ከአርበኞች ግንቦት 7 ዘመቻ ነፃ ትውልድ የተሰጠ መግለጫ

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

ቀን መጋቢት 10/2011ዓ/ም

እንደሚታወቀዉ ከሦስት ዓመታት በፊት ጎንደር ላይ በወልቃይት የማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላትን ከአርበኞች ግንቦት7 ጋር በማያያዝና የተጠለፈ የስልክ ልዉዉጥም ይዣለሁ በማለት ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ጎንደር ከተማ ላይ ኮረኔል ደመቀ ዘዉዱንና ሌሎች አባላትን ለማፈን በተደረገ ሕገወጥ ወያኔያዊ ዘመቻ ጀግናዉ ኮ/ር ደመቀ ዘዉዱ በወሰደዉ ቆራጥና የአልበገሬነት ዉሳኔ እጄን አልሰጥም በማለት ተላላኪ የአጋዚ ወታደሮችን ገድሎ ተጨማሪ ከመጡት ጋር እየተታኮሰ እንዳለ የሰማዉ የጎንደርና ዙሪያዉ ሕዝብ ፥ በየጎበዝ አለቃዉ እየተስባሰበና እየተጠራራ በቁጣ ከቦታዉ በመድረስ የአጋዚ ወታደሮችን ዙሪያዉን ከቦ እናልቃለን እንጂ ጀግናችን አናስወስድም በማለት በተፈጠረ ችግር ወያኔ ለግዜዉ አፈግፍጎ ኮረኔሉም በህግ ቁጥጥር ስር እንዲቆይ በተደረገ ባህላዊ ስምምነት በሁዋላ መደፈርን እንደሞት የቆጠረዉ ጀግናዉ የጎንደርና አካባቢዉ ሕዝብ በጎበዝ አለቆች እየተሰባሰበ በየቦታዉ በየጋራዉና ሽንተረሩ መሰባሰብ ቀጠለ።

ዉርደትን መሸነፍን የማይቀበለዉ ሕዝብ ለመጀመሪያ ግዜ ልቡ ሽፈተ፥ የጭቆና ገመዱን ለመበጠስ ቆርጦ ተነሳ፥ የወያኔ 5 ለአንድ አደረጃጀት ፈረሰ፥ አዉራ መንገዶች በሕዝብ ቁጥጥር ስር ወደቁ።

ይሄን በእልህ የተሰባሰበንና በገዛ ፈቃዱ ለነጻነቱ ለመታገል ቆርጦ የተነሳን ሕዝብ ግን ከጎኑ ሆኖ ስልታዊ በሆነና በተደራጄ መልኩ ሊያታግል የሚችል ድርጅት በወቅቱ እኔነኝ የሚል ባለመኖሩ በርካታ ድርጅቶች በስም ብቻ ቢፈጠሩም በተግባር አልተገኙም። ክዚህ ላይ ነዉ አታጋይ ድርጅት አስፈልጎ የነበረዉ በዚህ ግዜ ነበር ከሕዝቡም ከሜዲያም ጥሪዎች ይሰሙ የነበረዉ ግን በወቅቱ ከአርበኞች ግንቦት7 በቀር በተግባር የደረሰ ድርጅቶች አልነበሩም። ይህ ማለት ግን በወሬና በፌስ ቡክ የዚህ እንቅስቃሴ መሪዎች እኛ ነን፥ ይህ የጎበዝ አለቃ የሚመራዉ በኛ ነዉ፥ ለማለትና የባለቤትነት ሚና ለመጫወት የሞከሩ በተለይ ባካባቢዉ ስም ተደራጀን የሚሉ አልነበሩም ማለት አደለም።

ይሁን እንጂ አቅማቸዉ ዉስን በመሆኑና ከወሬ የዘለለ በግዜዉ ታጣቂዎችን አስተባብረዉ ሊያታግሉ የሚችል አቅም አልነበራቸዉም በዚህ ወቅት እኛ አርበኞች ግንቦት7 የጎደለዉን ለመሙላትና ይህ ብሶት የወለደዉ የትግል መነሳሳት እንዳይቀዘቅዝ ለማድረግ በየዞኑ የተሰለፉ የጎበዝ አለቆችን በመድረስ ትግሉን ከጎን ሁነን ማገዝ ጀመርን።

በጣም ፈታኝ ነበር ፈታኝነቱም

1፥ ለጦርነት የተሰለፈዉ ሕዝብ ዝግጅት ያልነበረዉና በተለይም ስንቅና ትጥቅ ያልተሟላለት በመሆኑ
2፥ በድንገት ከቤቱ የወጣ ስብስብ በመሆኑ
3፥ የጎበዝ አለቆቹ ባካባቢዉ ሕብረተሰቡና በወያኔ ካድሬዎች የሚታወቁ በመሆናቸዉ

4፥ የሽምቅ ዉጊያ ልምድ የሌላኣቸዉ በመሆኑ

5፥ የሚጠቀሙበት የመገናኛ ዘዴ ስልክ ብቻ በመሆኑ
6 ፥ በድርጅት የተደራጄ ባለመሆኑ
7፥ በጦርነት ግዜ እንደሁኔታዉ ማጥቃትና ማፈግፈግ ባለመቻሉ ከችግሮቹ ጥቂቶቹ ነበሩ ።

ከዚህ በመነሳት አግ7 ከነዚህ የጎበዝ አለቆች ጋር በመገናኘት መጀመሪያ ለወያኔ ተጠቂ እንዳይሆኑና ትግሉም እንዲቀጥል የሚያስፈልጉትን ጥንቃቄዎች ስንቅና ቆሳቁሶች በማቅረብ ትግሉእንዲቀጥል ማድረግ። ጎንለጎንም የሽምቅ ዉጊያስልትና የድርጅታችን ዓላማ ማስተማር ማሰልጠንና ማስታጠቅ ነበር።

በመሆኑም ስትራቴጂክ የሆኑ ቦታዎችን በመምረጥ ማሰልጠን ጅመርን ይህ የማሰልጠን ሥራ በጣም ፈታኝ የሆነ ነበር እሱም ወያኔ አርበኞች ግንቦት7 አገር ዉስጥ እግሩን ከተከለ በምንም አይነት ሊያጠፋዉ እንደማይችል ስለሚያዉቅ ያለ የሌለ ሀይሉን ተጠቅሞ ለማጥፋት ያደረገዉ ትንንቅ ነዉ።

ትንንቁ እንዴት ነበር ፥ የነጻነት ታጋዮች ከወያኔ ጋር ያደረጉት ተጋትሮ በተለያዩ የጎንደር አካባቢዎች የተደረጉ ጦርነቶች በስልትና በይዘት ተመሳሳይ ነበሩ እሱም ታጋዮች አሉ በሚባልበት ቦታ ሰራዊቱን በመላክ በሀይል ለመደምሰስ ጦርነት እየክፈቱብን ስለነበር ይህን የአፋኝ ጦር በየቦታዉ ያሉ የጎበዝ አለቆች ጓዶቻቸዉን በማስተባበር መግጠምና መመከት አማራጭ የሌለዉ ግዴታ በመሆኑ በርካታ ጦርነቶች ተካሂደዋል። በተለይ በሰሜን ጎንደር እንቃሽ በሳንጃ፥ ወገራ ሲላሬ ከተማን በመያዝና እስረኞችን በማስፈታት፥ ቋራ ፥ ደንቢያና ሊቦ ከምከም የተካሄዱት ጦርነቶች ወያኔ ተዋርዶ የተመለሰባቸዉና በርካታ ሰራዊት የተደመሰሰበት የጦር ቀጠናዎች ነበሩ እኛም በነዚህ የጦር ቀጠናዎች በመገኘት ለነጻነት ታጋዮች ስንቅና አላቂ ነገሮችን በማቅረብ መረጃ በማሰባሰብ እና የጦርነት እቅዶችን በማዉጣትና በማሰማራት የተቀኛጀ የማጥቃት ዘመቻዎችን አድርገናል።

በሌላ በኩል ትግሉን በማዘመን በርካታ ምሁራን የተካፈሉበት (ረመጥ) በሚል የተቋቋመ የደህንነት መረብ (counter-intelligence network) በመዘርጋት ትግሉ እንዲቀጥልና እንዲጎለብት በማድረግ የማይናቅ ሥራ ሰርተናል። ካጦርነቱም እንደተረዳነዉ ትግሉን ለማጎልበትና ለማስቀጠል የሚያስፈልገዉ
1፥ ታጋዮችን በአዲስ ማደራጀት
2፥ ማሰልጠን
3፥ ማስታጠቅ እንዳለብን በመረዳት መጀመሪያ በቋራ ቀጥሎም በደንቢያና ወገራ ወጣቶችን በማሰልጠን በማስታጠቅ ማደራጀትና ለረጅም የትግል ዝግጅት ማድረግ በመሆኑ አዲስና ስልታዊ አደረጃጀት በመፍጠር ለዘመናዊ የሽምቅ ዉጊያ የሚመጥን ዝግጅት አደረግን።በዚህም መሰረት

1የወታደራዊ እና የፖለቲካ ስልጠና መምሪያ

2- የወታደራዊ ሎጅስቲክ መምሪያ

3፥ የወታደራዊ ደህንነት መምሪያ

4፥ የዘመቻ መምሪያ

5፥ የሕዝባዊ እንቢተኝነት መምሪያ

በሚል አዋቅረን ትግሉን ወደ ጠላት ቀጠና በማስገባት በመንግሥት የሰራዊትና የአመራር መዋቅሮች ሰርገን በመግባት ጠላትን በማጥናትና ብሎም ስስ ብልቱን በማወቅ በአክራሪ ወያኔ አፍቃሪ ካድሬዎች ላይ የማያዳግም የቅጣት እርምጃ በመዉሰድ ዋና ዋና መንገዶችን በመዝጋት ከሱዳን ወደ አገር የሚገባዉን የነዳጅ መስመር በተደጋጋሚ በማቃጠል መስመሩን በመቁረጥ ለጠላት የጉሮሮ አጥንት በመሆናችን አገሪቱን ተደላድሎ የማስተዳደርና መቆጣጠር ባለመቻሉ የግዜያዊ ወታደራዊ አዋጅ (state of emergency) በማወጅ ጦርነቱን ቢቀጥልም በእልህ የተነሳዉን አመጽ ማክሽፍ አልቻለም ነበር። ይልቁንም ይሄን የታወጀ ግዜያዊ አዋጅ በመጣስ ሕዝብን በማሳድም መንገዶችን በተደጋጋሚ በመዝጋት ወታደራዊ ካምፖችን በማጥቃት የተጠናከረ የሽምቅ ዉጊያ አካሂደናል።

በመሆኑም።

ዘመቻ ነጻ ትዉልድ

የትጥቅ ትግሉን በአማራጭነት የተቀበለው አገሪቱን እየገዛ ያለው ዘረኛው የህወሓት ቡድን ሁሉን የዴሞክራሲ አማራጮች ዘግቶ በመያዝ በሕዝባችን ላይ ከፍተኛ በደሎቹን ቢፈፀሙ ይህን ለማስቆም አግ7 አታጋይ ድርጅታችን ነው በማለት በቡዙ ሽህ የሚቆጠሩ የአገሪቱ ልጆች ወደ ድርጅቱ በመቀላቀል ከሒይወት አስከ አካል መጎደል ድረስ መስዋዕትነት ከፍለዋል ። በዚህም የትንንቅ ትግልም ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ጀግኖቻችን አጥተናል በርካቶች ተጎድተዋል ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።

አገርውስጥ ያለው የአግ7 አርበኞች ከከተማና ግጠር ካሉ ሀይሎ ጋር በመናበም ባደረጉት የተቀናጄ ትግል በስርዓቱ ላይ የማይናቅ ተፅእኖ ምክንያት ህወሓት ከእንዴ ሁለት ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማወጅ ትግላችን ለመደምሰስ ተንቀሳቅሷል ።

አግ7 ደግሞ አዋጁ ስራ ላይ እንዳይውል የትግል ስልት በመቀያየር ባደረገው ተጋድሎ ስርዓቱን አንበርክኮ፥ ወደ ሊላ አማራጭ እንዲገባና ተገዶም ያሰራቸውን ዜጎች መፍታት ችላል ፡፡
አግ7 ዘመቻ ነጻ ትዉልድ፥ ከትጥቅ ትግሉ ጎን ለጎን የሰራው የማደራጀትና የቅስቀሳ ሥራም አድማሱን አስፍቶ በተለይም በዩንቨርሲቲና በመንግሥት ተቋማት ዉስጥ የድርጅቱን መረብ በመዘርጋት ቀላል በማይባል ሥራ ሠርቷል

ስርዓቱን በኢኮኖሚ እና በፖለቲካውም ኢህአዴግ በየስብሰባዉ እርስ በርስ የማይስማማበት አንዱ አንዱን ከመጠራጠር ደረጃ እንዲደርስ አድርጎታል ። በተለይም በብአዴን እና ኦህዴድ ውስጥ የተሰራው የፖለቲካ ስራ ቀላል እንዳልሆነ ይታወቃል ።

በስርዓቱ ውስጥ በተለይም በደህንነት እና በመከላከያ ውስጥ በተሰራው የስርገት ሥራም ጠቃሚ ውጤት እንደተገኘ ይታወቃል ። አሁንም እነዚህ ኃይሎች መሰረታዊ ለውጥ በአገሪቱ እንዲመጣ እየታገሉ ይገኛሉ ፡፡ ይህ ሁሉ ውጤት ሲመዘገብና አሁን ከአለንበት ደረጃ ለመድረስ በርካታ ድካም ተደክሟል ከፍተኛ ገንዘብም ወጥቷል ።

ሕዝባዊ እንቢተኝነቱም እንደዚሁ በጠንካራ አደረጃጀት ላይ ይገኛል። ለዚህም ነው አድማዎችን ፡ በተለያዩ አጋጣሚዎች በኳስ ፡ በባዓላት ፡ እንዲሁም በተገኘው አጋጣሚ ስርዓቱን ታግለውታል እየታገሉትም ይገኛል በስርዓቱ ታስረው የነበሩ ሰዎቻችን ሲፈቱ ከአቀባበል እስከ አቅም የፈቀደዉን ግዜያዊ ድጋፍ በማድረግ በኩል ያቅማችን በርካታ ስራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ። ታጋዮቻችን የሰነቁት የመጨረሻው ግብ እውን እንዲሆን እየሰሩ እና እየታገሉ ይገኛሉ ።

በመሆኑም ይህን ከፍተኛ መስዋእትነት ተከፍሎ የተገኘዉን ድል ስንቀበል በሳለፍነዉ መራራና እልህ እስጨራሽ ትግል በህይወትና በእስራት ዋጋ የከፈሉ አርበኞቻችን ሳንረሳ መሆን ይኖርበታል። በኛ የትግል ማህደር ለግዜዉ የመዘገብናቸዉ።
-176 ታጋዮች ስዉተናል -በመቶዎች የሚቆጠሩ አካለ ስንኩል ሆነዋል።
-በብዙ ሽዎች የሚቆጠሩ ለአሰቃቂ እስር ተዳርገዋል።
-በመቶዎች የሚቆጠሩ የአርበኛ ቤተሰቦችና ከነሱ ጋር ዝምድናና ግንኙነት አላቸዉ የተባሉ ቤተሰቦች እየተፈለጉ ቤታቸዉ ተቃጥሏል ማሳቸዉ ወድሟል፥ የቤት እንሰሶቻቸዉ እየታረዱ ለአጋዚ ወታደር ስንቅ ሆኗል።

-ልጆቻቸዉ ከትምህርት ቤት ተባረዉ ከተፈናቃይ ወላጆቻቸዉ ጋር ያገር ዉስጥ ስደተኞች ሁነዋል ፡፡

በመሆኑም አግ7 ከኢትዮጵያ መንግሰት ጋር በደረሰው ስምምነት መሰረት ነሀሴ 3 ቀን 2010 ዓ/ም የአግ7 ዘመቻ ነፃ ትውልድ ሁለት አባላት ወደ አማራ ክልል ተልከን ከክልሉ ጋር በአደረግነው ስምምነት ከኤርትራ የነበሩ አርበኞች እንዲገቡና በአገር ውስጥ የሚገኙ አርበኞችም ወደ ካምፕ እንዲገቡ ተነጋግረን ይህ ጉዳይ ተፈፅማል ፡ በተለይ ከዚህ ላይ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እና ክልሉን እየመራ የሚገኘው ፓርቲ አዴፓ ላደረጉልን ትብብር እጅግ እናመሰግናለን ፡፡ በዚህ ላይ አግ7 ከመንግስት ጋር በደረሰው ስምምነት መሰረት የመልሶ ማቋቋሙ ጉዳይ እንዲፋጠን በተደጋጋሚ ጥያቄዎችን አቅርበን በእኛ በኩል በመጀመሪያ የ5185 (አምስት ሽህ አንድ መቶ ሰማንያ አምስት )የአርበኞች ዝርዝር ልከናል በቀጣይ አፋጣኝ ጉዳያቸው የሚታይላቸው ተብሎ የ1091(አንድ ሽህ ዘጠና አንድ) አርበኞችን ዘርዝረን በጠቅላይ ሚኔስተር ለመልሶ ማቋቋም ጽ/ቤት ልከናል ፡፡ ሁኖም ግን ጠብቁ ከማለት ያለፈ የተደረገ ነገር ባለመኖሩ አብዛኛዎቹ አርበኞች ለችግር ተዳርገዋል ፡፡ ይህ አርበኛ ኃላፊነት የሚሰማውና በጥብቅ ዲስፔሊን የታነፀ በመሆኑ እንጅ ልክ እንዳአንዳንድ ድርጅቶች ኃይልን መጠቀም እጅግ ቀላል ነው ፡፡ መንግስትም ይህን ትዕግስት ተመልክቶ አፋጣኝ መፍትሔ መስጠት ሲገባው ጉዳዩን በቸልታ መመልከቱ ተገቢ አይደለም እንላለን ፡፡፡ ስለሆነም ፡ በቀጣይ ከኤርትራ የመጡ የትግል ጓዶቻችን እና ወንድሞቻችን ጨምሮ በአገር ውስጥ የሚገኙ አርበኞችን በፍጥነት የመልሶ ማቋቋሙ ስራ እንዲሰራ እየጠየቅን ፡ በቀጣይ አሁን አገራችን ብሎም ለጊዜው ቢሆንም ችግራችንን በመጋራት ድጋፍ እያደረገልን የሚገኘውን የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ በመገምገም ወደ ፊት ምን ማድረግ ይኖርብናል ? የሚለውን ከአባሎቻችን ጋር ተወያይተን መግለጫ እናወጣለን ፡፡
” አርበኝነት ያለ አርበኞቹ ከንቱ ጨዋታ ነው”

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.