ጂጂን ፍቱልን! የገብረክርስቶስ ደስታ ይበቃናል፤ (መስቀሉ አየለ)

1 min read

የሰው መዓዛ ከሩቅ በሚጣራባት ብቸና የበቀለች ጂጂ ሰውነት ትርጉም ባጣበት፣ ግለኝነት በገነነበትና አፍቅሮ ንዋይ ግን ቤተመንግስቱን በገነባበት በኒውዮርክ ከተማ ውስጥ ባይተዋር ሆና መኖሯ ስለምንድን ነው?

ድሮ ድሮ ያኔ አሜሪካ የማርስን ያህል እሩቅ በነበረችበት በስልሳዎቹ ዓም ነፍሱን ለኪነጥበብ የሰጠውና በብሩሹም በደማሙ ብእሩም የነፍሱን እውነት አውጥቶ የማሳየት አቅም የነበረው የኢትዮጵያው ልዩ አፈር ረቂቁ ገብረክርስቶስ ደስታን ያጣነው በዚሁ በኒውዮርክ ከተማ ነበር። ከሞቱ በላይ አሟሟቱ ልብን የሚሰብረው ይኽ ሰው እንዴት እንደወጣና እንደተራ ሰው በዚያው እንደቀረ ነፍሱን በጽርሃ ጽዮን ያሳርፍልንና ስለርሱ አንዲት መጠነኛ ፍንጭ ከሰጠው ከፈላስፋው ሰሎሞን ደሬሳ በስተቀር የተናገረ የለም። ያን ግዜ ኢንተርኔት አልነበረም። ዓለም እንዲህ እንደዛሬው አንድ መንደር አልሆነችም። “መረጃ በብርሃን ፍጥነት ይፈሳል” የሚለው እሳቤ ያን ግዜ ሳይንስ ፊክሽን እንጅ እንደዛሬው በእጃችን የጨበጥነው ሳይንሳዊ ሃቅ አልነበረምና የጥበበኛው የህይወት ፍጻሜ ለቅርብ ቤተሰቡና ጓደኞቹ ሳይቅር ሚስጥረ ስላሴ ሆኖ ቢቀር አይገርመንም ይሆናል።

ትናንት ግን ዛሬ አይደለምና አለም በመረጃ ቴክኖሎጅ ድርና ማግ በሆነችበት በዚህ ዘመን የጂጂ ነገር እንዲህ እንደዋዛ ከሰው ተሰውሮ ይቀራል ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው።

ጋሸ ሶሎሞን በጣም ከሚቆጨው ነገር ስለ ሰአሊና ገጣሚ ጏደኛው የገብረ ክርስቶስ ደስታን አሟሟት በቁጭት ሲናገር እንዴት እንደገለጠው ካነበብኩት በደምሳሳው እንዲህ አስታውሳለሁ ። “እኔ ፈረንሳይ እያለሁ ገብረክርስቶስ ደስታ የከፈተው የስእል ኤግዚቢዥን ለማየት ወደ ጀርመን ሄድኩኝ። እንደተመለስኩም አንድ ጏደኛየ ጥቁር አሜሪካዊት ቢያገባ ሚዜ ለመሆን ወደ አሜሪካን አቀናሁ፤ ከዛያም ቦሃላ ወደ አውሮፓ አልተመለስኩም። ገብረክርስቶስ ግን እንዴትና መቸ ወደ አሜሪካ እንደመጣ ሳልሰማ ብቻ እርሱን ያህል የጥበብ ፈርጥ ማንም በማያውቀው አገር፣ ባይተዋር ሆኖ እንደ ተራ ሰው ባዶ ቤት ሞተና በጎረቤት ጥቆማ በከተማው ማዘጋጃ ቤት ተቀበረ አሉ።በባዶ ቤት ውስጥ ሆኖ ብቻውን የተጋፈጠውን መራራ ሰአት ማሰቡን ሆድ አይችለውም። እኔ ይህን ነገር ባስታወስኩት ቁጥር ያመኛል።በእርግጥ መታመሙን ሰምቸ ቢሆን ኖሮ እንኳን ከመለዓክ ሞት ብርቱ ክንድ የምታደግበት ባይኖረኝም ቅሉ ቢያንስ ሲሞት የሚያውቀው ሰው ፊት እያየ እንዲሞት በጸአተ ነፍሱ የመጨረሻዋ ሰዓት ከፊቱ እቆምለት ነበረ..” ማለቱ ይጠቀሳል።

ምን ለማለት ነው፤ የኪነጥበብ ሰው ነፍሱ ቅርብ ናት። መንፈሱ ድንበር አልቦ ነው። ከሌላው ለየት የሚያደርገውም ይኼው ነው። እንዲህ ዓይነትን ሰው ድንቅ በሆነ ተፈጥሯዊ ጸጋው የሌላውን መንፈስ ለመጠገን የተሰጠውን ያህል በዚያ ልክ ደግሞ እራሱ ሲሰበር ህማሙ ከማንም በላይ ጠልቆ የሚሰማው ለዚያ ነው። እኛም ዛሬ በጅጅ ጉዳይ ዝም የማንለውም ይኼን ደረቅ ሃቅ በአንክሮ ስለምንረዳ ነው። በዚያ ላይ ኒውዪርክን አንወደውም። ከዚያ ከተማ ጋር የተቆራኘው የገብረክርስቶስ ደስታ ፍጻሜ ለኛ ከመቃብር ድንጋይ የከበደ ነውና ይኽችን እንቁ ከዚያ ሶዶማዊ ከተማ፣ ከዚያ ከምድረ ባርባሮስ፣ ከዚያ በብቸኝነት ተዘግታ ከምትኖርበት ጠባብ ክፍል ውስጥ አውጡልን። ከሚወዳት ህዝብም ጋር ትቀላቀል።በዚህም ባህር ለሆነ መንፈሷ በአድማሳትና ቀላያት የማይገደብ ሰፊ በጣም ሰፊ ግዛት አለ። በእናት አገር ምድሯ ላይ የነፍሷ ቁስል ይታከማልና።

ትኩረት ለጅጅ ሽባባው!
ፍትሕ ለኤርሚያስ አመልጋ!

4 Comments

 1. In today’s Ethiopia when Ethiopian people are not nice to each other with 4 millions in Ethiopia displaced by their own very close neighbors, being able to have your own residence in a sanctuary city of New York with no nagging defaming roommate/neighbor is a blessing.

  The life Mr. Gebrekristos Desta lived in New York until his very last breath is a dream of almost all single persons of Ethiopia.
  New York is still a dream destination for SF habeshas that want to live away from the back stabing Ill willed evil habesha frenemies that bother attack any chance they got regularly.

  After 50+ years later Artist Gebrekristos Desta’s death, locking your door , dieing peacefully at your home is considered to be a dream come true for the vast majority of Ethiopians.That is why I say Let Gigi live the lifestyle that most Ethiopians only long for to have one day.

  To Gigi
  Live your life the way you choose to, DONOT let anyone tell you your small room is not enough for you. Atleast you donot have to go room to room every minute checking if burglars are in, like those living in mansions do.Many will follow you the move out of SF to NY soon too. SF bay area habesha is mostly too scandalous that are always in competition amongst each other , they invite you for lunch to their homes and when you take a bite they talk about you as a starved bigger they are feeding.

  Texas is another place filled with people who left SF bay area just like you did.
  Sincerely, Almaz

 2. In today’s Ethiopia when Ethiopian people are not nice to each other with 4 millions in Ethiopia displaced by their own very close neighbors, being able to have your own residence in a sanctuary city of New York with no nagging defaming roommate/neighbor is a blessing.

  The life Mr. Gebrekristos Desta lived in New York until his very last breath is a dream of almost all single persons of Ethiopia.
  New York is still a dream destination for SF habeshas that want to live away from the back stabing Ill willed evil habesha frenemies that bother attack any chance they got regularly.

  After 50+ years later Artist Gebrekristos Desta’s death, locking your door , dieing peacefully at your home is considered to be a dream come true for the vast majority of Ethiopians.That is why I say Let Gigi live the lifestyle that most Ethiopians only long for to have one day.

  To Gigi
  Live your life the way you choose to, DONOT let anyone tell you your small room is not enough for you. Atleast you donot have to go room to room every minute checking if burglars are in, like those living in mansions do.Many will follow you the move out of SF to NY soon too. SF bay area habesha is mostly too scandalous that are always in competition amongst each other ,one good example that happened to many just this past Easter day was the ones with big residences invited people for lunch to their homes and when the invitees went take a bite they turn around and tell their families that you are an uninvited guest buster starved begger they fed.You are better off where you are.

  Texas is another place filled with people who left SF bay area just like you did.

  Sincerely, Almaz

  https://www.zehabesha.com/amharic/archives/95020

 3. በሃገራችን የኪነጥበብና የጽሁፍ ታሪክ ውስጥ ብዙዎች ሃገሬን ወገኔን በማለት በሰላምና በጤና ከሚኖሩበት የቅርብና የሩቅ ዋሻ ወጥተው የእሳት ራት ሆነዋል። ከእነዚህም መካከል እውቁ አቤ ጉበኛ ይገኝበታል። ከዘመናት በፊት በዚሁ ደራሲ የተጻፈውን “አልወለድም” መጽሃፍ ዛሬ ላይ ሆኖ ላነበበ የሃገራችን ህዝብ ህይወትና ፓለቲካ ቅንጣት ያህል ለውጥ እንደሌለው ያሳያል። በዓሉ ግርማ በኦሮማይ እንደሚለን “በውንብድና ዓለም ውስጥ መተማመን የለም”። ህይወቱን የቀጠፉት ወስላቶች ዛሬም ቆመው ሲሄድ ማየት ህይወትን መራራ ያደርጋታል። ብዙም ሳይርቅ ደግሞ ጋዜጠኛ ዳን ኤል ገዛኸኝ “ሲዋን” በሚለው መጽሃፉ የህዝባችንን የስደት ሰቆቃ ከሃገር ቤት እስከ ሶማሊያው ወደብ ቦሳሶ ከዚያም በየመን የሆነውን ግፍና መከራ ይተርካል። ታዲያማ ዛሬ ጂጂ የሚሉ ሁሉ አብሮ መኖርን ለምደው በዘርና በጎሳ ባይሰለፉ ምን አልባት እሷም ካለችበት የከተማ ዋሻ ራሷን ብቅ ለማድረግ ይመቻት ነበር። ለዘረኞችና ለከፋፋዮች ሞት። የህዝባችንን ሃበሳ ለራሳቸው መኖር ሲሉ ለሚያራዝሙ መከራና ሃበሳ አይለያቸው። አይ ሃገሬ …ጣሊያንን ያሸነፈ ትውልድ እንዳልነበረሽ በሃገር ቤት ጣሊያኖች ትፈራርሺ። መቼ ይሆን የሰቆቃሽ ማቆሚያ!የሚከተለው ግጥም ለጂጂ ሽባባው ይሁንልኝ።

  ከሰው ሁሉ ርቄ ሁሉን ረስቼ፤ ሃገሬን ወገኔን ደህና ሁኑ ብዬ
  ጫካ ገብቻለሁ ልኖር ካውሬዎች ጋር ያገኙትን በልተው ተመስገን ከሚሉ
  ለእየለት ጉርሻቸው ተግተው ከሚሰሩ ለነገ በማለት ከማያካብቱ
  ሰውን በስራቸው እጅጉን ካስናቁ ከአናብስቱ ጋራ መኖር ጀምሬአለሁ
  እርም ብዬ ሰውን እንስሳ ሆኛለሁ።
  ተከብቤ እያለሁ በህንጻዎች መሃል አይኖቼን ጨፍኜ ማንንም ላልሰማ ጫካ ነኝ ብያለሁ።
  አትረብሹኝ ተውኝ ህመም የለብኝም፤ እርዳታም አልሻ የምሰጠው የለኝ
  ያዙልኝ ፍቱልኝ ለቀቋት አትበሉ፤ እንደ ልቤ ልሁን ራቁ ከስሬ
  መኖር መርጫለሁ ከሰው ተሰውሬ።

 4. Almaz,

  Yoy are 100% right San Francisco Oakland Bay area habeshas are exactly as you described them above. Not only they hurt the souls of Artists but any soul of habesha is in constant tormenting. The divorce rate , elder abuse , child abuse , verbal abuse , emotional abuse , false rumors and physical abuse is all too common. Hate is everywhere amongst the whole Bay area habeshas.

Leave a Reply

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.