በለገጣፎ ጉዳይ የኦሮምያ ክልል ፕረዚዳንት ለማ መገርሳ አቅጣጫ አስቀመጡ

1 min read

በለገጣፎ የተወሰደውን እርምጃ ተከትሎ በአፈጻጸሙ ሂደት የተፈጠሩ ግድፈቶች እና ስህተቶች ካሉ ለይቶ ማረም አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ ይህንን ጉዳይ የሚያጣራ አንድ ግብረ ሀይልም ተደራጅቶ ወደ አካባቢዉ እንዲሰማራ የኦሮምያ ክልል ፕረዚዳንት ለማ መገርሳ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን አቶ አዲሱ አረጋ ገልጸዋል::


ግብረ ሃይሉም በጥቂት ቀናት ዉስጥ ወደማጣራት ስራ የሚገባ እና አጣርቶ በሚያቀርበዉ ሪፖርት መሰረትም ህገወጥ ግንባታን በማፍረስ ሂደት የተፈጸሙ ስህተቶች ካሉ ህግን ተከትሎ እርማት እንደሚወሰድ የገለጹት አቶ አዲሱ ህገ ወጥ ግንባታ የፈረሰባቸዉ የደሃ ደሃ የሆኑ ወገኖቻችን ያለ መጠለያ እንዳይቀሩ ግብረ ሃይሉ አጣርቶ በሚያቀርበዉ መሰረት ህግና ስርዓትን በተከተለ መንገድ በአጭር ጊዜ ውስጥ መፍትሄ እንዲያገኙ ይደረጋልም ሲሉ ተናግረእዋል::
“የተወሰደው ዕርምጃ ቀአንድ ብሄር ላይ ያተኮረ ጥቃት አስመስሎ በማህበራዊ ሚዲያ እና በሌሎች ሚዲያዎች እየቀረበ ያለው ዘገባ ግን ሀሰት መሆኑ ተረጋግጧል” በማለት አቶ አዲሱ አረጋ ጽፈው አንበበናል::