ዩኔስኮ ለሰሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ የአደጋ ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ለሰሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ የአደጋ ጊዜ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

ዩኔስኮ ለሰሜን ተራራዎች ብሔራዊ ፓርክ የፋይናንስ ድጋፉን ያደረገው በኢትዮጵያ ጥያቄ መሰረት መሆኑን በፈረንሳይ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

የገንዘብ ድጋፉም ፓርኩ ላይ የደረሰውን አደጋ የሚያጠና እና ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን መሠረት በማድረግ ሊወሰዱ ስለሚገቡ እርምጃዎች የመፍትሔ ሃሳቦችን የሚያቀርብ የኢትዮጵያ እና የዓለምአቀፍ የባለሙያዎች ቡድን ለመቀጥር የሚውል መሆኑም ተገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.