የአርበኞች ግንቦት 7 የባሕር ዳር ውይይት ለሌላ ጊዜ ተራዘመ

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

 

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 15/2011ዓ.ም (አብመድ) አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ በባሕር ዳር ከተማ ክልል ምክር ቤት አዳራሽ በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታና ከሕዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የጠራው ሕዝባዊ ውይይት ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡

ወጣቶች ‹‹ግንቦት ሰባት የአማራ ጠላት ነው›› በማለት ውይይት በተጠራበት አዳራሽ አካባቢ ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡

ንቅናቄው ለአዳራሽ ውይይቱ ተሳታፊዎችን በማስታወቂያና በመግቢያ ወረቀት መጋበዙን የውይይት ኮሚቴው አባል አቶ ዓለሙ ፈጠነ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ነገር ግን ወጣቶች ወደ አዳራሽ በመግባት የሰቀልናቸውን ጽሑፎች አውርደውብናል፣ የራሳቸውን ጽሑፍ በመስቀልም አውከውናል›› ብለዋል አቶ ዓለሙ፡፡

ተቃውሞ ያቀረቡት ወጣቶች በበኩላቸው ‹‹ግንቦት 7 የአማራን ብሔርተኝት የሚያዳክም፣ በኢትዮጵያዊነት ስም አማራን እንዳይደራጅ የሚያሴር፣ ሀገሪቱ በብሔር ፖለቲካ መወጠሯን እያወቀ አማራ ብቻ ስለኢትዮጵያ እንዲያቀነቅን የሚወተውት ፀረ-አማራ ነው›› ብለዋል፡፡

ንቅናቄው ለሚፈልጋቸው ግለሰቦች ብቻ ወደ ስብሰባው መግቢያ ወረቀት አዘጋጅቶ ህዝብ ላወያይ ብሎ ማሰብ ተገቢነት የለውም ነው ያሉት ወጣቶቹ።

የግንቦት 7 ከፍተኛ አመራሮች በክልል ምክር ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ አባሎቻቸውን ሰብስበው ውይይቱን ማካሄድ እንዳልቻሉና ስብሰባው ወደ ቀጣይ ጊዜ አንደተራዘመ ተናግረዋል ።

የንቅናቄው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በስልክ ባስተላለፉት መልዕክትም ስብሰባው ለሌላ ጊዜ መራዘሙንና ተፎካካሪ ፖርቲዎች የተስማሙበትን የጋራ የቃል ኪዳን ሰነድ መሰረት በማድረግ ቀጣይ ስራዎችን አንደሚሰሩ ተናግረዋል።

ንቅናቄው በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታዎች እና ከህዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ከባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ለመምከር አስቦ እንደነበር የባህርዳር ከተማ የአርበኞች ግንቦት 7 ፀሀፊ አቶ መንግስቱ አማረ ለአብመድ ተናግረዋል ።

ዘጋቢ፡- ኃይሉ ማሞ

 

5 Responses to የአርበኞች ግንቦት 7 የባሕር ዳር ውይይት ለሌላ ጊዜ ተራዘመ

 1. የአርበኞች ግንቦት 7 ድርጅት አገርቤት ከገባ በኋላ ብዙ ወርቃማ እድሎች አባክኗል ። ምክቱም ሕዝባችን 27 ዓመት ሙሉ
  በሕወሀት የጎጥ ፖሌቲካ ቁም ስቅሉን ያዬ በመሆኑና ሁሉም ነገር በጎጥ ተቃኝቶ አንድነቱን የጎዳው ስለሆነ ከዚያ የሚያላቅቀው የተደራጀና ጠንካራ ሕዝባዊ መሰረት ያለው የተደራጀ ሃይል የሚፈልግበት ወቅት ነው ። ታዲያ በዚህ ወቅት አገር ውስጥ ያሉም ሆነ ከውጭ ተቻኩለው የገቡ ጎጠኛ ድርጅቶች ያለ የሌለ ሀይላቸውን አስተባብረው የመንግሥትንም መዋቅር ጭምር ተጠቅመው ኦሮሞ ያልሆነውን ኢትዮጵያዊ ሲያፈናቅሉ ሌሎች የብሔር ድርጅቶች ሳይቀሩ ቢያንስ መግለጫ ሲያወጡ ግንቦት 7 ብቻል ቦታው ድረስ በመሄድ በማነጋገር የችግሩ ተጋሪ መሆን በተገባው ነበር ካልሆነ ድርጊቱን ማውገዝ ያባት ነው ። ዝምታው መስማማት ላለመሆኑ ምን ማረጋገጫ አለን ? ማንም ቢሆን የአህያ ባል እንዲኖረው አይፈልግም ። ግንቦት 7 በዚሁ ከቀጠለ ተአማንነቱን ይበልጥ ያጣል ። የፖሌቲካ አቋሙን በተመለከት መሽኮርመምና ግለሰብን ላለማስቀየም በመሞከር ደጋፊ ሊያገኝ አይችልም ።

  Avatar for Zegeyedelu

  Zegeyedelu
  March 25, 2019 at 5:23 am
  Reply

  • The issue is not about G7 program or political stance. It is about the rule of law – No one has the legal right to disrupt the meeting of others. It is anti-democratic!
   If it were Kerro who did this in Adama or Chiro, I am sure you would be the first person to paint it ethnic color!

   Avatar for Kedir Setete

   Kedir Setete
   March 26, 2019 at 8:59 am
   Reply

 2. ኣብኖች !
  ግንቦት 7 በጠራው ስብሰባ ስለተነሳው ውዝግብ የናተን መግለጫ/ኣቁዋም በናፍቆት እየጠበኩ ነው።ዝም ልትሉ ከቶ ኣይገባች ሁም !
  በቅርቡ በደሴ የተፈጸመውን እናስታውሳለን።
  Thanks

  Avatar for Zega

  Zega
  March 25, 2019 at 8:17 am
  Reply

 3. ግንቦት 7 አካሄዱን በደንብ ሊፈትሽና ሊገመግም ይገባል፡፡

  በየክልሉ ያሉ አባላቶቹ የቅድመ መረጃ አሰባሰብና አፍራሽ ሃይል ቢኖር እንዴት መቋቋም እንደሚችሉ ቅድመ ስራ ማከናወን ይኖርበቸዋል፡፡ አንድ ኢትዮጵያዊ ደም ያለውና ቀጣይ የገሪቷን ህልውና ሊያስቀጥል ይችላል ብሎ ህዝብ ተስፋ የጣለበት ድርጅት መፍረክረክ የለበትም፡፡ እንደ ሙሁር ድርጅት Strategy & plan በደንብ በመቅረፅ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል፡፡

  ወደደም ተጠላ ወጣቱ በትንሽ ነገር እየተሸወደ የአገሪቷን መፂህ ተስፋ ባለማጨለም በብልጠት ሊጓዝ ይገባል፡፡

  ኢትዮጵያዊ ለዘላለም ትኑር!!

  Avatar for Yetesfa Chilanchele

  Yetesfa Chilanchele
  March 26, 2019 at 7:58 am
  Reply

 4. The game is over no more patriotic Ginbot 7. The stolen title patriotic must be returned to the appropriate for fathers who kept our country from Italian invaders before half-century. If you like may you continue with only Ginbot 7 or discrete it and go to your noble profession. It is up to you( highly respected prof.).

  Regards,

  Avatar for biru belachwew

  biru belachwew
  April 1, 2019 at 6:51 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.