/

ምስክሮችን ፎቶ በማንሳት ተጠርጥረው የታሰሩት ዋስትና ተፈቀደላቸው

1 min read

የፌዴራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ዛሬ በዋለው ችሎት ፎቶ በማንሳት በማህበራዊ ድረ ገጽ ሲለጥፉ በቁጥጥር ስር ውለዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች የጠየቁትን የዋስትና ጥያቄ ተቀበለ።

መርማሪ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ወንጀል ፈጽመዋል ተብለው በምርመራ ላይ በሚገኙ ግለሰቦች ላይ ምስክርነት በመስጠት ፍርድ ቤት ቅድመ ምርመራ ላይ እያሉ፥ ፎቷቸውን በማንሳት በማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ በመለጠፍ መጠርጠራቸውን ተከትሎ ሲያደርግ የቆየውን ምርመራ ማጠናቀቁን እና የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ ማስረከቡን ለችሎቱ ገልጿል። ተጠርጣሪዎቹ በበኩላቸው ፍርድ ቤቱ ዋስትና እንዲፈቅድላቸው ባመለከቱት መሰረት በሁለት ሺ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ አዟል፡፡