/

ናይጄሪያዊው አጥቂ ኦኪኪ አፎላቢ በመጨረሻም የጅማ አባጅፋር ንብረት ሆኗል

1 min read

በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ስኬታማ ጊዜ ካሳለፉ የውጭ ተጫዋቾች መካከል አንዱ የሆነው ናይጄሪያዊው አጥቂ ኦኪኪ አፎላቢ የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነትን በ23 ግቦች ካጠናቀቀ በኃላ ውስብስብ በሆኑ አወዛጋቢ ጉዳዮች ታክለውበት ወደ ግብፁ ኢስማኤል ቢያመራም እምብዛም የመጫወት ዕድል ባለማግኘቱ ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል፡፡ ዳግም ከተመለሰ በኋላ የቀድሞው ክለቡን በስፋት ይቀላቀላል ቢባልም በርካታ ክለቦች እሱን ፈላጊ በመሆናቸው ወደ ጅማ የመዘዋወሩን ጉዳይ አጠራጣሪ  አድርጎት ቢቆይም በመጨረሻም የጅማ አባጅፋር ንብረት ሆኗል ሲል ኢትዮሶከር ዘግቧል::

በሌላ ስፖርት ዜና በ2010 በጊዜያዊ አሰልጣኝነት ከተሾሙ በኋላ በአፍሪካ ኮንፌድሬሽን ዋንጫው ውጤታማ የውድድር ጊዜ የነበራቸው እና በዘንድሮው ፕሪምየር ሊግ ውድድር ውጤት የራቃቸው አሰልጣኝ ዘነበ ፍሰሀ ዛሬ ከወላይታ ድቻ ጋር በስምምነት ተለያይተዋል፡፡

 አሰልጣኙ በትግራይ ስትዲየም በደደቢት ከተረቱ በኃላ ክለቡ እንዲለቃቸው ደብዳቤ ያስገቡ ሲሆን ከወልዋሎ በሜዳቸው 1-1 ነጥብ ከተጋሩ በኃላ ከደጋፊዎች ተቃውሞ ማስተናገዳቸውን ተከትሎ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ከክለቡ ጋር ለመለያየት ጥያቄ ማቅረባቸውን መግለፃቸው ይታወሳል። ነገር ግን ቦርዱ ከደጋፊዎች ጋር ከተነጋገረ በኋላ በድጋሚ ሀሳባቸውን አስቀይረው ክለቡን እንዲመሩ መደረጉም ይታወሳል፡፡ ሆኖም ክለቡ በተደጋጋሚ በውጤቱ ላይ መሻሻል ባለማሳየቱ አሰልጣኙ ያቀረቡት ጥያቄ ዛሬ አመሻሽ 11:00 ላይ ተቀባይነት አግኝቶ በይፋዊ ስምምነት ከክለቡ ጋር ሊለያዩ ችለዋል፡፡

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.