‘’የኢትዮጵያ ፅዳት እና ገበታ ለሸገር’’ አንድ ዓላማ ለማሳካት የሚከወኑ ሁለት ተግባራት

1 min read

እሁድ ግንቦት 11 ቀን 2011 ዓ.ም የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ባለፈው ወር የተጀመረው ኢትዮጵያን የማፅዳት ፕሮገራም ከጠዋቱ 1፡30 ሰዓት ጀምሮ ካሄዳል፡፡ አዲስ አበባን የማስዋብ አካል የሆነው የገበታ ለሸገር የእራት መርሀ- ግብር ደግሞ በምሽቱ ፕሮግራም ይካሄዳል፡፡

ባለፈው ሚያዝያ ወር ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በተገኙበት ኢትዮጵያን የማጽዳት ዘመቻ በይፋ መጀመሩ ይታወሳል፡፡ ከአዲስ በአበባ በተጨማሪም በልዩ ልዩ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የፅዳት ዘመቻ ተካሂዷል፡፡

ይህ የፅዳት መርሀ ግብር የቆሸሹ አካባቢዎችን በእጃችን እያፀዳን በጥላቻ፣በቂም በቀል እና በቁርሾ የቆሸሹ ጭንቅላቶቻቻንን በሰላም፣በይቅርታ እና በፍቅር ለማፅዳት አዲስ ምዕራፍ የምንከፍትበት ከአካባቢ ፅዳት የዘለለ ሀገር የመለወጥ እና ህብረተሰብ የመገንባት ዘመን ተሸጋሪ ዓላማ ያነገበ ነው፡፡ይህንን ተግባር ስንፈፅም ራሳችንን ከጥላቻ፣ከቂም በቀል እና ከቁርሾ በማፅዳት ስለአገራችን አንድነት እና ስለህዝቦቿ አብሮነት መትጋት እንደሚገባን ያሰታውሰናል፡፡
በጥላቻ፣በቂም እና በቁርሾ የተሞላ ልብ በአንድ ጊዜ በሰላም፣በይቅርታ እና በፍቅር እንደማይሞላ ሁሉ ከተሞቻችንም በአንድ ሰሞን የፅዳት ዘመቻ ንፁህ፣ፅዱና ማራኪ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ይህንን በመገንዘብ አካባቢያችን
ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ በቋሚነት የማፅዳት ልምድ ብናዳብር ከተሞቻችንን ለኑሮ እና ለስራ ምቹ፣የቱሪስቶች አይን ማረፊያ ፣የኢኮኖሚ መሰረት እናየ እድል ፈጣራ ማዕከላት ልናደርጋቸው እንችላላን፡፡

ይህንን ታሳቢ ያደረገው እና አዲስ አበባን የማስዋብ የሶስት አመት ‘ሸገርን ማስዋብ’ ፕሮጀክት አካል የሆነው ‘የገበታ ለሸገር’ የእራት ፕሮግራም እሁድ ግንቦት 11 ቀን 2011 ዓ.ም. ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ በሚደረገው የቤተመንግሰት ጉብኝት ተጀምሮ ምሸት ላይ በአፄ ሚኒሊክ የግብር አዳራሽ የእራት ምርሀ ግብር ይጠናቀቃል፡፡ እሰከ አሁን ድረስ ከ200 በላይ ግለሰቦች፣ዓለም አቀፍ እና የአገር ውስጥ ድርጅቶች እና ተቋማት በፕሮግራሙ ለመታደም እና አሻራቸውን ለማኖር መቀመጫ ቦታ ገዝተዋል፡፡

የጠቅላይ ሚንስትር ፅህፈት ቤት አሻራቸውን ላኖሩ ሁሉ ታላቅ አክብሮት ያለው መሆኑን በመግለፅ እያመሰገነ ፤እሰከ አሁን አሻራችሁን ያላኖራችሁ የሀገራችን ዜጎች በሚቀጥሉት ሶስት ቀናት አሻራችሁን እንድታኖሩ እና በአካባቢያችሁ ፅዳትም እንድትሳተፉ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

#PMOEthiopia

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.