ምርጫ ቦርዱ ለቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ የዝግጅት ስራውን ማጠናቀቅ እንዳለበት ምክር ቤቱ አሳሰበ

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ፍትሃዊና ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን ለማድረግ የዝግጅት ስራውን ማጠናቀቅ እንዳለበት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አሳሰበ፡፡
የምክር ቤቱ የህግ፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ2011 በጀት ዓመት የ9 ወር እቅድ አፈፃፀም ሪፖርቱን ገምግሟል፡፡

በግምገማውም ቦርዱ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችና የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ስልጠና መስጠቱ በጠንካራ ጎን መመልከቱን ቋሚ ኮሚቴው ገልጿል፡፡ቦርዱ የምርጫ ስራውን ለማዘመን የሚስችሉ የተለያዩ ማኑዋሎችን የማዘጋጀት ስራ መስራቱ እንደ መልካም አፈፃፀም መታየቱን ተነግሯል፡፡

ሆኖም የተጀመረውን የሪፎርም ስራ ፈጥኖ በማጠናቀቅ ቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሃዊ፣ ተዓማኒና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ለማድረግ የሚያስችል ስራ መስራት ይጠበቅበታል ብሏል ቋሚ ኮሚቴው፡፡ ለዚህም ቦርዱ ለቀጣዩ ምርጫ የዝግጅት ስራውን ማጠናቀቅ እንዳለበት አሳስቧል ነው የተባለው፡፡

One Response to ምርጫ ቦርዱ ለቀጣዩ ሀገራዊ ምርጫ የዝግጅት ስራውን ማጠናቀቅ እንዳለበት ምክር ቤቱ አሳሰበ

 1. ለፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ገና ብዙ የሚቀር ጉዳይ እንዳለ የሚታወቅ ስለሆነ የምርጫ ቦርድም ያለተፅእኖ እና በራሱ በመመራት እንዲሁም የፓርቲዎች ሃሳብን በመቀበል ምርጫው መራዘም ካለበት Logical የሆነ የውሳኔ ሃሳብ ማቅረብ አለበት፡፡ ወ/ት ብርቱካን ምዴቃሳም ድሮ በፍርድ ቤቶች ታሳይዊ እነደነበረ ነፃ፣ ገለለተኛና ከአድሎ የፀዳ ፍትህ በምርጫ ሂደቱም ላይ ይህ እንዲፀባረቅ ህዝብ ይመኛል፡፡

  አሁን ባለው ሁኔታ ግን የነ ቶሎ ቶሎ ቤት ግርግዳው ሰንበሌጥ እንዳይሆን ነገሩ ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ይህ ምስኪን ህዝብና በስሜት የሚመራን አፍላ ወጣት ወደልሆነ አቅጣጫ በመምራት የችኮላ ምርጫ ውጤቱ አስከፊ እንዳይሆንና ተጠያቂነትም እንዳይመጣ ማስተዋል ይገባል፡፡

  ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!

  Avatar for Yetesfa Chilanchele

  Yetesfa Chilanchele
  May 16, 2019 at 6:53 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.