/

ንግድን የማሳለጥ (Doing Business) መርሐ ግብር የአንድ ወር አፈጻጸም ግምገማ በጠ/ሚር ጽ/ቤት ሲካሄድ ውሏል

1 min read
1

ንግድን የማሳለጥ (Doing Business) መርሐ ግብር የአንድ ወር አፈጻጸም ግምገማ በጠ/ሚር ጽ/ቤት ሲካሄድ ውሏል::

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ መዋቅራዊ የሥራ አጥነት ችግርን ለመቅረፍ የግል ዘርፉ ንግድን ለመጀመርና ፋይናንስን በቀላሉ ለማግኘት እንዲችል ምቹ ሁኔታ የመፍጠርን አስፈላጊነት መናገራውን እንዲሁም በተለይም ጀማሪ ንግዶች ፋይናንስን በቀላሉ ለማግኘት ያሉባቸውን ማነቆዎች ከመፍታት አኳያ የብድር ሥርዓቱን በመከለስ ተንቀሳቃሽ ንብረትን በመያዣነት ለመበደር የሚያስችል አሠራር በሂደት ላይ መሆኑን ጠ/ሚሩ አስታውቀዋል ሲል ጽህፈት ቤታቸው አስታውቋል::

እንደ ጠቅላይ ሚኒስቱ ገልጻ ንግድን ለማሳለጥ ዐሥሩ መገለጫዎች:-

1. የንግድ ፈቃድ

2. የግንባታ ፈቃድ

3. ንብረትን ማስመዝገብ ሂደት

4. የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት

5. የብድር አቅርቦት

6. ግብር መክፈልና አከፋፈል

7. ዓለም አቀፍ ንግድ

8. ኪሣራና ዕዳን ማደራጀት

9. የአነስተኛ ባለ አክስዮኖች ጥበቃ

10. ውል ማስፈጸም ሲሆን  ጠ/ሚር ዐቢይ በዚህ ረገድ የቢሮክራሲ ማነቆዎችን ማስወገድ በኤሌክትሪክ ኃይል: በማዕድን: በቤት ግንባታ: በማኑፋክቸሪንግና በአነስተኛና ጥቃቅን አደረጃጀቶች የሥራ ቅልጥፍናን የበለጠ ለማሳለጥ እንደሚረዳ ማመልከታቸውን ጽህፈት ቤታቸው ያሰራጨው መረጃ ይጠቁማል::