የሃገር መከላከያው ሴክተር ላይ ተደረገ የተባለው “ሪፎርም” – ወንድይራድ ሀይለገብርኤል

1 min read

በግልፅ እንዳየነው ጠቅላይ ሚንስትር አብይ በአዴፓ ትከሻ ላይ ተፈናጥጠው ስልጣን በተቆናጠጡ ማግስት በቶሎ ተቻኩለው ግዜ ሳይሰጡ የመጀመሪያውን የፖለቲካ ሸፍጥ የተገበሩት የሃገር መከላከያ ሰራዊቱን “ትግራዊ የነበረውን መከላከያ ኢትዮጵያዊ ቅርፅና ይዘት መስጠት” በሚል መሪ ቃል የሰራዊቱን ከፍተኛና ቁልፍ የዕዝ ወንበሮች ከህወሐት ነጥቆ የኦዴፓ/ኦነግ በማድረግ ነው። ይህንን በማድረጋቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ ያልሆነ የኦሮሞ መከላከያ ሀይል በተሳካ ሁኔታ መፍጠር ችለዋል።
===

ሸፍጡን በስኬት አጠናቀውታል። የተደረገው ሪፎርም ሳይሆን “ከህወሐት ወደ ኦዴፓ/ኦነግ” ስልታዊ ርክክብ ነው። የርክክብ ሰነዱ የመጀመሪያ ድራፍት በነህዝቃዔል ጋቢሳና ጀዋር መሀመድ ተዘጋጅቶ ለኦዴፓ እንደቀረበ መረጃዎች አሉ። አረካካቢው ጄኔራልም ሰዐረ መኮንን ናቸው። በቆራጭ ፈላጭነት ስልጣኑን የተረከቡትም የሻዕቢያው ምርኮኛ የደርጉ ም/አስር አለቃ የኦዴፓው ጄኔራል ብርሀኑ ጁላ ናቸው። ሰዐረ በግማሽ የአማራነት ደሙ በህወሐት ተገፍቶ የመኖሩን ቁጭት መከላከያውን ከህወሐት ወደ ኦዴፓ/ኦነግ የባለይዞታ ማረጋገጫነት ርክክብን በታማኝነት አጠናቛል። አለቀ።
===

አዴፓ እንደአርባ ሚሊዮን ህዝብ ተወካይነቱ ኮንሲደር ሳይደረግ በዶር አብይ አህመድ ትልቁ ክህደት “ሀ” ብሎ የተፈፀመበት እዚህ ላይ ነው።
===

መፍትሄ —
——-

መከላከያ ሴክተሩ ውስጥ ተደረገ የተባለው ሪፎርም ፍትሃዊ በሆነ መንገድ እንደገና እንዲታይ አዴፓ ዜሬ በሚጀመረው የኢህአዴግ ምክርቤት ስብሰባ አጀንዳ አሲዞ ችግሩን ቢያስመረምር መልካም ነው። ተደረገ የተባለው ሪፎርም በየትኛውም መለኪያ ተቀባይነት የለውም።
===

ለምሳሌ ያክል ሰሞኑን በከሚሴና አካባቢዋ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የመከላከያውን ሃይል በግልፅ ለአንድወገን ሳይፈራና ሳያፍር ድጋፍ ማሳየት ብቻ ሳይሆን የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትን የፀጥታ ተቋም እስከማውገዝ ድረስ መድረሱ የሃገር መከላከያ ሀይሉ የማንን “ልዩ ጥቅም” ለማስጠበቅ ታስቦ “ሪፎርም” እንደተደረገ ገላጭ ነው።
======

ቆማጣን ያየ በቆራጣ አይቀልድም እንዲሉ!!!
————- ———– ————- ———-

ሌላም አለ!!!!!
————-

*** የመከላከያንና የገቢዎች ሚንስቴር መስሬያቤትን ያየ በውጭ ጉዳይ የሚንስቴር መስሪያቤት አይቀልድምና ትኩረት ወደውጭ ጉዳይ የሚንስቴር መስሪያቤቱ በአስቸዃይ እንዲደረግ ለመጠቆም እንወዳለን።
===

እንደተባለው ቦታው ለአዴፓ ተሰጥቶ ከሆነ የኦዴፓ/ኦነግ መስሪያቤቱን ማመስ ለምን አስፈለገ? አቶ ለማ መገርሳ የኦቢኤን ስራአስኪያጅ የነበረውን ግለሰብ ጨምሮ ቁጥራቸው ከሀያ በላይ ለሆኑ በኦ/ብ /ክ /መ ውስጥ በተለያዩ ሀላፊነቶች ተመድበው ሲያገለግሉ የነበሩ ግለሰቦችን በጅምላ ወደውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መስሪያቤት ሊልዃቸው እንደሆነ መረጃ ደርሶናል። አዴፓ ፍተሻ ቢያደርግ መልካም ነው።
===

የምንታገለው ወርድና ቁመታችንን ለሚመጥን ፍህታዊ የስልጣን ክፍፍል መሆኑን መዘንጋት ዋጋ ያስከፍለናል።

ይታሰብበት ለማለት ነው!!!

2 Comments

  1. እጅግ በጣም ጥሩ ማሳስውቢያ ነው ፡

    የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሌላ መሰጠት የለበትም፤ አዴፓ አማራ ክልል መሆን አለበት፤

    መይሳው

    • አቶ ሃይለገብርኤል አያሌው፤ ቴዎድሮስ፤ ዛሬ ደግሞ ወንድይራድ ሄደህ ሄደህ እዛው ጎጥህ ውስጥ ይህንን ቦታማ አማራ ሊይዘው ይገባል ትላለህ? ደግሞ ከዚህ ሁሉ ጊዜ በኋላ እዛው የዘር ጉድጓድህ ትቀረቀራለህ? ዝም ማለት እኮ ዋጋ አለው። ቢያንስ ለሃያ አመት ያህል ፖለቲካው ውስጥ ዱብ ዱብ ብለህ እዛው መአህድ ውስጥ ትቀረቀራለህ ብዬ ለአንድም ቀን አስቤ አላውቅም ነበረ። ወይ ነዶ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.