ከጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ድህረ ምረቃ ተማሪዎች (Residents) የተላለፈ መልእክት

1 min read

.
እኛ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ሬዚደንት ሀኪሞች ያሉብንን ችግሮች በተለያዩ ጊዜያት ለሆስፒታሉ እና ለሌሎች የሚመለከታቸው አካላት በተለያዩ መድረኮች ያቀረብን ቢሆንም ለእነዚህ ጥያቄዎቻችን ተገቢውን ምላሽ ማግኘት ባለመቻላችን በጋራ ባደረግነው ውይይት መሰረት ሰላማዊ እና ህጋዊ አሰራርን በተከተለ ፤ ታካሚዎችን በከፍተኛ ደረጃ ሊጎዳ በማይችል መልኩ ማለትም የጽኑ ህሙማን ክፍል( ICU) ፣ የማዋለጃ ክፍል( Labor ward) ፣ ድንገተኛ ክፍል( EOPD) እና ድንገተኛ ቀዶ ህክምና( Emergency surgery)ን በduty መርሀ ግብር ለመሸፈን ተስማምተን ስራ ማቆማችን ይታወቃል።
.
ሆኖም ግን በሆስፒታሉ የአስተዳደር ሰራተኞች በኩል እየተፈጸመ ያለው ዛቻ እና ከእውነታው የራቀ የሚዲያ ዘመቻ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው እና ከእውነታው የራቀ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።
.
ማስረጃዎች
1. በቀን 06/09/2011ዓ.ም ስራ የምናቆም መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ አስቀድመን ካስገባነው የጥያቄዎች ሰነድ ጋር አባሪ አድርገን ለሁሉም የትምህርት ክፍል አስተባባሪዎች፣ ለሆስፒታሉ አስተዳደሮች እና ለሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ያስገባንና የሆስፒታሉ አስተዳደር (CED) እና አካዳሚክ ዳይሬክተር ግን የተላከላቸውን ደብዳቤ አንቀበልም ብለው የመለሱ ቢሆንም በቀን 07/09/2011ዓ.ም ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ግን ስለሁኔታው ምንም እንደማያውቁ ገልጸዋል።
.
2. ሆስፒታሉ ውስጥ አሁንም እየሰራ የሚገኘው ሀኪም ከላይ በተጠቀሰው መሰረት በduty መርሀ ግብር ብቻ እየተሸፈነ ባለበት ሁኔታ የሆስፒታሉ አስተዳድሮች ግን ምንም አይነት የስራ ክፍተት ያልተፈጠረ አስመስለው ማቅረባቸው ጉዳዩ ተገቢው ትኩረት እንዳይሰጠው ከማድረጕም በላይ በታካሚወች ላይ የተቃጣ ሀላፊነት የጎደለው ንግግር ሆኖ አግኝታነዋል።
.
3. በመግለጫው ላይ የቀረቡ ማስፋራሪያዎች እና የሀሰት መረጃዎች ፤ ያቀረብናቸውን ጥያቄዎች በህግ አግባብ ከመመለስ ይልቅ ዛሬም እንደትላንቱ በሃይል እና በማስፋራራት ለማፈን እየተሞከረ ለመሆኑ ማሳያወች ናቸው።
.
በመሆኑም የሆስፒታሉ አስተዳደር ከእንደዚሕ አይነት ስራ እንዲቆጠቡ እያሳሰብን ፤ ሌሎችም የሆስፒታላችን ነባር ሀኪሞች፤ የትምህርት ክፍል ሀላፊዎች እና የአስተዳደር ሰራተኞች ጥያቄዎቻችን ተራ የጥቅም ጥያቄዎች ሳይሆኑ በጤናው ዘርፍ የሚታየውን ብልሹ አሰራር እና ደረጃውን ያልጠበቀ የህክምና አሰጣጥ ስርዓት ለማስተካከል የሚደረግ ሁሉን አቀፍ ትግል መሆኑን ተረድታችሁ ከጎናችን በመቆም ታሪካዊ ሀላፊነታችሁን እንድትወጡ ስንል በትህትና እንጠይቃለን።
.
የአዲስ አበባ ሬዚደንት ሀኪሞች

2 Comments

 1. መብትን በህግ አግባብ መጠየቅ ምንም አይደለም እንደውም ታፍኖ ከመሞት መተንፈስ መቻላችሁ ለዚህ ያበቃችሁን የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል ነውና አመስግኑት፡፡
  ግን ዋናው ጥያቄያችሁ ከኑሮ ጋር የተያያዘ ሲሆን አዲስ አለመሆኑን፣ ዘመናትን ያስቆጠረ ነው፡፡ የናንተን ችግር በሁሉም ዘርፍ እየፈጋ ያለው ጎስቋላው የመግስት ሰራተኛ ሁሉ የሚጋራው ነው፡፡ ከጤና አጠባበቅ ጋር ያለው ችግር ስር የሰደደ ነው፡፡ ለዘመናትም የተዘፈዘፈ ነው፡፡ ግን መድሃኒት ስለሌለ፣ ወይም ሌላ ስራ እናቆማለን ማለት ስትመረቁ የገባችሁት መሃላን የዘነጋና ያስተዛዘበ ነው፡፡
  እንዲህ በሰፊው ጥያቄ ስለመኖሩ በማህበራችሁ አማካኝነት እንኳን ሳትነግሩን፣ አገሪቷ መከራ ውስጥ ባለችበት ሰዓት ለምን ሆነ ብለን እንድናስብ እንዲሁም የለውጥ ጠሎች የፖለቲካ ሴራ ይኖራታል ብለን ብንጠረጥር አትፍረዱብን፡፡ ግን ሰልፉና ጥያቄው ለምን ከአክሱም ጀመረ፣ ለምንስ ከሙያ ማበሮቻችሁ አፈነገጣችሁ፣ በሰው ህወት ላይ እየደረሰ ላለው ችግር ተጠያቂው ማነው፣ ሌላውን የመንግስት ሰራተኛ ብሶቱን በመቆስቆስ በመንግስት ላይ ለአመጽ እንዲነሳ በእጅ አዙር የተሸረበ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡
  ከየቦታው ተፈናቅሎ በሚሊየን የሚቆጠረው ህዝብ ምን ይታዘባችሁ ይሆን፡፡ ላመንኛውም እናቱ የሞተችበትና ገበያ የሄደችበት—-ይባላል፡፡
  ለማንኛውም ለአመታት የተዘፈዘፈውን ችግር አንድም ጊዜ ወያኔን ሳትጠይቁ ዛሬ ላይ በሴረኞች እያደረሳችሁ ያለውን ችግር መቼም ቢሆን ታሪክ ይፋረዳችኋል፡፡ ልብ አድርጉ እያልኩ ያለሁት ለምን ጠየቃችሁ ሳይሆን ለምን ዛሬ ሆነ ማለቴ ነው፡፡

 2. ጠቅልሎ ካቀረቡ በኋላ የኛ ጥያቄ ስለህዝቡ ነው ማለት የአዞ እምባ ነው፡፡ ጆሮውን ላመመው ታካሚ የሰገራ ምርመራ ማን እንዳዘዘ አወቁት፡፡ ደሞዝና ጥቅማጥቅም መጠየቅ መብት ነው፣፣ ግን መሸፋፈኛ ህዝቡን ማድረግ ስንተዋወቅ አንተናነቅ ነውና ተዉን፡፡
  የመንግስቱን ተዉteና አስቲ ለምን በግል ስለሚሰራው ችግር፣ ገፈፋ አትነግሩንም፡፡ ስለህዝቡ የምታወሩ፣ ስለፖሊሲው የምትነግሩን ከሆነ በግሉ የጤና ተቋማት በህዝብ ላይ ስለሚደርስ ከእናንተም ውስጥ በማበር ስለምታደርሱት በዝር ከነገራችሁን ወደ አንደ መግባባት መድረስ ይቻላል፡፡ ዛሬ ላይ ስላለው የጤና አገልግሎት መንግስትን እና ተቋማቱን ከግሉ ዘርፍ ነጥላችሁ መብላት አምሯችሁ ከሆነ ሲያምራችሁ ይቅር፡፡ የምንኖረው በአንድ የጋራ አገር፣ ዙሪያ ገባውን አገልግሎት አሰጣጥ፣ ማን እንደሚሰጥ፣ እንዴት እንደሚዘረፍ እናውቃለን ታውቃላችሁና በጠቅላይ ሚ/ሩ ተዘክዝኮ በግልጽ የተነገራችሁን ተቀብላችሁ ማሻሻል፣ መንግስትም ማሟላት ያለበትን በህግ አግባብ መስራት ይገባዋል፡፡
  ወደ አንድ ወገን ብቻ መወርወር አያስፈልግም፡፡ እኛም ጋ ችግር አለ ማለት ለህሊና ሰላም ይሰጣልና፡፡ አለበለዚያ ለ27 አመታት ግፍ ሲፈጽሙብን እንደነበሩ መሪዎቻችን አይንን በጨው አጥቦ ምንም የሚቆጨን ነገር የለም፣ ከደሙ ንጹህ ነን ማለት ስምምነት ላይ ለመድረስ የመጀመሪያው እንቅፋት መሆኑን የተለየ ሳይንስ አያስፈልገውም፡፡ በተረፈ ትንሽ ቆሎ ይዞ ወደ አሻሮ ጠጋ እንደሚባለው በህዝብ ስም፣ በጤና ፖሊሲ ስም የራሳችሁን የግል ጥቅማጥቅምና የሴረኞችን ፍላጎት ለማሳካት መሯሯጥ ሲበዛ ትዝብት ላይ ይጥላልና አይመጥናችሁም፡፡
  የጤና ባለሙያው ችግር ከወታደሩ፣ ከፖሊሱ፣ ከመምህሩ በአጠቃላይ ከሲቪል ሰርቪስ ሰራተኛው የከፋ ነው ብሎ ለመናገር አንድም ማስረጃ ማቅረብ አይቻልም፡፡ ሁሉም ሴክተር ችግር ላይ ነው፤ ሰራተኛው ስቃይ ላይ ነው ነገር ግን ወቅቱ አይደለም ብሎ፣ ችግር ላይ ላለው ህዝብ አዝኖ ከሌለው ላይ እየረዳ ነው እንጂ ወቅቱማ ሃሳብን በነጻነት ለመግለጽ ይመቻል፡፡
  ጥያቄችሁ ወቅቱን ካልጠበቀ ዝናብ ጋር ብናገናኘው ይከፋችሁ ይሆን፡፡ ሰው ተፈናቅሎ፣ ተሰዶ፣ ሞቶ ባለበት በዚህ ሰኣት በመቅረቡ አፈርን፡፡ ለእናንተ የሚሰጥ ማንኛውም ምላሽ በሌላው የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኛ በማነሳሳት አገሪቷን ለማመሰቃቀል የታሰበ መሆኑ ለማወቅ ጠንቋይ መቀለብ አያስፈልገውም፡፡ በመላው አገራችን ተፈናቅሎ ስቃዩን እየበላ ያለው ህዝባችን ምን ይል ይሆን፡፡
  አቤት ትዝብት

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.