የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ ምስጋና አቀረበ

1 min read

በ2011 ዓ.ም እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ላይ እየተካፈለ የሚገኘው ክለባችሁ ግንቦት 4 ቀን 2011 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ በፋሲለደስ ስታዲየም ከወልዋሎ አ/ዩ ክለብ ጋር በነበረበት የ23ኛ ሳምንት ጨዋታ ፡-
1. ከውድድሩ 4 ቀን ቀደም ብሎ የክለቡ አመራሮች ወደ እንግዳው ክለብ አመራሮች ስልክ በመደወል የመረጃ ልውውጥ በማድረግ የማረፊያ ሆቴል ቅድመ ዝግጅት ያደረገ ስለመሆኑ፡-
2. ግንቦት 2 ቀን 2011 ዓ.ም የእንግዳው ክለብ አባላት ከቀኑ 7፡00 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ቁጥሩ በርካታ የሆነ የስፖርት ቤተሰብ አቀባበል አድርጎ ከፍተኛ አውቶቢስ በመመደብ ከአውሮፕላን ማረፈያው እስከ ሆቴል ድረስ በተመልካቾች ታጅቦ የተጓዘ ስለመሆኑ፡-
3. የቡድን አባላት ያረፉበት ሆቴል አካባቢ በግልጽና በስውር ጥበቃ የሚያርጉ የፖሊስ አባላት በመመደብ ጥበቃ ስለመደረጉ
4. ውድድሩ በሚደረግበት ፋሲለደስ ስታዲየም ግንቦት 2 እና 3 /2011 ዓ.ም በተከታታይ ለሁለት ቀኖች ልምምድ እንዲሰሩ ተፈቅዶላቸው ልምምዱን ያከናወኑ ስለመሆኑ፡-
5. በሁለቱ ቀናት የልምምድ ወቅት የፋሲል ከነማ ደጋፊዎች በስታዲየም ተገኝተው ለተጫዋቾቹ ድጋፍና የማበረታቻ ጭብጨባ ያደረጉ ስለመሆኑ፡-
6. ግንቦት 2 ቀን 2011 ዓ.ም በክለቡ ቡድን መሪ አማካኝነት የክለቡ አመራሮች ፣የደጋፊ ማህበር ተጠሪዎች ፣የፀጥታ ሀይል ሀላፊዎች ከቀኑ 10፡00 – 11፡30 ድረስ ጨዋታውን ለመከታተል ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ተመድበው ከተላኩት ኮሚሽነር ጋር ስለተደረገው ዝግጅት ሰፊ ውይይት የተደረገ ስለመሆኑ
7. በመኪና ላይ በተጫነ ሞንታርቦ ድምጽ ማጉያ መሳሪያ በከተማው ውስጥ ስለ ስፖርታዊ ጨዋነት ቅስቀሳ ይደረግ የነበረ ስለመሆኑ ፡-
8. በጨዋታው እለት ወደ ሜዳ ተይዘው ስለሚገቡ የክለቡ አርማና ደጋፍ መስጫ ቁሳቁሶች በደጋፊ ማህበሩ አስተባባሪዎች ተፈትሸው እንዲገቡ በክለቡ ድህረ ገጽ መመሪያ ያስተላለፉ ስለመሆኑ
በአጠቃላይ ከጨዋታው በፊት በጨዋታ መካከል እና ከጨዋታው ፍፃሜ በኋላ የፀጥታ አስተባባሪ ሀይሉ፣የደጋፊ ማህበር አመራሮችና በእለቱ ጨዋታ እስታዲየም የገብተው የነበሩ ቁጥሩ 25,000 የሚገመት ተመልካች የክለቡ አመራር አካላት በመቀናጀት ስፖርታዊ በመሆነ ጨዋነት ለእንግዳው ለወልዋሎ አ/ዩ እግር ኳስ ክለብ ከፍተኛ ድጋፊና መስተንግዶ በማድረግ የክለቡን አመራሮች ተቀብለው ያስተናገዱና የሸኙ መሆኑን ከእለቱ ጨዋታ ኮሚሽነር ሪፖርት የቀረበ ስለሆነ ክለባችሁ ላደረገው አቀባበልና አሸኛኘት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ ምስናጋና አቅርቧል፡፡
via – የአፄዎቹ ገፅ

1 Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.