አዲሱ አረጋ ከለገጣፎ መልስ የጻፉት ጽሁፍ

1 min read

በለገጣፎ ለገዳዲ ህገወጥ ናቸው በሚል እየተፈጸመ ያለው የድሃ ወገኖቻችንን መኖሪያ ቤቶች በተመለከተ ላለፉት ቀናት በስፋት እየዘገብን ይገኛል:: ሌሎች በርካታ ሚዲያዎችም ትኩረት ሰጥተው እየሰሩበት ይገኛሉ:: አብዛኛው ዘገባ እያተኮረ ያለው የወገኖቻችን ስቃይ መመልከቱና ማየቱ ላይ እንጂ መፍትሄው ምንድን ነው? እነዚህ ወገኖች ቀጣይ እጣ ፈንታ ምን ይሆናል? መንግስት ካለቤት የቀሩትን ወገኖች ምን ሊያደርጋቸው ነው? የሚሉ ጉዳዮች ትኩረት አልተሰጠባቸውም::’

ቤታቸው የፈረሰባቸው ወገኖች ተወካዮች ትናንት ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ከተወያዩ በኋላ ዛሬ ደግሞ የክልሉ መንግስት ማብራሪያ እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው ተሰምቷል:: በተጨማሪም በዛሬው ዕለት የፕሬስ ሴክረተሪያቸውን አቶ ንጉሱ ጥላሁንን ከኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ጋር ወደ ስፍራው ልከዋል::

ዛሬ ወደ ስፍራው የተጓዙትና ቤታቸው የፈረሰባቸውን ወገኖችን ከጎበኙት መካከል የኦሮሚያ ክልል የገጠር ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊና የኦዲፓ ስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ አዲሱ አረጋ ይገኙበታል:: አቶ አዲሱ እነዚህን ወገኖች ሄደው ካነጋገሩ በኋላ “ህገወጥ ግንባታን በተመለከተ” በሚል ጽሁፍ ጽፈው በፌስቡክ ገጻቸው ለቀዋል:: ለዘ-ሐበሻ ቤተሰቦች ለግንዛቤ ይረዳል በሚል አቀናብረን ይዘንላችሁ ቀርበናል ተከታተሉት:: የአቶ አዲሱን ጽሁፍ ተከታትላችሁ አስተያየታችሁን ከታች ማስቀመጡን እንዳትዘነጉ::