በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በተሰጠ መግለጫ የምሁራን አስተያየት

1 min read

የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረ ሚካዔል በቅርቡ በመቀሌ ከተማ ባካሄዱት ጋዜጣዊ ጉባዔ ላይ በትግራይና በአጠቃላይ በሀገሪቱ ስላለው ሁኔታ ሰፊ መግለጫ ሰጥተዋል። ባነሷቸው ነጥቦች ላይ አመለካከታቸውን እንዲገልፁ የህግ ምሁር ዶ/ር መሀሪ ረዳኢንና በፖለቲካ ሥራ የተሰማሩትን አቶ ገብሩ አስታትን ጋብዘናል።

ዶ/ር ደብረጽዮን ካነሷቸው ነጥቦች መካከል ጥቂቶቹን ለመጥቀስ ያህል በትግራይ ላይ ብዙ መረባረብ ቢኖርም ሰላማችንን ለመጠበቅ በመቻላችን ልንቋቋመው ችለናል ብለዋል።

ትግራይ ውስጥ በጊዜ ብድር ያለመክፍል ችግር እንዳለም አንስተዋል። ለአርሶ አደሮች ከፌዴራል መንግሥት ብድር የሚሰጠው በክልል ዋስትና በመሆኑ በጊዜ አልተከፈለም በሚል ፌደራል መንግሥት ለትግራይ ክልል ከሚመድበው ባጀት 200 ሚልዮን ብር ቆርጧል። ገናም እንደሚቀንስ ተናግሯል ብለዋል ዶ/ር ደብረጽዮን። ዶ/ር መሐሪ ታድያ መንግሥት ራሱ ከቻይና የተበደረውን ብድር መክፈል አቅቶት የክፍያ ማራዘምያ እየጠየቀ ባለበት ሁኔታ የትግራይ ገበሬ ብድሩን ባለመክፍሉ የክልሉን ባጀት መቁረጥ ተገቢ አይደልም ብለዋል።

ዶ/ር መሐሪ ረዳኢ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህር ናቸው። አቶ ገብሩ አስራት ደግም የዓረና ትግራይ ለሉዓላዊንትና ለዲሞክራሲ እንዲሁም የመድረክ አመራር አባል ናቸው።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

1 Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.