ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ በሌሉበት ጉዳያቸው እየታየ ያሉ አራት የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገለግሎት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች መጥሪያ ደርሷቸው እንዲቀርቡ ፍርድ ቤት በድጋሚ ትዕዛዝ ሰጠ

1 min read

የፌዴራል ከፍተኛ ደረጃ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት በድጋሚ ትዕዛዝ የሰጠው ሚያዚያ 30 በተሰጠው ትዕዛዝ መጥርያው ከፍርድ ቤት ወጪ ባለመሆኑ ነው።

አሁን ግን ፍርድ ቤቱ የፌደራል ፖሊስ መጥሪያውን ባሉበት እንዲያደርስ ጠቅላይ አቃቢ ህግም ጉዳዩን እንዲከታተል ትዕዛዝ ሰጥቷል።

የዚህን ውጤት ለመጠባበቅና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ትዕዛዝ ለመስጠት ፍርድቤቱ ለግንቦት 16 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል ፡፡

በጥላሁን ካሳ/ EBC

4 Comments

 1. So far Meaza Ashenafi proved she is the wrong person to lead the Ethiopian Justice System. Just like her predecessor She also is too slow to act, she also gives the criminals too much time to cover their tracks. Her predecessor is as guilty as Getachew Assefa or any other top TPLF officials but he is not charged yet.

  Meaza Ashenafi should go back to law school and learn about genocide laws , crime against humanity laws , ethnic cleansing Laws , war crimes laws and parliament monopolizing laws before she rules the Ethiopian justice system.

  The timing of issuing the two warrants for Getachew Assefa are too late. Timing of both the first and the second charging of Getachew Assefa is questionable. Noone knows why Getechew Assefa was not officially charged until it was too late .For the longest Noone even knew if there was ever a warrant out for Getachew’s arrest . Addis Ababa youth were arrested for chewing khat within first few months when team Lemma got to power but Getachew Assefa had no warrant for his arrest out until now. Getachew Assefa Got Egyptian passport because Meaza didn’t charge him until recently giving him enough time to go to Egypt.

  To put our thrust on the justice system or to put our thrust on the government the people of Ethiopia need to freely elect their leaders. EPRDF is going through a fake inner struggle TPLF (Getachew) verses (Abiy) team Lemma Just to postpone election 2020. EPRDF is the cancer for the justice system of Ethiopia.

 2. @paulos, this is very far from reality, dont mix poletics and justice, issues related to Getachew is more of pletics than justice, so it should be solved through poletical decission.

 3. በመዋሸት የተገነባ አመኔታ ከጥርጣሬ የፀዳ አይሆንም፡፡ውሸት ማራባት ከጥቅም ውጪ የሚሆንበት ጊዜ አለው፡፡የማታ ማታም ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ሰዎችም በአንድ ውሸት ሲሳቡና ያንን ውሸት የራሳቸው ሲያደርጉ ከዚያ የሚለያቸው ኃይል አይኖርም፡፡ ኦርጅናሌ ዋሾውን እንደተአምረኛ ያዩታል፡፡ በዙሪያው ይከባሉ፡፡ እንደመንጋም ይነዳሉ፡፡

  በየፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ ጉዳያችን አንፃር የሌለንን አለን፣ ያለንን የለንም ብለን ከዋሸንና ካሳመንን፤ ተከታያችን ሊደሰትበት፣ አልፎም ሊኮራበት ይችላል፡፡ ይሄ እርግማን ነው፡፡ እርግማኑ በመንግሥትም፣ በተቃዋሚም፣ በሰባክያንም፣ በምዕመናንም አንፃር ብናሰላው ያው ነው፡፡ ህዝብን ማታለል ክፉ እርግማን ነው፡፡ የማታ ማታም ዋጋ ያስከፍላል፡፡ያም ሆኖ እንደማናቸውም ነገር ውሸትም ከጥቅም ውጪ የሚሆንበት ጊዜ አለው፡፡

  ያለአቅማችን ጉልበተኛ ነን ማለትም ሆነ ጉልበተኛ ሆነን ምስኪን ኮሳሳ ነን ማለትም ያው መዋሸት ነው፡፡ እያየን አላየንም፣ እየሰማን አልሰማንም፣ እያጠፋን አላጠፋንም ማለትም ያው መቅጠፍ ነው! ስለግልፅነት እያወራን የበለጠ ሚስጥራዊ የምንሆን ከሆነ ያው መዋሸት ነው፡፡ ዛሬ ያልነውን ነገ ካልደገምነው ያው መዋሸታችን ነው፡፡ ሰውን በሸራ ኳስ እያጫወትን እኛ በካፖርተኒ የምንጫወት ከሆነ ያው ማጭበርበራችን ነው፡፡ያብዬን እከክ ወደ እምዬ ልክክም ያው መዋሸት ነው!ካፈርኩ አይመልሰኝ ማለትም ያው መዋሸት ነው!

  አስገድደን የምንፈፅመውም ሆነ ዋሽተን የምናሳምነው፣ አሊያም በገንዘብ የምንደልልው፤ የዘወትሩን ሰው ቢያስጨበጭብልንም የክቱን ሰው ያሳዝናል፡፡ በመዋሸት የተገነባ አመኔታ ከጥርጣሬ የፀዳ አይሆንም፡፡የሌለ ጀግና መፍጠርም ሆነ፤ ያለን ጀግና መካድ ሁለቱም ማታለል ነው፡፡በከፋ መልኩ ሲታይ ራስንም ማታለል ነው፡፡ የሰው ዓላማ የኔ ነው ማለትና የሌላውን ስም የራስ ማድረግ፤ ከኢኮኖሚ ዘረፋም የከፋ ዘረፋ ነው፡:ውሸት እንደማግኔት መግነጢሳዊ ኃይል አለው፡፡ ማግኔት፤ በአንዳች የማይታይ ኃይል ባካባቢ ያሉ ነገሮችን ይስባል፡፡ እነዚያ ነገሮችም በፈንታቸው የመሳብ ኃይል ያበጃሉ::ባካባቢያቸው ያሉትን ነገሮችን በተራቸው ይስባሉ፡፡ ያንን ኃይል ይዘው ይቆያሉ፡፡ ዋናው ነገር እውነቷን፣ እቅጯን አለመርሳት ነው፡፡

 4. Why not such cases are compiled and appeal to International court, Hague? Human Right groups should work with Interpol office, CIA, and other offices to arrest him anywhere and bring to Justice. Based on such report he committed it is one of the worst crime, mass arrest and genocide in present time. Western countries shall also not make ignorance, because mostly they show their concern only if it has their own interest.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.