ፋሲል ከነማ ደጋፊዎች አሳፍሮ ከባህርዳር ወደ ጎንደር በማምራት ላይ ያለ አውቶብስ…

Filed under: News Feature,ስፖርት |

ፋሲል ከነማ ደጋፊዎች አሳፍሮ ከባህርዳር ወደ ጎንደር በማምራት ላይ ያለ አውቶብስ ተገልብጦ በሰው ህይወት እና አካል ላይ ጉዳት መድረሱ ተነግሯል።

የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ደጋፊዎቹ ትናንት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 12ኛ ሳምንት በባህርዳር ከተማ እና ፋሲል ከነማ መካከል ከተደረገው ጨዋታ በኃላ ወደ ጎንደር እየተመለሱ ጣራ ገዳም በሚባል አካባቢ ሲደርሱ ነው የመኪና አደጋው ያጋጠማቸው።

በአደጋውም የሁለት ደጋፊዎች ህይወት ሲያልፍ ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ደጋፊዎች ላይም የተለያየ መጠን ያለው የአካል ጉዳት መድረሱ ተገልጿል።

በተሽከርካሪ አደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ደጋፊዎች በጎንደር ሆስፒታል እና በአዲስ ዘመን ሆስፒታል ህክምና እየተከታተሉ መሆኑን የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ አስታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.