corrupted,selfish ,narrow minded poleticians there blinded supporters and paid agents .

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.