/

 ሕወሓቶች ለምን ኪሮስ ዓለማየሁን ገደሉት? –

1 min read

ብዙም የማይወራ ወይም ያልተወራ ርዕስ ነው:: በዚህ ጉዳይ የኢትዮሚዲያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ አብርሃ በላይ የጻፈውን ከማንበቤ በፊት ስለኪሮስ ዓለማየሁ የሙዚቃ ሕይወት ጥቂት ላስተዋውቃችሁ::

ለአማርኛ ሙዚቃ – ጥላሁን ገሰሰ; ለኦሮሚያ ሙዚቃ አሊ ቢራ; ለትግርኛ ሙዚቃ ኪሮስ ዓለማየሁን በአንደኝነት የሚያስቀምጡና ለሙዚቃው እድገት ወሳኝ ሚና እንደነበራቸው የሚመሰክሩ በርካታ ናቸው:: 

ኪሮስ ዓለማየሁ በ1948 ዓ.ም.   የተወለደው በትግራይ ክልል ክዕልተ አውላሎ አውራጃ ፀአዳ አምባ ወረዳ ሰንደዳ ቀበሌ ነው፡፡  የቀለም ትምህርቱንም ከቤተክህነት ጀምሮ እስከ ሁለተኛ ደረጃ የተማረው  እዚያው ትግራይ ሲሆን የመጀመሪያና 2ኛ ደረጃ ትምህርቱን እንዳጠናቀቀ በአፄ ዮሐንስ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለ3 ዓመታት በመምህርነት ማገልገሉን; ከዚያም ለሙዚቃ ባለው ዝንባሌ በራሱ ዜማና ግጥም ደራሲነት የትግሪኛ ጨዋታዎችን ለሰፊው ሕዝብ በማቅረብ እና በክራር ተጫዋችነቱ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ማግኘቱን ከሕይወት ታሪኩ ተጽፎ አይተናል:: 

ኪሮስ በ1975 ዓ.ም. በራስ ቲያትር ቤት ተቀጥሮ ከመስራቱ በፊት የትግራይ ክ/ሀገር የኪነት ቡድን ረዳት አሰልጣኝ ሆኖ አገልግሏል ።  በሀገር ውስጥ ከሚጫወታቸው አዝናኝ የትግርኛ ዘፈኖች በተጨማሪ ከሌሎች የሥራ ባልደረቦቹ ጋር በመሆን በተለያዩ ሃገራት በመዞር ሃገራችንን በመወከል ሥራዎቹን አቅርቧል:: 

እጅግ የተዋጣለት የሙዚቃ አልበም ለአድማጩ በማቅረብ የሚታወቀው ድምፃዊ ኪሮስ አለማየሁ በራስ ቴአትር ቤት ቆይታው በጊዜው ከነበሩት ዝነኛ ድምፃውያን አጋሮቹ ጋር በመሆን በሙዚቃ ሥራው የራስ ቴአትርን ቤት ብቻም ሳይሆን የአገር አቀፍ ዝናና ተወዳጅነትን ያተረፈ ተጠቃሽ ሙያተኛ ነበር፡፡

ከአሥራ አምስት ዓመታት በላይ በኪነጥበቡ ዘርፍ የሠራው ድምፃዊ ኪሮስ አለማየሁ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ አብዘኛው ብሔረሰቦች ባንዴ እንደሚያደምጡት ይነገራል::  ምክንያቱ ደግሞ ኪሮስ ዜማዎቹንም ሆነ ግጥሞቹን እንዲሁም ቅንብሩን ሲሰራ ጊዜ ወስዶና ተጠብቦ በተመስጦ በመሆኑ ነው ይላሉ በቅርብ የሚያወቁት የሙያ ባልደረቦቹ፡፡ በዚህም ሙዚቃ የአለም ቋንቋ ነው የሚለውን ብሂል ኪሮስ አለማየሁ ተርጉሞት አልፏል ማለት ነው::

ድምፃዊ ኪሮስ አለማየሁ ከፈጠራ ሥራዎቹ ለዜማና ግጥም ለሙዚቃ ቅንብር ይዘቶቹ በተቸገረ ስለሆነ ከበሮ አመታትና ጭብጨባ ባህላዊ ሥረዓት በወጉ አውቆ ያሣወቀ እንዲሁም በርከት ያሉ የባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎችን ጠንቅቆ የሚጫወት አሰደናቂ የጥበብ ሰው ነበር፡፡ ዛሬ ይህ ተወዳጅ ድምፃዊ በህይወት ባይኖርም ከአብራኩ የወጣችዋን እንሥት ልጁን ለኪነጥበብ ሙያ አድናቂዎቹና ወዳጆቹ ተክቷል፡፡

አሁን ወደ አብርሃ በላይ ጽሁፍ እናልፋለን:: ሕወሓቶች ለምን ኪሮስ ዓለማየሁን ገደሉት?

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.