የሳኡዲ አረቢያ መንግስት ኢትዮጵያዊያን የቤት ሰራተኞችን በተመለከተ አዲስ ህግ አወጣ!

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

 

አለ ማዲና ለተሰኘው በአረብኛ ቋንቋ ለሚታተመው ጋዜጣ መግለጫ የሰጡት በጂዳ ንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት የስራ ቅጥር ኮሚቴ ሊቀመንበሩ ያህያ አል ማቅቡል እንደተናገሩት ወደሳኡዲ ለስራ የሚሄዱት ሴቶች እድሜ ከ23 አመት እንዳያንስ አዲስ መመሪያ ወጥቷል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ሴቶቹ በአገራቸው ማሰልጠኛ ተቋም የሚሰጠውን ስልጠና ቢያንስ ለ30 ቀናት መከታተል እንዳለባቸው ጠቁመው የቤት ውስጥ ስራዎችን ማከናወን የሚችሉ ሊሆኑ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

 

እነዚህ ሴቶች ከተላላፊ በሽታዎችና ከወንጀል ነፃ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ እንደኒገደዱም አስረድተዋል፡፡ በተጨማሪም አዲስ አበባ የሚገኘው የሳኡዲ አረቢያ ኤምባሲ እውቅና ወደሚሰጠው ሆስፒታል በመሄድ የስነልቦና ጤና ምርመራ ተደርጎላቸው ካለፉ ብቻ እንደሚቀጠሩ አል ማቅቡል ይፋ አድርገዋል፡፡ እነዚህን መስፈርቶች የሚያሟሉ ሴቶች ከ900 ሪያል (240 ዶላር) ጀምሮ ሳኡዲ ውስጥ እንዲቀጠሩ ሁኔታዎች መቻቸታቸውንም ጠቁመዋል፡፡ በተለይም ከመጪው ረመዳን የፆም ወር በፊት አገሪቱ በርካታ ሰራተኞችን ለመቅጠር እንደምትፈልግ ተናግረዋል፡፡-

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.