በባሕር ዳር ከተማ በተከሰተ #የእሳት_አደጋ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

የአደጋው መንስኤ እና የደረሰው ጉዳት ላይ የማጣራት ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም ነው ፖሊስ ያስታወቀው፡፡

እንደ ፖሊስ መረጃ ቃጠሎው የተከሰተው ትናንት ማታ 5፡00 አካባቢ ነው፡፡ በዚህም የሰው ሕይወት ማለፉን፤ በአካል እና በንብረት ላይም ጉዳት መድረሱን የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ ለአብመድ አስታውቋል፡፡ ስለአደጋው መንስኤ እና ስለደረሰው ጉዳት ዝርዝር መረጃ ለማግኘት ጉዳዩን እያጣራ መሆኑንም ነው መምሪያው የገለጸው፡፡

ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ አካላትን በቁጥጥር ስር የማዋል ተግባር እየተከናወነ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ መምሪያው ዝርዝር መረጃውን ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡

በባሕር ዳር ከተማ ከወራት በፊት በደረሰ የእሳት አደጋ በርካታ ቤቶች መቃጠላቸው እና የከተማ አስተዳደሩና የከተማዋ ነዋሪዎች ተጎጂዎችን የማቋቋም ሥራ እያከናወኑ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ AMMA

One Response to በባሕር ዳር ከተማ በተከሰተ #የእሳት_አደጋ ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታወቀ

 1. Unlike most parts of Ethiopia, Tigrai had been accepting all ethnicities to live freely all throughout history until today.

  Tigrai should be a role model to all ethnicities and regions to show them how to treat all Ethiopians .

  Tigrai should teach all Ethiopian ethnicities and regions how to establish other ethnicities in their mist, to live with no worry of being displaced.

  Currently Mekele is the number one place where all young Ethiopians from all ethnicities choose to move to, because of the relatively peaceful climate and the thriving economy in Mekele.

  Avatar for Harayama

  Harayama
  May 18, 2019 at 6:42 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.