የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ የፊታችን አርብ በሼራተን አዲስ ሆቴል በይፋ ስራ ሊጀምር መሆኑ ተነገረ

Filed under: News Feature,የዕለቱ ዜናዎች |

የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ የፊታችን አርብ በሼራተን አዲስ ሆቴል በይፋ ስራ ሊጀምር መሆኑ ተነገረ፡፡ ተጠሪነቱ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆነው ይህ የፌደራል መስሪያ ቤት በዋና ዳይሬክተሯ ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት አማካኝነት ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በመግለጫው ኤጀንሲው በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የውጭ ዜጎች መብትና ጥቅም የማስጠበቅ ተልዕኮ እንዳለው የጠናገሩ ወ/ሮ ሰላማዊት በየትኛውም ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ያለምንም ልዩነት በሀገራቸው ጉዳይ በንቃት እንዲሳተፉ ማድረግ እንዳሰበ ተናግረዋል፡፡ በተጨማሪም ዲያስፖራውን የማስተባበርና የመምራት እንዲሁም የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በተቀላጠፈ መንገድ ለማድረስ ዝግጅታቸውን እንደጨረሱ ገልጸዋል። የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መሀመድ እንድሪስ በበኩላቸው ዲያስፖራውን ንቁ ተሳታፊ በማድረግ በሀገሩ ገብቶ መስራት የሚችልበትን እድል የማመቻቸት ተግባር ይከናወናል ብለዋል። በውጭ የሚኖረው ኢትዮጵያዊያና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ቁጥር በሚሊዮኖች የሚገመት ቢሆንም ኤጀንሲው በቅድሚያ ከሚያከናውናቸው ተግባራት መካከል ቁጥሩን በውል ማረጋገጥን ጨምሮ አጠቃላይ የዲያስፖራውን መረጃ ማሰባሰብ እንደሚሆን ተገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.