ዛሬ በዱባይ በተካሄደው ማራቶን ኢትዮጵያዊያን ድል ቀናቸው፣ ጌታነህ ሞላ የቦታውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ አሸንፏል

Filed under: News Feature,ስፖርት |

ዱባይ በተካሄደው የማራቶን ውድድር በወንዶች አትሌት ጌታነህ ሞላ 2 ሰአት ከ ደቂቃ ከ34 ሰከንድ የሆነ ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ሲያሸነፍ፤ ሂርጳሳ ነጋሳ ሁለተኛ፤ እንዲሁም አሰፋ መንግስቱ ሶስተኛ በመሆን አጠናቀዋል፡፡

 

ከ5 እስከ 9 ያለውን ደረጃም የያዙት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሆነዋል፡፡  በሴቶች በተካሄደው ውድድር ኬንያዊቷ ሩት በአንደኛ ስትወጣ እሷን በመከተል ወርቅነሽ ደገፋ ሁለተኛ፤ ወርቅነሽ ኢዶሳ ሶስተኛ፤ ዋጋነሽ መነካሻ አራተኛ፤ ስንታየሁ ለውጠኝ አምስተኛ፤ ራህማ ቱሳ ስድስተኛ፤ ሙሉሀብት ፀጋ ሰባተኛ እንዲሁም ሱሌ ኡቱራ ስምንተኛ በመውጣት በድጋሚ በዱባይ ማራቶን የበላይ መሆናቸውን አሳይተዋል፡፡

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.