ኢዜማ የፖለቲካፕሮግራም ክፍል 1

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

የኢዜማ የፖለቲካ ፕሮግራም በወሳኝ መልኩ ያልተማከለ አስተዳደር (ፌዴራላዊ) ሥርዓትን መከተለን ምርጫው ያደረገ ነው፡፡ ከፍተኛው የመንግሥት ሃላፊነት በሕዝብ ቀጥታ ምርጫ የሚመረጥ ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት እንዲሆን አበክሮ ይሰራል፡፡ ኢ-ዜማ የሕዝብን የሥልጣን ባለቤትነት በማረጋገጥ፤ ዜጎች ከማህበራዊ ፍትህ እሳቤ የሚመነጩ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ፖሊሲዎች የሚከተል ፕሮግራም ከሚገኝ ትሩፋት ተጠቃሚ ይሆናሉ ብሎ ያምናል፡፡ ኢ-ዜማ ሕገ መንግሥት ማሻሻያ በሥርዓት በማድረግ፤ ዜጎች ያለተፅእኖ ተሳትፎ ያደረጉበት፣ የመንግሥትን ተጠያቂነት የሚያረጋግጥ እንዲሆን በትጋት ይስራል፡፡ ዝርዝር የፖለቲካ ምልከታችን ከዚህ እንደሚከተለው ይሆናል፡፡

1.1. የፖለቲካ ሥርዓቱ አደረጃጀት
1.1.1. ኢ-ዜማ የሕገ መንግሥት ማሻሻያ መደረግ አለበት ብሎ ያምናል፡፡ ሕገ መንግስቱ የግለሰብ መብትን የመብቶች ሁሉ የማእዘን ድንጋይ አድርጎ እንዲወስደው፣ የቡድንና የወል መብቶች ከግለሰብ መብቶች የሚመነጩ መሆናቸውን የሚቀበል፣በዘር ወይም በእምነት ላይ ያልተመሰረተ፣ ያልተማከለ ፌዴራላዊ አስተዳደር እንዲኖር ይስራል፣

1.1.2. የፖለቲካ ስልጣን ምንጭ ከህዝብ ይሁንታ የሚገኝ መሆኑን በማመን በነፃ ፍትሓዊ ምርጫዎች ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ አማራጮቹን ለህዝብ ያቀርባል፤ ይህም የሕዝብ የሉዓላዊነት መገለጫ አንደሆነ እና ሥልጣን በሕዝብ ይሁንታ የሚገኝ መሆኑን ማረጋገጫ አድርጎ ይወስደዋል፡፡ የትግል ስልቱም ሰላማዊ ትግል ይሆናል፡፡
1.1.3. ማንኛውም የፖለቲካ ጥያቄዎች በውይይት እና በዴሞክራሲያዊ ስርኣት እንዲፈቱ ይደረጋል፡፡ እንደ አስፈላጊነቱ ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮች ወደ ህዝብ ውሣኔ እንዲሄዱ ስርዓት በማበጀት የህዝብን ውሣኔ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡

1.1.4. የኢ-ዜማ የፖለቲካ ፕሮግራም በማንኛውም ሁኔታ የዜጎችን የኤኮኖሚ ነፃነት፣ ማህበራዊ ፍትህ እንዲሁም የመኖሪያ ምድራችንን ከባቢ ሊጎዳ በሚችል መልኩ አይቀረፅም፡፡
1.1.5. ዜጎች ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ሌሎችንም መብቶቻቸውንና ጥቅሞቻቸውን ለማስከበር በጋራ የመደራጀት፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብታቸው ይከበራል፣

1.1.6. የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት ሊገሰስ የማይችልና የማይገሰስ መሆኑን፤ በኢትዮጵያ ሉአላዊ ግዛት ውስጥ የሚገኝ ማናቸውም የተፈጥሮ ሃብት የሃገሪቱ ዜጎች ሁሉ የጋራ ሃብት መሆኑን ኢ-ዜማ ያምናል፣
1.1.7. ዜጎች በመላው ሃገሪቱ ያለምንም ገደብ መንቀሳቀስ መስራትና መኖር፣ ሃብት ማካበት፣ ባካባቢያቸውም ሆነ በሃገሪቱ ፖለቲካ ያለምንም ገደብ መሳተፍ የሚችሉበትን ያልተሸራረፉ መብቶች ያስከበረ፣

1.1.8. የዜጎችን ህይወት ነጻነትና ንብረት መከላከል የሃገሪቱ መንግስት ተቀዳሚና ፍጹማዊ ግዴታ መሆኑን ያምናል።
1.2. አጠቃላይ የመንግስት አደረጃጀት
1.2.1. የመንግስት አደረጃጀት ፌዴራላዊ ይሆናል፡፡ የፌዴራል መንግስትና የአካባቢ አስተዳደሮች ይኖራሉ፡፡ የአስተዳደር አካባቢዎች አወቃቀር በሚከተሉት መርሆዎች የተመሰረተ ይሆናል፤

1.2.1.1.
1.2.1.2. 1.2.1.3. 1.2.1.4.
መልከአ ምድራዊ አቀማመጥን፣ የሕዝብ አሰፋፈር ለአጠቃላይ አስተዳደራዊና ለልማት ሥራዎች አመቺነትን፤ ቋንቋ፤ ባህል; ስነልቦናዊ ቁርኝት እና ታሪክን፤ የሃብት ስብጥርና ፍትሃዊነት
ለብሔራዊ መግባባት አመቺ ሁኔታ መፍጠርን፤ መሠረት ባደረገ ሁኔታ ይሆናል፡፡

1.2.2. ፌዴራላዊ አወቃቀሩ አንዴ ተሰርቶ የሚያበቃለት ሳይሆን የተቀመጡትን መርሆዎችን ጠብቆ በህዝብ ውሣኔ ከኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እድገታችን ጋራ በመግባባት መንፈስ እየዳበረ የሚሄድ ይሆናል፡፡

1.2.3. የፌዴራል መንግሥቱና በአካባቢ መስተዳድር የሚሾሙ የመንግስት ባለሥልጣናት በሕግ የተወሰነ የየራሳቸው የሥልጣን ድርሻ ይኖራቸዋል፡፡ አንዱ በሌላው የውስጥ ጉዳይ እንዳይገባ ይደረጋል፡፡ የየራሳቸው ሕግ አውጪ፣ ሕግ አስፈፃሚ እና ሕግ ተርጓሚ ይኖራቸዋል፡፡ የአካባቢ መስተዳድሮች የራሳቸው የወንጀል መቆጣጠሪያ የፖሊስ ተቋም ይኖራቸዋል እንጂ ከዚያ ያለፈ ወታደራዊ ኃይል ማደራጀት አይችሉም። የፌደራል መንግሥቱ ብቻ ነው የተደራጀ የጦር ኃይል የሚኖረው።

1.2.4. አማርኛ የፌዴራል መንግስቱ የሥራ ቋንቋ ሆኖ ያገለግላል፡፡ እንዲሁም በሕዝብ ውሳኔ ሲፀድቅ ከአማርኛ ሌላ በተጨማሪ ሌሎች ቋንቋዎች የፌደራሉ መንግሥት የሥራ ቋንቋ እንዲኖር ይደረጋል፡፡

1.2.5. የአካባቢ መስተዳድሮች የሥራ ቋንቋ በአካባቢው በሚኖረው ሕዝብ በሚያደርገው ሕዝበ ውሳኔ መሰረት የሚወሰን ይሆናል፡፡ የአካባቢው መስተዳድር የዜጎችን በፌዴራል ስርዓት በቂ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማድረግ የፌዴራሉን የሥራ ቋንቋ በትምህርት ሥርዓት ውስጥ እንዲካተት ማድረግ ይኖርበታል ብሎ ያምናል፡፡

1.2.6. የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ይሆናል፡፡ የመንግሥት ዓርማ የሚያስፈልገው ከሆነ በሕዝብ ይሁንታ የሚወሰን ይሆናል፡፡ የፌዴራል መንግስት አደረጃጀት

1.3.የፌዴራል መንግስቱ በሕገ-መንግሰቱ መሰረት ተጠያቂነት ባለበት ሁኔታ እንዲደራጅ ይደረጋል፡፡ በህዝበ ውሳኔ በሚደረግ የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ስርዓት መሰረት አድርጎ የሚከተሉት የፌዴራል ስርዓቶች እንዲዘረጉ ይደረጋል፤
1.3.1.1. 1.3.1.2. 1.3.1.3.
1.3.1.4. 1.3.1.5. 1.3.1.6.
1.3.1.7.
1.3.1.8. 1.3.1.9.

በዜጎች ቀጥተኛ ምርጫ በሚመረጠው ፕሬዚደንት ስር የሚቋቋመው የህግ አስፈጻሚው አካልና ህግ በሚያወጡት ሁለት ምክር ቤቶችና ህግ በሚተረጉመው ሶስተኛው አካል መሃል ግልጽነት ያለው ህገመንግስታዊ የስልጣን ክፍፍል እንዲኖር፣ አንዱ በሌላው ስልጣን ጣልቃ እንዳይገባ ማድረግ፣ ለፕሬዜዳንትነት የሚመረጥ ሰው የጠቅላላውን መራጭ 50%+1 ማግኘት አለበት። በመጀመሪያው ዙር ማንም ተወዳዳሪ ይህንን ማግኘት ካልቻለ በሁለተኛ ዙር ሁለቱ ከፍተኛ ደምጽ ያገኙት ተወዳዳሪዎች ብቻ ተወዳድረው ያሸነፈው የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ይሆናል።

ሕግ አውጪው አካል ሁለት ክፍሎች (የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት) የሚኖሩት ሲሆን ሁለቱም ሕግ የማውጣት ስልጣን ያላቸው እና በሕዝብ የተመረጡ ይሆናሉ፡፡ የፌዴራሽን ምክር ቤቱ በአስዳደር አካባቢዎች በእኩል የሚወከሉበት እና የአስተዳደር አካባቢዎች በሚኖራቸው ብሔረሰቦች ብዛት አነስተኛ ቁጥር ላላቸው ብሔረሰቦች ተጨማሪ ውክልና የሚሰጥ ሆኖ አስፈላጊው ድጋፍ እንዲያገኙ ህጎችን የማመንጨት፤ ሕጎችን የመገምገም፤ አፈፃፀማቸውን የመከታተል ሃላፊነት ይኖርበታል፡፡
ሕገ መንግስቱን የመተርጎም ሥልጣን ሕገ መንግስትን ለመተርጎም ስልጣን ለተሰጠው ሕገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ይሆናል፡፡ ምክርቤቶች ሕግን ማውጣት እንጂ ሕገ-መንግስትን ወይም ሌሎች ሕጎችን የመተርጎም ሥልጣን አይኖራቸውም፡፡ የመንግስትን ስራ አስፈጻሚ አካላት እንዲመራ፣ ዜጎች በአንድ ሰው አንድ ድምጽ መርህ የሚመርጡት የሃገር መሪ እንዲኖር የሚያደርግ ፕሬዚደንታዊ የአስተዳደር ስርአት ይሆናል፣ ፕሬዝዳንቱ የሚመረጠው ለአምስት ዓመት ሆኖ በተከታታይ ከሁለት ጊዜ በላይ ሊመረጥ አይችልም፡፡ የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ያልተስማማበትን የሕግ ረቂቅ ለፓርላማ የመመለስና እንደገና ውይይት እንዲደረግበት የማድረግ መብት ይኖረዋል፡፡ ፕሬዝደንቱ እንደገና እንዲታይ የመለሰው የሕግ ረቂቅ በተወካዮች ምክር ቤትና በፌደሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብሰባ በሦስት አራተኛ ድምጽ ከተደገፈ ፕሬዝደንቱ ባይስማማበትም ሕግ ሆኖ ይወጣል፡፡
በአስፈጻሚ አካል ውስጥ በፖለቲካ ሹመት የሚመደቡ ኃላፊነቶች ተለይተው እንዲወሰኑ ይደረጋል፡፡ ማንኛውም የፌዴራል መንግስት የፖለቲካ ሹመት ሥልጣንና ኃላፊነት [በፕሬዜዳንቱ አቅራቢነት?] በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት [ሲጸድቅ] ብቻ የሚወሰኑ ይሆናሉ፡፡ ሹመቱን የማጽደቁ ስራ የእያንዳንዱን እጩ ብቃት በነጠላ በመመርመር ይከናወናል፡፡
[ከፖለቲካ ሹመቱ ውጭ] በአስፈፃሚው አካል ሥር የሚዋቀረው ሲቪል ሰርቪስ ከፖለቲካ ገለልተኛ በሆነ መንገድ በችሎታ እና ብቃት ላይ ተመስርቶ በግልጽነትና በተጠያቂነት መንፈስ የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት በሚችልበት ሁኔታ ይደራጃል፡፡ በሁሉም ያስተዳድር መዋቅር፤ (ቀበሌ፤ ወረዳ፤ ዞን፤ የአካባቢ መሰተዳድር፤ ፌደራል) ያካባቢው ነዋሪ በቀጥታ የሚመርጣቸው ያካባቢ አስተዳደሮች ይኖራሉ።

.1.10. ዜጎችየየአካባቢያቸውንየፍትህናየፖሊስሃላፊዎችበዴሞክራሲያዊመንገድእንዲሾሙናእንዲሽሩተሳትፎ የሚያድርጉበት ሥርዓት ይዘረጋል፣
ሰብአዊና ዴሞክራስያዊ መብቶች
ኢዜማ በሕገ-መንግሰት እውቅና የተሰጣቸውን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ አገራችን የፈረመቻቸውን የሰው ልጆችን ስብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የሚደነግጉ ስምምነቶችን ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፡፡ የአገራችንን ልዩ ሁኔታ ባገናዘበ የቡድን (የብሔረሰብ፣ የሀይማኖት፣ ወዘተ) መብቶች ከግለሰብ መብቶች ጋር ግጭት በማይፈጥረበት መልኩ ጥበቃ የሚደረግለት ሲሆን፤ በጥናት ላይ የተመሰረተ የቡድን ፍላጎታቸውን ለማዳበር እንዲችሉ ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡ የሚዲያ ተቋማት እንዲሁም ሲቪል ማህበራት የዜጎችን ስብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ለማዳበር በነፃነት እንዲደራጁ አስፈላጊውን ድጋፍ የሚያደረግ ይሆናል፡፡

የሃገር መከላከያ ሰራዊት፣ ፖሊስና ድህንነትን
1.5.1. የሃገሪቱ የፀጥታና ደህንነት ተቋማት በሙሉ፤ የሃገሪቱን ሕገ-መንግሥት ጠንቅቀው የሚያውቁ፣ ለህግ የበላይነትና ለዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር በጽናት የሚቆሙ ከፍተኛ እውቀትና ብቃት ባላቸው መሪዎችና አባላት የተደራጁ ተደርገው ይገነባሉ፤

1.5.2. የአገራችን የመከላከያ፣ የደህንነት እና የፖሊስ ተቋማት የአገሪቱን ዜጎች እና ሉዓላዊነት ከማንኛውም ስጋቶች ሽብርተኝነትን ጨምሮ ለመጠበቅ እንዲችሉ፤ የአከባቢያችን ጂኦ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች እና የአገሪቱን አቅም ባገናዘበ መልኩ ሙያዊ ጥራቱና ወቅታዊነቱ የተረጋገጠ ሥልጠና እና ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡
1.5.3. የመከላከያ፣ የደህንነት እና የፖሊስ ተቋማት መንግስት በተቀያየረ ቁጥር የማይቀያየሩ እንደተቋም ቋሚ ሆኖ የመቀጠል ዋስትና ይኖራቸው ዘንድ ከማንኛውም ፖለቲካዊ ፓርቲ ወገንተኝነት የራቁ ተቋማት እንዲሆኑ ይደረጋል፤
1.5.4. የመከላካያና የፖሊስ አባላት ከመደበኛ ወታደራዊ/ፖሊስ ሙያ ውጭ በተለያዩ ሙያዎች የሰለጠኑ፣ ግዳጆች በሌሉባቸው ሰላማዊ ወቅቶች፣ ህዝብን በጤና፣ በደን ልማት፣ በሌሎች ማህበራዊና ኤኮኖሚያዊ አገልግሎት፣ በአደጋ ደራሽነት ስራዎች ለማገልገል የሚያስችለው ብቃት ያለው ተቋም ተደርጎ ይደራጃል፣
1.5.5. የመከላከያ፣ የፖሊስና ደህንነት ተቋማት ለሁሉም የሃገሪቱ ዜጎች፣ የተለያዩ ቋንቋ ተናጋሪዎች፣ ባህል ተላባሾች የእምነት ባለቤቶች ተሳታፊነትን የሚያበረታታና የሚያደፋፍር ፖሊሲዎች ያለውና ፖሊሲዎቹን በተግባር የሚተገብር እውነተኛ ሃገራዊ ተቋም እንዲሆን ይደረጋል፣

2.የኢኮኖሚ ፕሮግራም
ኢዜማ ከሚከተለው የፖለቲካ ፍልስፍና/ማህበራዊ ፍትህ/ ጋር የሚጣጣም ለዜጎች ኤኮኖሚያዊ ነፃነት እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ የኤኮኖሚ ፕሮግራም እና ፖሊሲዎችን ይቀርፃል፡፡ ኢዜማ የመንግሰት የኤኮኖሚ ጣልቃገብነት ሊኖር የሚችልባቸውን ዘርፎች በመለየት በግልፅ የሚያስቀምጥ ሲሆን በማንኛውም ሁኔታ ከዜጎች ጋር መንግስት ውድድር ውስጥ ሊገባ የሚችልበት እድል አይኖርም፡፡
2.1. መርሆዎች
2.1.1. የኢኮኖሚ ፖሊሲያችን የሚቀዳበት ዋና መርህ፤ የአንድ ሀገር ዋና የልማት መሰረትና ሀብት ሕዝቧ ነው ብሎ ይነሳል። የልማት ግብም ሕዝቡ እያደር የተሻለ የኢኮኖሚ ሕይወት እንዲኖረው ማስቻል ነው። ስለዚህም የኢኮኖሚ ፖሊሲያችን ውጤታማነት የሚለካው ይህንን ያገሪቱን ትልቅ ሀብት ባግባቡና ምርታማ በሆነ መንገድ መጠቀምን፤ የዜጎችን ሁለንተናዊ ነጻነትን ማስፋትን (የፖለቲካ ነጻነት ብቻ ሳይሆን ዜጎች አምራች ዜጋ እንዳይሆኑ የሚገድቡ ማናቸውንም እንቅፋቶች ማንሳትን)፤ የዜጎችን አፍላቂነትና ተነሳሽነትን የሚያበረታታ እንዲሆን ማገዝ፤ ማህበረሰቡ በመሰረታዊ ቁሳዊ ፍላጎት ማጣት ምክንያት መሰረታዊ ነጻነቱን እንዳያጣ ማስቻል ዋና ጥቅል መመሪያዎቹ ይሆናሉ።
2.1.2. ኢዜማ ለዘላቂ ልማትና ብልጽግና ትኩረት በመስጠት የሕብረተሰቡን አጠቃላይ የኑሮ ደረጃና ማሕበራዊ ሕይወት የሚያሻሽል፤ [በመንግሥትና በግል ኢኮኖሚ መስኩ ትብብርና መደጋገፍ ላይ የተመሰረተ በስርዓት የሚመራ ገበያ መር የኢኮኖሚ ፖሊሲ ይከተላል፡፡ የግሉ ዘርፍ የኢኮኖሚ ዋና አንቀሳቃሽ ነው ብሎ ያምናል፡፡ ይሁን እንጂ ከፍተኛ የሥራ አጥነት ሲከሰት፣ የኢኮኖሚ መቆርቆዝ

ሲያጋጥም፣ የዋጋ ግሽበት ሲመጣ፣ የመንግስት የበጀት ጉድለት እና መሰል ችግሮች ሲከሰቱ መንግስት
በእውቀትና በጥናት ላይ የተመሰረተ ጊዜያዊ የማረጋጋት እርምጃ ይወስዳል፡፡
2.1.3. ከፍተኛ ካፒታል የሚጠይቅ፣ አዋጪነቱ አጠያያቂ ወይም የሚያስገኘው ጥቅም ከረዥም ጊዜ በኋላ ሲሆን ወይም ተፈላጊነቱ ስትራተጂካዊ በመሆኑ እና በመሳሰሉት ምክንያቶች መንግስት ከግሉ ዘርፍ ጋር በሽርክና ወይም ለብቻው መሰረተ ልማትን ይገነባል፤ የልማት ድርጅቶችን አቋቁሞ ያስተዳድራል፡፡ በግል ባለሀብቶች ሊመሩ የሚችሉ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወደ ግሉ ይዞታ ወይም አስተዳደር
እንዲዛወሩ አፋጣኝ እርምጃ ይወስዳል፡፡
2.1.4. ኢዜማ ለኢኮኖሚ ዘላቂ ልማት ወሳኝ በሆኑ የመሬትና የተፈጥሮ ሀብቶች አጠቃቀም የነፃ ገበያ
ኤኮኖሚን እና የሀገር ሉዓላዊነትን ባስጠበቀ መልኩ እንዲከናወን ዝርዝር ፖሊሲዎች ያውጣል፡፡
2.1.5. ኢዜማ ከዚህም በተጨማሪ ማህበራዊ ፍትህ በሀገሩ እንዲሰፍን፤ በራሳቸው ስንፍና ሳይሆን በገበያ ኢኮኖሚው ተገፍተው ለድህነት የተዳረጉ ዜጎችን ለመታደግ ከሀገሪቱ አቅም ጋር የተናበቡ የኢኮኖሚ
ፖሊሲ እርምጃዎችን ይወስዳል.
ግብርና
2.2.1. ግብርናን በተመለከተ- አብዛኛው የሀገሪቱ ህዝብ ገበሬ በመሆኑና ግብርናም መተዳደሪያው በመሆኑ፣ ከግብርና ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የግብርናውን የኢኮኖሚ ዘርፍ የሚያሳድጉና የገበሬውን ጥቅም የሚያስጠብቁ፣ ከመሬት ባለቤትነት፣ ከግብር፣ ተውፊታዊና ዘመናዊ አስተራረስና ምርት የማሳደግ፣ ከምርት ማከማቸት፣ ከገበያ አቅርቦት፣ ከመሰረተ ልማት እድገት፣ ከአካባቢ ጥበቃ፣ ከምርቶች የአይነት ብዝሃነት ከአምራቹና ከሃገራዊ የምግብ ዋስትና መረጋገጥ፣ ከግብርና ኢንዱስትሪ፣ ከንግድ፣ ከፋይናንስ፣ ከግል ካፒታል ተሳትፎና እንዲሁም ቴከኖሎጂን መሰረት አድርጎ ከእድገት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ፖሊሲዎች በማጥናት ተግባራዊ ያደርጋል፣
2.2.2. ሰፋፊ እርሻዎች እንዲስፋፉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ ሲሆን፣ በኩታ ገጠም ያሉ በአነስተኛ ማሣ ላይ ያሉ አርሶ አደሮች በትብብር እንዲያለሙ ማበረታቻ ይሰጣቸዋል፡፡
2.2.3. የእንስሳና የአሳ ሃብትን በተመለከተ- ከግብርና ቀጥሎ የሃገሪቱ አብዛኛው አምራች ሃይል የተሰማራው በከብት እርባታ ላይ ነው። አሳ የሚያሰግሩ ቁጥራቸው ትንሽ ቢሆንም በሃገራችን በቀላሉ ለበርካታዎች የስራ መስክና የከፍተኛ ሃገራዊ ሃብት ምንጭ መሆን የሚችል ነው። ከነዚህ የኢኮኖሚ ዘርፎች ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የአርብቶ አደሩንና የዓሣ አስጋሪውን ጥቅም የሚያስጠብቁ ከመሬት፣ ከሃይቆችና ከወንዞች አጠቃቀም፣ከተውፊታዊና ዘመናዊ ምርት የማሳደግ፣ ምርት አሰባሰብ፣ ከገበያ አቅርቦት፣ ከመሰረተ ልማት እድገት፣ ከአካባቢ ጥበቃ፣ ከምርቶች የአይነት ብዝሃንነትና ጥራት፣ ከአምራቹና ከሃገራዊ የምግብ ዋስትና መረጋገጥ፣ ከግብርና ኢንዱስትሪ፣ ከንግድና ከፋይናንስ እድገት ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ፖሊሲዎች በማጥናት ተግባራዊ ያደርጋል፣
ኢንዱስትሪ/የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ
2.3.1. የኢንዱስትሪ/ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ አሁን በአገሪቱ ያለውን ከፍተኛ የወጣት ሀይል ወደ ሥራ ለማስማራት የሚችል መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ባለሀብቶች በዚህ ረገድ ለሚያደርጉት ተሣትፎ ከፍተኛ ድጋፍ የሚያደርግ ፖሊሲ ይነድፋል
2.3.2. ሰፊ የአምራች መሰረት ያለው፣ በአነስተኛና በመካከለኛ ደረጃ በሚገኙ ኢንዱስትሪዎች አማካይነት ሃገራዊና ከባቢያዊ እንዲሁም አለማቀፋዊ ተፈላጊነት ያላቸውን ምርቶች በጥራት የሚያመርት፣ ቀጣይነት ያለው በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሚደገፍ፣ ለጥናትና ምርምር፣ ለፈጠራና ለግኝት በቂ ካፒታል የሚያውል፣ በአከባቢያዊና በአለማቀፍ መድረኮች በምርት አይነትና ጥራት ተፎካካሪ መሆን የሚችል፣ ከገበሬውና ከግብርናው ዘርፍ ጋር በቅጡ የተሳሰረ፣ የአካባቢ ጥበቃን፣ የሰራተኛውን ጥቅምና ደህንነት የሚያስከብር፣ለውጭ ባላሃብቶች ከሃገሬው ጋር ተቀናጅተው የሚሰሩበትን አግባብ የሚያበረታታ፣ ለሃገራዊ ባላሃብቶች እንክብካቤ የሚያደርግ በጥናት ላይ የተመሰረተ የማኑፋክቸሪንግ ፖሊሲ ቀርጾ ተግባራዊ ያደርጋል።

የአገልግሎት
2.4.1. የቱሪዝምና የሆቴል እንዱስትሪውን ጨምሮ ሌሎችንም በሃገራችን ያሉ የአገልግሎት ዘርፎችን በአንድ ስንደምራቸው በርካታ ባለሃብቶች ከከፍተኛ እስከ ዝቅተኛ ደረጃ የሚሳተፉባቸውና የበርካታ የሃገሪቱ ዜጎች የስራ ምንጭ ናቸው። በአገልግሎት ዘርፉ የተሰማሩት ስራተኞች ቁጥር ከፋብሪካ ሰራተኞች ቁጥር እጅግ ይልቃል። በዘርፉ ጥራትና ልቀት ላይ የተመሰረቱ ለደንበኞቻቸው አስተማማኝ አግለግሎቶች የሚያቀርቡ ድርጅቶች እንዲስፋፉ ማድረግ፣
2.4.2. ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ ልዩ ቦታ እንዲኖራት የሚያስችል፣ አገሪቱ ያላትን ቅርሶችና የተፈጥሮ ሀብት በተገቢው በማስተዋወቅ፣ እንዲሁም በኮንፈረንስ ቱሪዝም ልታገኝ የምትችለውን ጥቅም ባገናዘበ መልኩ ባለሀብቶች ተሳትፎ እንዲያደርጉ ምቹ ሁኔታ የሚፈጠር ሲሆን ትምህርት ቤቶች ለቱሪዝም ሴክተሩ በተጠና ሁኔታ የሰው ሀይል እንዲያቀርቡ ፖሊሲዎች ይቀረፃሉ፡፡
2.4.3. የቱሪዝም መዳረሻ ስፍራዎች ተለይተው በቂ የመሰረተ ልማትና ምቹ መስተንግዶ እንዲኖራቸው በማድረግ የቱሪስቶችን የቆይታ ጊዜ ለማራዘም የተቀናጀ ስራ ይሰራል፡፡
የተፈጥሮ ሀብትና መሬት
በኢትዮጵያ የግዛት ክልል የሚገኝ ማንኛውም የተፈጥሮ ሀብት የሁሉም ዜጎች የጋራ ሀብት ነው ብሎ ኢዜማ ያምናል፡፡ አሁን ያለው የመሬት ፖሊሲ ለኢኮኖሚ እድገት ያለውን እንቅፋት በመረዳት የተለያዩ ዓይነት የመሬት አጠቃቀም እና ይዞታ እንዲኖር ያደርጋል፡፡ የመሬት ይዞታም በመንግሰት፣ በማሕበረሰብ ወይም በግል ሊሆን ይችላል፡፡
2.5.1. በኢትዮጵያ ግዛት ክልል ዜጎች ያልሰፈሩበትን ቦታ ጨምሮ ሌሎች ፓርኮችና ለመንግሥት አገልግሎት አስፈላጊ የሆኑ ቦታዎች በመንግሥት ይዞታነት ሊያዙ ይችላሉ፤ በመንግሥት ይዞታነት ያሉ ቦታዎች ግልፅ በሆነ መሰፈርት እና የገበያ ዋጋ ወደ ግል ሊዛወሩ ይችላሉ፤
2.5.2. በአርብቶ አደር አካባቢ ለግጦሽ፣ በሌሎች አካባቢም ለልዩ ልዩ ማህበራዊ አገልግሎት የሚውሉ በማሕበረሰቡ የሚተዳደሩ የወል የመሬት ይዞታዎች ሊኖሩ ይችላሉ፤
2.5.3. ዜጎች መሬትን በግል ይዞታነት በባለቤትነት መያዝ፣ ማከራየት፣ መግዛት መሸጥና መለወጥ የሚችሉበት ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል፡፡
2.5.4. ኢዜማ የአካባቢ ጥበቃን በሚመለከት ግልፅ የሆነ የአረንጓዴ ልማት ፖሊሲ ቀርፆ ተግባራዊ ይደረጋል፡ ፡
የከተማ ልማት
2.6.1. ኢዜማ አሁን አገራችን የምትገኝበትን ዝቅተኛ የከተሜነት ደረጃ ለመለወጥ፣ ቢያንስ በአፍሪካ ደረጃ በአጭር ጊዜ ለመድረስ የሚያስችል የከተሞች መስፋፋትን ያበረታታል፡፡ የአስተዳደር አካባቢዎች በተቻለ ሁኔታ ከአንድ ርዕሰ ከተማ ውጭ ለመፍጠር እንዲችሉ ማበረታቻ ይደረጋል፡፡ ዜጎች በሁሉም የአገሪቱ ክፍሎች ተዘዋውረው መስራት የሚችሉበትን ሰላማዊ ሁኔታ በመፍጠር የተለያዩ ከተሞች እንዲፈጠሩ የሚያበረታታ ፖሊሲ ይቀረፃል፡፡
2.6.2. የመሰረተ ልማት ግንባታዎች ከተሞችን ለመመስረት በሚያመች መልኩ እንዲሆኑ በማድረግ በገጠር መሬት ላይ ያለውን ጫና በመቀነስ ምርታማነት እንዲያድግ እገዛ የሚያደርግ ከተሜነት ያበረታታል፡፡
2.6.3. ከተሞች የአረንጓዴ ልማትን ያካተቱ መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊነት
2.6.4. በሁሉም የአስተዳደር አካባቢዎች የሚገኙ ከተሞችም ሆነ እንደ ድሬዳዋና አዲስ አበባ ያሉ የፌደራል
ከተሞች ውስጥ በከተማው ነዋሪዎች የሚመረጡና የከተማውን ህዝብ ፍላጎትና ለከተማ ነዋሪዎች የሚያስፈልጉ አገልግሎቶችን ማቅረብ ዋና ተልእኮአቸው ያደረጉ በሕዝብ ቀጥታ ምርጫ የተመረጡ ከንቲባዎች የሚተዳደሩ የከተማ አስተዳደሮች ይደራጃሉ።
መስረተ ልማትን
2.7.1. መሰረተ ልማት ባጠቃላይ ኢኮኖሚውን አሳላጭና የሚያሳድግ ብቻ ሳይሆን ከፍተኛ የስራ ፈጣሪ የኢኮኖሚ መስክ ነው። ማንኛውም የመሰረተ ልማት ስራ በሃገር ውስጥ ባለሃብቶችና ባለሙያተኞች፣
2.6.
2.7.

በሃገር ውስጥ ሰራተኞች በሃገር ወስጥ በሚመረቱ የእቃ አቅርቦቶች የሚሰራበትን አግባብ ማመቻቸት፣ አቅም መገንባት ማናቸውንም የተለያዩ አሰፈላጊ ድጋፎች በማድረግ በከፍተኛ ጥራትና ልቀት የሚፈጽም ይሆናል። የተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች ተመጣጣኝ የሆነ የመስረተ ልማት ሽፋን እንዲያገኙ፣ በመሰረተልማት መረብ እንዲተሳሰሩ የሚያደርግ በጥናት ላይ የተመሰረተ የመሰረተ ልማት ፖሊሲ ተግባራዊ ያደርጋል።
ትራንስፖርት፣ ኮምኒኬሽን፣ የዉሃና ፍሳሽ እንዲሁም የኤሌክትሪክ አገልግሎቶች ከህዝቡ ገቢ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ በብዙሃን ማጓጓዣ ላይ የተመሰረተ የባቡሮችና የአውቶቡሶች አገልግሎቶች ማስፋፋት፣ ከኤሌትሪክ ማመንጨት እድገት ጋር ተያይዞ የሃገሪቱን የተለያዩ የአስተዳደር አካባቢዎችና ከተሞች በኤሌትሪክ ጉልበት በሚሰሩ ከተማና የአስተዳደር አካባቢ አቋራጭ የባቡር መጓጓዣዎች ማስተሳስር፤ አካባቢንና አየርን የሚበክሉ ማናቸውንም አይነት የመጓጓዣ ዘዴዎችን የሚቀንስ የትራንስፖርት ፖሊሲ መከተል፣
3.
2.8. የፋይናንስ እና የባንክ የአገልግሎት
19.1. ጥብቅ የሆነ የፊስካል እና ሞኒታሪ ፖሊሲ ተግባራዊ ማድረግ፣ ከአቅም በላይ መንጠራራትን፣ ከሃገሪቱ አመታዊ ገቢ የመክፈል አቅም ጋር ሲነጻጸር አደገኛ የሆነ፣ከውጭ ሃገርም ሆነ ከሃገር ውስጥ በመንግስት የሚወሰድን የብድር ስርአት የማይፈቅድ፣ የዋጋ ግሽበትን የሚቆጣጠር፣ የህዝብ ንብረት ብክነትን ለመቆጣጠር የሚያስችል የአካውንቲንግና የኦዲቲንግ ሙያተኞችን ሃላፊነትን ያገናዘበ ህጋዊ ጥበቃ የሚደረግለት ነፃና ገለልተኛ የፋይናንስና የባንክ ፖሊሲ ተግባራዊ ያደርጋል፣
19.2. ጥናት ላይ ተመስረቶ ተገቢውን ወለድ በመክፈል የገንዘብ ቁጠባን የሚያበረታታ፣ የቢዝነስ የንግድና የፕሮጀክቶችን አዋጭነት በመገምገም ያለ ማስያዣ ለታታሪ ሰራተኞች ብድር የሚያሰጥ አሰራርን የሚያበረታታ፣ ባንኮች ከወለድ ነፃ አገልግሎት ሊሰጡ የሚችሉ መሆናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ የፋይናንስ ሴክተር በዘር፣ በሀይማኖት ተለይቶ እንዳይደራጅ ቁጥጥር ያደርጋል፡፡
የማሕበራዊ ፕሮግራም
2.7.2.
የኢዜማ ማህበራዊ ፕሮግራም ዓላማ፤ በተለያየ የተበላሻ የመንግሥት ፖሊስ በመገፋት ከኤኮኖሚ እና ፖለቲካዊ ተሳትፎ እንዲርቁ የተደረጉ ብቻ ሳይሆን በዚሁ መነሻ ለከፍተኛ ማህበራዊ ቀውስ የተዳረጉ ዜጎችን በስርዓቱ ውስጥ ለማካተት የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት ነው፡፡ ዜጎች በማህበራዊ ዘርፍ ኢዜማ የሚወስዳቸውን ተጨባጭ እርምጃዎች በመጠቀም እራሳቸውን ጠቅመው ለአገር የሚተርፉ ዜጎች ማድረግ የማህበራዊ ፕሮግራማችን ቀዳሚ ትኩረት ነው፡፡ የኢዜማ ፕሮግራም በምንም መልኩ ሥራ ጠልነት እና ድጋፍ ጠባቂነትን አያበረታታም፣ ዝርዝር ፖሊሲዎችም ይህን ታሣቢ ያደረጉ ይሆናሉ፡፡
3.1. ድህነት ማጥፋት
ኢዜማ ድህነት ዝም ብሎ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ችግር ብቻ ሳይሆን የሰውን ልጅ ነጻነት የሚገድብ፤ እንደፖለቲካ ማህበረሰብ በሰላም ለመኖር የማያስችለን ችግር መሆኑን ተገንዝቦ ድህነትን ከምድራችን ለማጥፋት የቅድሚያ ቅድሚያ ሰጥቶ ይንቀሳቀሳል።
ኢዜማ ድህነት የመንግሰት ፖሊስ ድክመት ውጤትና በጥሩ ሁኔታ ቁጥጥር ያልተደረገበት ልቅ የገበያ ኢኮኖሚ ድክመት ውጤት መሆኑን ይገነዘባል። በመሆኑም ሥርዓቱ እነኝህን ድክመቶች ተገንዝቦ ድህነትን ከሀገራቸን ለማጥፋት መወሰድ ያለባቸውን ዝርዝር የፖሊሲና ያሰራር አቅጣጫዎች በጥናት ላይ በመመርኮዝ ተግባራዊ ያደርጋል። በተጨማሪም ዜጎች ድህነትን በመጠየፍ የሚወስዱት ተነሳሽነት እጅግ አስፈላጊ በመሆኑ፣ ዜጎች ለስራ ያላቸውን ተነሳሽነት የሚያጎለብቱ የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስራዎች ይሰራሉ፡፡
3.2. የሰው ሀይል ፍልሰትና ስደት
ዜጎች ሀገራቸውን ለቀው ለስደት የሚነሳሱት በሀገር ውስጥ በሚኖር የኤኮኖሚ አማራጭ እጦት፤ በስልጣን ላይ የወጡ ኃይሎች ለደጋፊዎቻቸው ወይንም ለጥቅም ተጋሪዎቻቸው በሚያደርጉት አድሎአዊ አስራር እንዲሁም በነፃነት ተዘዋውሮ ለመስራት በተለያየ መንገድ በሚደረጉ ፖለቲካዊ ገደቦች ናቸው፡፡ ዜጎች በአማራጭ የሰራ በሕክምና ጥራት ደካማነት ምክንያት የሀገሪቱ ባለሀብቶችና የተሻለ የኢኮኖሚ ይዞታ ላይ የሚገኙ ዜጎች ለህክምና ውጭ ሀገር እየሄዱ የሚያጠፉትን የውጭ ምንዛሪ ለማስቆም ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ዘመናዊ ሆስፒታሎች እንዲያደራጁ ማበረታታት።
3.5. ማህበራዊ ዋስትና
የማህበራዊ ዋስትና ለዜጎች መስጠት ለአንድ ሀገር ግዴታ መሆኑን በመረዳት፤ ዜጎች ይህን ለማድረግ የሚያስችል ተመጣጣኝ መዋጮ እንዲያደርጉ ይደረጋል፡፡ በፍላጎታቸው በሚያደርጉት መወጮ መሰረትም መብታቸው ሊከበርላቸው የሚችልበት ስርዓት ይዘረጋል፡፡ ማህበራዊ ዋስትና የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች ከኢኮኖሚ እድገት ደረጃ ጋር እየተገናዘበ ማስተካከያና ማሻሻያ ይደረግበታል፡፡ አሁን በስራ ላይ ያለው በማህበራዊ ዋስትና ስም የግል ተቀጣሪ ሰራተኞች ገንዘብ እንዲያዋጡ፤ ነገር ግን በምንም መልኩ ተጠቃሚ የማይሆኑበት ስርዓት ግልፅነት ባለው አስራር እና ዜጎችን በሚጠቅም መልኩ ይለውጣል፡፡ ዜጎች ሁሉ ወጥ የሆነ የማህበራዊ ዋስትና መለያ እንዲኖራቸው በማድረግ ተጠያቂነት ያለው የማህበራዊ ዋስትና ስርዓት ይዘረጋል፡፡
3.6. ሴቶች
ኢዜማ ሴቶችን ያገለለ ማንኛውም ዓይነት ፖሊስ ውጤታማ እንደማይሆን ይገነዘባል፡፡ በተለይ የሴቶች በፖለቲካው መስክ መሳተፍ የራሳቸውን ጉዳይ በጥልቅ ያገናዘበ ፖሊስ ለመቅረፅ ፋይዳው የጎላ እንደሚሆን ያምናል፡፡ ትምህርት ለእኩል ተሣትፎ ወሣኝ መሣሪያ በመሆኑ ሴት ልጆች ከትምህርት ገበታ የሚያስቀሩ ማነቆዎችን በማስወገድ ዘላቂ የሆነ የሴቶች ተሳትፎን ለማረጋገጥ ይስራል፡፡ ሴቶች አሁን ያለው የፖለቲካ ምህዳር የፈጠረው አፈና ሲነሣ ሙሉ ሀይላቸውን ሊጠቀሙ የሚችሉበት ዕድል እንደሚፈጠር ኢዜማ ያምናል፡፡ ለይስሙላ ለፖለቲካ ፍጆታ በሚል የሚደረጉ የሴቶች ተሳትፎን ኢዜማ አይቀበልም፡፡
3.7. ወጣቶች
በሀገራችን የሚታየው የወጣት ስራ አጥነት በግልፅ የሚያመለክተው፤ አገሪቱ ያላትን ወሣኝ የእድገት ምንጭ በአግባቡ መጠቀም ያለመቻሏን ነው፡፡ ይህን እምቅ የእድገት ምንጭ የሆነውን የወጣት ሀይል አሟጦ ለመጠቀም እንዲቻል፤ ይልቁንም ወጣቱን ከወላጆቹ ጋር በተጣበበ የግብርና መሬት ላይ የሚያደርገውን የመሬት ቅርምት በማላቀቅ ከግብርና ውጭ ባሉ የስራ እድሎች ተሣታፊ ለማድረግ የተቀናጀ የከተማ ልማት ስትራቴጂዎች ይቀረፃሉ፡ ፡
3.8. አካል ጉዳተኞች
በአሀገራችን ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ የተለያየ የአካል ጉዳት ያላባቸው ፤ነገር ግን በአገር ዕድገት ላይ ከፍተኛ ተሳትፎ ማድረግ የሚችሉ ዜጎች ይኖራሉ፡፡ አካል ጉዳተኞችን ከግምት ውስጥ ያስገባ የመስረተ ልማት ግንባታዎች ያለመኖር፣ አድሎዋዊ የስራ ቅጥርና ምደባ፣አስፈላጊው የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች አለመኖር፣ ወዘተ፣ ኑሮዋቸውን አስቸጋሪ ያደረገው መሆኑን ኢዜማ ይገነዘባል፡፡ ይህን አስቸጋሪ ሁኔታ ለመለወጥ የሚያስችል ዝርዝር ፖሊሲ ወጥቶ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
3.9. አረጋውያንና ወላጆቻቸውን ያጡ ህጻናት
ተንከባካቢ የሌላቸው አረጋዊያን እንዲሁም ወላጅ ያጡ ህፃናትን መንከባከብ ለበጎ ምግባር በሚዘጋጁ ዜጎች ብቻ የሚተው ባለመሆኑ አስፈላጊው ድጋፍና እንክብካቤ እንዲያገኙ የሚያስችል ስርዓት ይዘረጋል፡፡ በማንኛውም ሁኔታ ህፃናትን ለልመና ተግባር ማዋል እንዲቀር የሚያደርግ ፖሊሲ ተቀርፆ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
3.10. ስነ ሕዝብን
የተመጣጠነ የህዝብ እድገት ለዘላቂ ልማት ወሣኝ መሆኑን በመገንዘብ ሀገሪቱ የምታስመዘግበውን እድገት በማይፃረር መልኩ፤ የስነ ህዝብ ፖሊሲ ተቀርፆ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ የህዝብ ቆጣራ ውጤቶች ከምንም ዓይነት የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነፃ በሆነ መንገድ እንዲከናወን እና ውጤቱም ለሰብዓዊ ልማት ብቻ የሚውል ይሆናል፡፡

ይቀጥላል

14 Responses to ኢዜማ የፖለቲካፕሮግራም ክፍል 1

 1. When was Amharic chosen by referendum to be the official language? How far do you thing you can go with your political program? Go to Bahr Dar to preach it and you will see what will happen to you. Oh, ya! Berhanu has already seen it before. Will he go there again?

  OR, go to Oromia, Gurage, Sidama, Walayta, Somali, Afar, Kambata, Hadiya, ALL SOUTH and preach it. I don’t understand why the 7-star general Berhanu Nega cannot grasp this reality after graduating from seven party colleges. Shameless! Your so-called program is DEAD ON ARRIVAL.

  John Smith
  May 18, 2019 at 11:42 am
  Reply

  • በአማርኛ አንበብህ በእንግሊዘኛ የምትጽፍ ስሚዝዬ ደህና ነህ፡፡ የአንተ ደግሞ አደባበቅ በራስህም በአባትህም ስም መሆኑ ለየት ያደርግሃል፡፡ አይ ጆኒ
   በፕሮግራሙ ላይ ብዙ ተብሎ አንድ ነገር ላይ ብቻ መንጠልጠልህ ምን ያህል ጥላቻ ለህዝቡ እንዳለህ ማሳያ ነው፡፡ በፕሮግራሙ ፖለቲካው፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮቹን አንስቶ የኔ ፍላጎት የሚለውን ነገረን-ፓርቲው፡፡ አሁን ከአማርኛ ውጭ ሁሉንም የኢትዮጵያ ህዝብ ሊያግባባ የሚችል ሌላ ቋንቋ አለ ብሎ ማሰብ ይቻላልን ወይንስ ተራ ጨለምተኛ መሆን ነው፡፡ ለማንኛውም ጋምቤላ፣ ደቡብ፣ ቤኒሻንጉል፣ አዲስ አበባ፣ ሃራሪ፣ የክልሎቹ ጭምር ቋንቋ አማርኛ ነው፡፡ አማርኛን ሊተካ የሚችል አጠገቡ የሚደርስ ካለ ይነገረን፡፡ መቼም ስሚዝዬ እንትን እንደማትል እርግጠኛ ነኝ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ 80 ሚሊዮን ህዝብ አማርኛ ቋንቋን ይናገረዋል፣ ይጽፈዋል፣ ያነበዋል፡፡ በቃ ምክንያቱ ይህ እንጂ በዘር/ጎሳ ቁጥርማ አይደለም፡፡ የዘር ቁጥር የሚጠቅመው ወያኔ ላቋቋመው ምክር ቤት ወንበር ድልድል ብቻ ነው፡፡ አሁንስ
   ፈረንጅ ቻው

   አማርኛ
   May 22, 2019 at 9:32 pm
   Reply

   • ኢትዮጵያዊ ማለት አንተ ብቻ ነህ? እነማንን ቆጥረህ ነው ኢትዮጵያዊ ሁሉ አማርኛ ይናገራል የምትል ጨምላቃ? One of the main quest of the Oromo is to make Oromiffa the other official language. That is not yet answered. Do you think the Oromo people went back to sleep? Every nation and nationality has the right to demand that its language be a working language of the federation. If the demand is not met? There is still article 39 in the constitution! If that too is denied? One has AK47s! Capito?

    Abba Caala
    May 26, 2019 at 6:50 pm
    Reply

 2. This trash reflects for which values this organization standards. The individuals in this group are the neo-nazist of Ethiopia. They want to take back the Oromo and oromia about 100 years. But they have forgotten who has given them the freedom of coming together.

  You are supported by ultranationalists like Dawit Woldegeorgies and Eskinder Nega. But is futile.

  Dawit Woldegeorgies is one of  the worst racists and anti-Oromo elements. He has been approaching the Oromo politicians and intellectuals in the last couple of years, in order to convince them his malicious strategies. I think all of the Oromo politicans have ignored his deceptive strategies. That is why he has strated desperately and hopelessly barking like a greedy dog. 

  Dawit has been scheming day and night a plan of instigating violences in Ethiopia, so that the formation of a transitional government maybe realized. Thereby, his main objective is helping the ultra nationalists of the Amahara, so that they can overtake political powers during the transitional period and can change the Ethiopian constitution, the current federal structures and make everything retrogressive.

  The ultranationalists of the Amahara like Dawit Woldegeorgies are always sick. Their mind setup is based on blaming others for the problems they have created. Dawit tried to sell the problems which have been created by the members of the National Movement of the Amahara (NAMA) as if it was caused by external forces. 

  For all these chaos are only the racist  neo- nazist organization NAMA and its associates responsible. The stubbornness and arrogance of these bunch of individuals will be punished soon all over Ethiopia.

  Here are the slogans of the neo-nazist organization NAMA, just to mention a few:
  – The Amahara  people will be back to its superiority!
  – Most part of Oromia belongs to  the Amahara people 
  – Amahara people must be worshiped as a creator of Ethiopia.
  – The Shewa Oromoo are not Oromo, they are Oromizied Amhara.
  – The Amahara are the best nation in the world.
  – All peoples in Amhara region (Oromo, Agawo, Kimanti, Wayito and Argoba) are Amahara weather they like it or not.
  – Amaharanism is like sprite.  Ever kids in Ethiopia goes to school, in order to behave like Amhara or to become Amhara.

  With such illusions they try to mislead the Amahara people. Their contempt for the other peoples of Ethiopia is enormous.

  Gamadaa
  May 18, 2019 at 6:54 pm
  Reply

  • Dear commentators, Gemeda, smith and Mbirr,
   your are really trash! pure non sense. you will see Ezema will govern Ethiopia.

   Belay
   May 21, 2019 at 2:06 am
   Reply

  • በአማርኛ አንበብህ በእንግሊዘኛ የምትጽፍ ዘመዴ ጋሜ-ደህና ነህ?
   የፖለቲካ ፓርቲ የሚቋቋመው በግለሰቦች ስብስብ የገባቸውን፣ ይጠቅማል የሚሉትን ለህዝብ በመግለጽ አሸናፊ ሆነው ከተገኙ ሀገር ለመምራት ነው፡፡ ኢ-ዜማ በፕሮግራሙ ላይ ብዙ ብሎ አንድ ነገር ላይ ብቻ መንጠልጠል ምን ያህል ጥላቻ ለኢትዮጵያ ህዝብ እንዳለህ ማሳያ ነው፡፡ በፕሮግራሙ ፖለቲካው፣ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳዮቹን አንስቶ የኔ አረዳድ የሚለውን ነገረን-ፓርቲው፡፡
   አሁን ከአማርኛ ውጭ ሁሉንም የኢትዮጵያ ህዝብ ሊያግባባ የሚችል ሌላ ቋንቋ አለ ብሎ ማሰብ ይቻላልን? ወይንስ ተራ ጨለምተኛ መሆን ነው፡፡ ለማንኛውም ድሬዳዋ፣ጋምቤላ፣ ደቡብ፣ ቤኒሻንጉል፣ አዲስ አበባ፣ ሃራሪ፣ የክልሎቹና የዞኖቻቸው ጭምር የስራ ቋንቋ አማርኛ ነው፡፡ አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ አማርኛን ሊተካ የሚችል ሌላ ቋንቋ ካለ ይነገረን፡፡ መቼም “እንትን” የሚባለው ቋንቋ እንደማትል እርግጠኛ ነኝ፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ 80 ሚሊዮን ህዝብ አማርኛ ቋንቋን ይናገረዋል፣ ይጽፈዋል፣ ያነበዋል፡፡ በቃ ምክንያቱ ይህ እንጂ በዘር/ጎሳ ቁጥርማ አይደለም፡፡ የዘር ቁጥር የሚጠቅመው ወያኔ ላቋቋመው ምክር ቤት ወንበር ድልድል ብቻ ነው፡፡ እሱም ወንበር ላይ ተዘፍዝፎ ለነመለስ ለማጨብጨብ ካልሆነ ለአንተም ለኔም የበጀን ነገር አላየንም፡፡ ስሙ የህዝብ ተወካዮች እንጂ የብሄር ተወካዮች አይልም፡፡ ይሄን ጊዜው ሲፈቅድ እnengageraለን፡፡ በሃሳብ ተወዳድሬ አሸንፌያለሁ ካሉ በኋላ በኮታ ወንበር አይሰጥም፡፡ የተመረጠው ሃሳብ እንጂ ዘር አይደለምና፡፡
   አሁን የኦነግ የፖለቲካ ፕሮግራም በአማርኛ ተጽፎ፣ ሌሎቻችንም አካታች ስለመሆኑ ለማወቅ ጉጉት ላይ ነን፡፡ ይህን የሚነግረን አጣን፡፡ ድርጅቱን በወሬ ካልሆነ እኛ ጆሮ ቆራጣዎቹ በስማ በለው እንኳን የሚነግረን አላገኘንም ፡፡ ግን አንዳንዶች ድርጅቱን የሚደግፉት ፕሮግራሙን አንበበውና ተረድተው ወይንስ በነሲብ? ጋሜ ምላሽ ስጠን
   ለማንኛውም በአማርኛ ላይ መግባባት ካቃተን በየአመቱ እጣ እየተጣለ ሁሉም ቋንቋ በተራ የፌዴራል መግባቢያ ለምንአይሆንም፡፡ በዚህ ከተስማማን በ80 አመት አንዴ ይደርሰናል፡፡ ይሄ ደግሞ ምርጥ ድንቁርና ነው፡፡ ለዚህም ነው የኔ ካለሆነ፣ ብዙ ስለሆንኩ፣ ቆዳ ስፋቴ የትዬ ለሌ በመሆኑ እኝክ ብሎ ረገዳ መርገጥ ትርፉ ጉልበት መጨረስ ነውና አማርኛ የኛ የሁላችን ነው ብለን ተቀብለን፣ ሌሎቹንም ቋንቋዎች እያሳደግን መሄድ ጠቃሚ ነው፡፡
   ጋሜዋ ቻው

   nazrawi
   May 23, 2019 at 10:24 am
   Reply

 3. Now it is clear that the racist NAMA appears with a new name and old Menlikawian political programs. But this group forgets that we are in the ear of the Qeerroos. 

  According to your political programs the Oromo people and other subjugated nations of Ethiopia are going to give up their political achievements of the last 50 years. It is ridiculous. In your primitive mind you have locked afaan Oromoo again in the boxes of the country sides. The wishes of the anti-Oromo elements like the arogant Girma Seifu and the latent racist Angergachew Tsige and their friends are now on a table. They want to decide the fate of afaan Oromoo by referendum. What is about Amharic? Who have decided Amharic as a national language of Ethiopia? Was it decided by referendum?  With this bold and naive assertion you are going to play with fire. Such maneuver will eliminate not only  your programs which is anti-Oromo and full of latent racism, but also yourself.

  Your political programs reflect for which values your organization standards. The individuals in this group are the neo-nazist of Ethiopia. You want to take back the Oromo and oromia about 100 years to the era of your ghost grand father,  Menilik. But you have forgotten who has given you the freedom of coming together. You have forgotten who set you free from the bondage of the TPLF.

  You are supported by ultranationalists like Dawit Woldegeorgies and Eskinder Nega. But it is futile. You are only tiger on paper and other media.

  Dawit Woldegeorgies is one of  the worst racists and anti-Oromo elements. He has been approaching the Oromo politicians and intellectuals in the last couple of years, in order to convince them his malicious strategies. I think all of the Oromo politicans have ignored his deceptive strategies. That is why he has strated desperately and hopelessly barking like a greedy dog. 

  Dawit has been scheming day and night a plan of instigating violences in Ethiopia, so that the formation of a transitional government maybe realized. Thereby, his main objective is helping the ultra nationalists of the Amahara, so that they can overtake political powers during the transitional period and can change the Ethiopian constitution, the current federal structures and make everything retrogressive.

  The ultranationalists of the Amahara like Dawit Woldegeorgies are always sick. Their mind setup is based on blaming others for the problems they have created. Dawit tried to sell the problems which have been created by the members of the National Movement of the Amahara (NAMA) as if it was caused by external forces. 

  For all these chaos are only the racist  neo- nazist organization NAMA and its associates responsible. The stubbornness and arrogance of these bunch of individuals will be punished soon all over Ethiopia.

  Here are the slogans of the neo-nazist organization NAMA, just to mention a few:

  – The Amahara  people will be back to its superiority!
  – Most part of Oromia belongs to  the Amahara people 
  – Amahara people must be worshiped as a creator of Ethiopia.
  – The Shewa Oromoo are not Oromo, they are Oromizied Amhara.
  – The Amahara are the best nation in the world.
  – All peoples in Amhara region (Oromo, Agawo, Kimanti, Wayito and Argoba) are Amahara weather they like it or not.
  – Amaharanism is like sprite.  Ever kids in Ethiopia goes to school, in order to behave like Amhara or to become Amhara. 

  Keep on your illusions! No more scramble for Oromia and the southern peoples of Ethiopia. The Walayita people has told you clearly two days ago. The Sidama and Hadiya peoples have been telling for many years.

  By the  way what is their mission  when they preach about the causes of the political conflicts in Ethiopia. They tell us always as the main causes the politics of ethnicity (YEZER POLITIKA). Is it new for them? Since the formation of the new Ethiopian state about 140 years ago, we have  been experiencing and suffering under the worst ethnic politics which are full of psychological war on different cultures and languages, degradation of human values and latent discrimination. 

  The worst ethnic politicans are those like this group who are working day and night against the democratic rights of the differet nations in Ethiopia. They have been using always derogatory terminologies in order to undermine the demands of the Oromo, the Somali, the Afar, the Sidama and all other nations. Such efforts are futile. If we will not solve our problems step by step, we can jeopardize our common existence. Our other main problem is the malicious politics of the hatemongers and greedy politicians.

  Gamadaa
  May 19, 2019 at 1:53 am
  Reply

 4. ይህ ከላይ የተቀመጠው አንድ የፖለቲካ ድርጅት የተግባር ወይንም የፖለቲካ ፕሮግራም ነው ። ድርጅቱ ሥልጣን ብይዝ ይህንን እተግብረዋለሁ ብሎ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አማራጭ ይዞ ቀርቧል ። ሕዝባችን ድግሞ ከሚቀርቡ አማራጮች ይበጀኛል ያለውን የመምረጥ መብት ካለው ቀድሞ መሳደብና መፍራትን ምን አመጣው ። ፕሮግራሙ እንዳላችሁት ቆሻሻ ከሆነ የቆሸሹ ናቸው ያላችኋቸውን ነጥቦ ነቅሳችሁ በማውጣት መተቸት ሲቻል መሳደብ ያላዋቅነት መገለጫ መሆኑን ለምን ዘነጋችሁ ወገኖቼ። ሌላው ቀርቶ ኦሮሞን እንኳ የሸዋና የሸዋ ያልሆነ ስትሉ እንዴት አታፍሩም ። በወጣቱ ስም የሚነግዱትን የለውጥ እንቅፋቶችን ጨምራችሁ በጅምላ ቄሮ፣ፋኖና ወዘተ ስትሉ አለማፈራችሁ አስገራሚ ነው። ጎበዝ የሆነ ሃሳብን በሃሳብ ሞግቶ የሚያሳምን ወይንም የሚያሸንፍ እንጂ በ21ኛ ክፍለዘምን በጉልበት ድርሽ ትልና እንተያያለን ብሎ በማስፈራራት አይደለም ።

  Zegeyedelu
  May 19, 2019 at 1:07 pm
  Reply

 5. John Smith,
  I agree with you 100% anything that includes the vagabond Birhanu Nega is dead on arrival. Remember he is a hired agent to benefit his handlers not Ethiopia.

  Gammada,
  As usual you are swimming in inferiority complex as if anyone cares. Keep it up until you have a brain anyurism.

  Zegeyedilu,
  You are a Birhanu foot soldier and we can smell people like you from afar. Since when Birhanu Nega discussed with real people? He is always sabotaging every organization he joined. For your info this one is his eighth organization. Dumb people learn from their own mistake while smart people learn from other people’s mistake. In other words fool me once shame on you, fool me twice shame on me. Go sell your blah blah somewhere else. Chew on this.

  Mebirr
  May 20, 2019 at 12:46 am
  Reply

 6. ክፍል አንድ ላይ እንደተገለፀው፣

  ፖሊሲው እንደአጠቃላይ ጥሩ ይመስላል ግን ለህዝብ ውይይት ሲቀርብ ሊዳብር ይችላል፡፡ ቀጠይ ክፍሉም የሚታይ ቢሆንም፡፡

  አንድ አንድ ሃሳብ ሰጪዎች ግን ምን አገባቸው ፓርቲው ያዋጣኛል ያለውን ሃሳብ ይዞ ቢቀርብ ፍርዱ የህዝብ ነው፡፡ አወቅን ለማለት መቀባጠር አያስኬድም ታዲያ በናንተ ሃሳብ አገሮችን ይህቺ መቼ ነው ወደ ዲሞክራሲ መንገድ ልትጓዝ የምትችለው? ሌላ 100 ዓመት? ሃሳብን ማጥበብ አያስፈልግም፡፡ Stop for dump idea & comment!!
  አማርኛ እና ሌላ ቋንቋ በህዝብ ምርጫ ብሔራዊ ቋንቋ መሆኑ ምንም ችግር የለውም፡፡ ምሳሌ ከናዳ እና ፈርንሳይ አገሮች ፈረንሳይኛና ኢንግሊዘኛ፣ እንግሊዝ ኢንግሊዘኛ ብሔራዊ ቋንቋ ሌሎችም፡፡

  ሌላው የኢዜማ ፕሮግራም ላይ የሚከተሉትን አስተያየቶች ብትመለከቱት ሃሳቡ ዋናው ሃሳብ ላይ እንዲሁም በመጨረሻ ሀሳብ ላይ ተቀምጧል፡፡

  1.5.3. የመከላከያ፣ የደህንነት እና የፖሊስ ተቋማት መንግስት በተቀያየረ ቁጥር የማይቀያየሩ እንደተቋም ቋሚ ሆኖ የመቀጠል ዋስትና እንዲኖራቸው እና ፍፁም በኢትጵያዊ ዜግነት ላይ የተገነበ ተቋም እንዲሆን ከማንኛውም ፖለቲካዊ ፓርቲ ወገንተኝነት የራቁ ተቋማት እንዲሆኑ ይደረጋል፤

  2.2.2. ሰፋፊ እርሻዎች እንዲስፋፉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ ሲሆን፣ በኩታ ገጠም ያሉ በአነስተኛ ማሣ ላይ ያሉ አርሶ አደሮች በትብብር እንዲያለሙ ማበረታቻ ይሰጣቸዋል ወይም በተጠና መልኩ የአክሲዮን ድርሻ እንዲኖራቸው ያደርጋል፡፡

  2.5.3. ዜጎች መሬትን በግል ይዞታነት በባለቤትነት መያዝ፣ ማከራየት፣ መግዛት መሸጥና መለወጥ የሚችሉበት ምቹ ሁኔታ ይፈጠራል፡፡
  ይህ ጉዳይ የለየለት ባለሃብት ወይም Pure monopoly ተፈጥሮ በርካታ ደሃ እንዳይፈጠር በደንብ መታየት አለበት፡፡
  2.8. የፋይናንስ እና የባንክ የአገልግሎት
  ስለ ውጭ ምንዛሪ ምንጭና አጠቃቀም አልተጠቀሰም ሆኖም ከባድ ችግር ያለው እዚህ ላይ ነው፡፡

  3.7. ወጣቶች
  በሀገራችን የሚታየው የወጣት ስራ አጥነት በግልፅ የሚያመለክተው፤ አገሪቱ ያላትን ወሣኝ የእድገት ምንጭ በአግባቡ መጠቀም ያለመቻሏን ነው፡፡ ይህን እምቅ የእድገት ምንጭ የሆነውን የወጣት ሀይል አሟጦ ለመጠቀም እንዲቻል፤ ይልቁንም ወጣቱን ከወላጆቹ ጋር በተጣበበ የግብርና መሬት ላይ የሚያደርገውን የመሬት ቅርምት በማላቀቅ ከግብርና ውጭ ባሉ የስራ እድሎች ተሣታፊ ለማድረግ የተቀናጀ የከተማ ልማት ስትራቴጂዎች ይቀረፃሉ፡

  ወጣቱን ከገባበት መጥፎ ሱስ ለማወጣት መደረግ ስላለበት ፖሊሲ በጥቅሉ ቢጠቀስ፡፡

  Yetesfa Chilanchele
  May 20, 2019 at 1:02 pm
  Reply

 7. የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ፕሮግራም እይታ – በወፍ በረር

  <> ወይስ <>

  ከስሙ በመነሳት የኢዜማ ትኩረት ዜግነትና ማህበራዊ ፍትህ መሆናቸውን መገመት ይቻላል። ይህም ቢባል ስለፓርቲው ምንነት በበቂ ሁኔታ ለመረዳት ከሁለቱ ጠቋሚ ቃላት በዘለለ ፕሮግራሙን በሙሉ ማንበብ ያስፈልጋል። እኔ ከዚህ ማህበራዊ ገጽ ላይ አግኝቼ አንብቤዋለሁ። እውነት ለመናገር እንደጠበኩት አይደለም። ላስረዳ።

  ኢዜማ <> የሚለውን መሰረታዊ ሃሳብ ያነሳው የ<> ፖለቲካን እንደማይቀበል ለማሳየት መስሎኝ ነበር። ፕሮግራሙን ሳየው ግን ያገኘሁት ተቃራኒውን ነው:: የሚከተለውን ከፕሮግራሙ በቀጥታ የተወሰደ ክፍል እንመልከት::

  <>

  ይህ <> ያልተጠበቀ አይደለም። ኢዜማ ምርጫ አደርግሁ ይበል እንጂ ከፌደራሊዝም ሌላ ምርጫ አልነበረውም። ዋናው ጥያቄ ግን ምን አይነት ፌዴራሊዝም የሚለው ነው። ከላይ ያየነው ጥቅስ ይህን ጥያቄ አይመልስም። ይህ ማለት ግን ኢዜማ ሊያቆመው የሚፈልገውን የፌዴራላዚም አይነት በፖለቲካ ፕሮግራሙ ውስጥ አልገልጸም ማለት አይደለም። በጉዳዩ ላይ የሚከተለውን ይላል።

  <>

  አንደገባኝ ከሆነ በስራ ላይ ያለው ህገመንግስት ፌደራሊዝምን ያዋቀረው በ<> አስፋፈር ላይ ስለሆነ የተባለው የሕገ መንግሥ ት ማሻሻያ የሚደረገው በዚሁ ህገመንግስት ላይ ነው ማለት ነው።

  ኢዜማ ያለውን ህገመንግስት መቀበሉ ጥሩ ጅምር ነው። ያለውን ማሻሻል አንጂ ከዚህ በፊት በሰፊው ይባል አንደነበረው በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ተቀባይነት ያለውን ሀገመንግስት አንዳለ ለመተካት መስራት ጊዜና ጉልበት ከማባከን በተረፈ ግጭትን ባባባሰ ነበር። ህገመንግስቱን መቀበል ከህገመንግስቱ ደጋፊዎች ጋር ለመነጋገር፥ ለመደማምጥ፥ አምኖ ለማሳመንና አቅዋም ለማስለወጥ እንዲሁም አብሮ ለመስራት በር ይከፍታል። ይህ ደግሞ መበረታታት ያለበት ተግባር ነው::

  ከላይ 1.1.1. ስር የሰፈረው <> የሚለው በተቃራኒው ይሁን አይሁን ወይም ሁለቱም በአንድ ጊዜና ቦታ ሊከበሩ የሚችሉ ወይም የተለያዩ መብቶች ይሁኑ አይሁኑ ብዙ የንድ ፈሃሳብ ክርክርና ውይይት የተደረገባቸው ወደፊትም ሊደረጉባቸው የሚችሉ ጉዳዩች ናቸው። ይህ አንድ ሰፊ ጥናት ተደርጎበት ለማስተማሪያነትና ለማጣቀሻነት የሚያገለግል ሰነድ ሊዘጋጅበት የሚችል ነገር ነው። ለእንደዚህ አይነት ስራ ኢዜማ አንድ የምሁራን ቡድን ሳያስፈልገው አይቀርም።

  አሁንም አንደገባኝ ከሆነ የኢዜማ ፍላጎት <> ላይ ያልተመሰረተ ፌዴራሊዚም ማቆም ነው። ይህ ከሆነ በ1.2.1 ስር <> የሚለውን ምን አመጣው?

  ኢዜማ <> የሚለው ምንን እንደሆነ ግልጽ አስካላደርገ ድረስ በስራ ላይ ያለው ህገመንግስት <> ያላቸውን መሆኑን መገመት ይቻላል። ህገመንግስቱ <> ያላቸውን በአንቀጽ 39 (5) ስር ይተረጉማል።
  ትርጉሙ አንደሚከተለው ይነበባል።

  “ሰፋ ያለ የጋራ ጠባይ የሚያንጸባርቅ ባህል ወይም ተመሳሳይ ልምድ ያላቸው፣ ሊግባቡበት የሚችሉበት የጋራ ቋንቋ
  ያላቸው፣ የጋራ ወይም የተዛመደ ህልውና አለን ብለው የሚያምኑ፣ የሥነ ልቦና አንድነት ያላቸውና ባአብዛኛው
  በተያያዘ መልክዓ ምድር የሚኖሩ ናቸው

  ሙሉ ለሙሉም ባይሆን ከላይ በቁጥር 1.2.1. ስር የሰፈረው የኢዜማ የአስተዳደር አካባቢዎች መርሆዎች <> አስካነሳ ድረስ በስራ ላይ ካላው ህገመንግስት አንቀጽ 39 (5) ዝርዝር ጋር የሚጋራው ብዙ ነገር አለ። ይህም የ<> ክልላዊ አደረጃጀት በመቀበል ነው። ይህ ከሆነ የ<> ላይ ላልተመሰረተ ፌደራሊዝም አንሰራለን የሚባለው ምንድነው?

  ችግሩ ያለው ህገመንግስቱ ያቆመው በ<> ላይ የተመሰረተ ህገ መንግስት የፈጠረውን ሃገራዊ ጉዳት በፖለቲካ ሃኪምነት አናድናለን በሚል ጉዳት ያሉትን ሀገመንግስት አንዳለ ይዘው ያለውን ጉዳት የሚያባብስ ተጨማሪ አደረጃጀቶ ማምጣታቸው ነው። አነዚህም <> የተባሉት ናቸው።

  እግዚኣብሄር ያሳያችህ! በ<> የተዋቀረን ፌደራሊዝም በሚገባ መምራት አቅቶን አየተንገዳገድን ይሀ ፌደራሊዝም አንዳለ ሆኖ ሌሎች አምስት ወይም ስድስት አዲስ የፌደራሊዝም አደረጀጀቶች አክለንበት ተያይዘን ገደል ስንገባ። እነዚህ ተጫማሪ የተባሉ የፌደራሊዝም አደረጃጀቶች እየተዳከመ ያለውን ሃገራዊ መግባባት አጥፍተው በማን አንሼነት ማለቂያ የሌለው ሃገር አቀፍ የማያስፈልግ አተካራና ፍትጊያ በመጨረሻም የሃገርን መፍረስ የሚያስክትሉ ናቸው። እንዲያው ለነገሩ ማን ነው በየትኛው አደረጃጀት ስር የሚገባው? ይህንንስ የሚወስነው ማነው? እንዴትስ ተግባራዊ ይሆናል? በማን? ያልተመለሱ ምናልባትም ሊመለሱ የማይችሉ ጥያቄዎች ይሆናሉ።

  በነገራችን ላይ የቤልጅም ብሄርተኞችን እያወዛገበ ሀገሪቱንም ለማፍረስ በቋፍ ያደረሳት በቋንቋ ፌደራሊዝም ላይ የተጨመሩ ሁለት ማለትም የመሬት አቀማመጥ (ጂኦግራፊያዊና) ማህበረሰባዊ (ኮሙኒቲ) አደረጃጀቶች ናቸው:: ከዚሁ ውዝግብ የተነሳ ቤልጅም ውስጥ አንድ ም እንኳ ሃገራዊ ፓርቲ መመስረት አልተቻለም:: ይህ ብቻ አይደለም – ብሐራዊ ሚዲያ የለም:: ሃገር አቀፍ ምርጫ ተደርጎ መንግስት ለማቆም ችግር ይፈጠራል:: ከምርጫ በኋላ ያለሃገራዊ መንግስት ከአምስት መቶ ቀናት በላይ በመቆየት ቤልጀም ርከርድ ይዛላች:: እኛስ የምንፈለገው እንደቤልጀም መሆን ነው:: አስቡት! ከሰማንያ በላይ ብሄር ብሄረሰብ ባላበት ሃገር የተወሳሰበ ሌላ ፌደራላዊ አደረጃጀት ጨምረብነት የት እንደምንደርስ!

  ኢዜማ በዘር የተመሰረተ ፌዴራላዊ አስተዳደር አልቀበልም – ፕሮግራሜም ተዛብቶ የ<> ፌደራሊዝም አንደምደግፍ ተደርጎ ቀርቦአል የሚል ቢሆን ተጨማሪ መረጃዎች እናቅርብ።

  በፕሮግራሙ 1.3 ስር አሁን በስራ ላይ ያለው ህገ መንግስት ያቆመው የፌደሬሽን ምክር ቤት ያለስም ለውጥ አንደሚኖር እንደሚከተለው ተገልጻል።

  <>

  እዚህ ላይ ፍላጎታችን የምክር ቤቱን አዲስ ስልጣን መመርመር ሳይሆን እንደ ተቋም በአስተዳደርዊ ክልል የሚገኙ <> የሚወከሉበት መሆኑን ማሳየት ብቻ ነው ። ባጭሩ አሁን አእንዳለው የፌደሬሽን ምክር ቤት የ<> ቤት ነው ማለት ነው። ይህ የሚያሳየው ኢዜማ የ<> ፌደራሊዝም አራማጅ መሆኑን ነው:: ይህ ከሆነ አሁን ያለውን ፈደራሊዝም የ<> ምናምን እያለ ማጣጣሉ ትርጉም የለውም። ይባስ ብሎ ሌሎች ተጨማሪ አደረጃጀቶች ይዞ ብቅ ማለቱ አሳሳቢ ችግር ነው።

  ይህ ብቻ አይደለም:: አሁን ያለው ህገመንግስት የተቀበለውን ህዝበ ውሳኔ እንደዋነኛ መሳሪያነት እንደሚጠቀምበት በተላይዩ የፕሮግራሙ ክፍሎች ጠቁሟል:: የ<> የሚቀበል እንደምሆኑ መጠን የመገንጠል ህዝበ ውሳኔንም ይቀበላል ማለት ነው:: ይህ ደግሞ በ 1.1.6. ስር ከሰፈረው ” የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት ሊገሰስ የማይችልና የማይገሰስ መሆኑን” ከሚገልጸው በቀጥታ ይጋጫአል:: <> እና ህዝበ ውሳኔን ተቀብሎ ስለሀገራዊ የግዛት አንድነት ማውራት አይቻልም::

  ኢዜማ የ<> ፌደራሊዝም አራማጅ እስከሆነና ህዝበ ውሳኔ እስከተቀበለ ድረስ በፕሮግራሙ ውስጥ የጠቀሰው የህገመንግስት ማሻሻል አያስፈልገውም። የቡድንና የወል መብቶች ከግለሰብ መብቶች የሚመነጩም ሆኑ አልሆኑ መብቶቹ ከላይ በቀረበው አይነት ህገመንግስታዊ ተቀባይነት ካገኙ ከብሄርተኞች ጋር ያለው የአደረጃጀት ልዩነት አውነትም ልዩነት አይደለም ማለት ነው። የዜጋ ፖለቲካ የሚባውም ቱሻ ነው ማለት ነው።

  ኢዜማ <> የተደራጀ ፌደራሊዝምን እስከ ህዝበ ውሳኔ ስለሚቀበል ይህን ፖለቲካ የ<> ፖለቲካ – የመስመሩን አራማጆችን ደግሞ የ <> ፖለቲከኞች አያለ መጥራት አይኖርበትም። አመራሩም ሆነ አባላቱ አነዚህን ቃላት ክመጠቀም ተቆጥበው ፖለቲካውን የብሄር ፖለቲካ አራማጅቹን ደግም ብሄርተኞች ሊሏቸው ይገባል ባይ ነኝ። አለበለዚያ የአስተሳሰብ ወጥነት የጎደለውና እምነት ሊጣልበት የማይችል ድርጅት ተደርጎ ሊታይ ይችላል።

  ይቀጥላል።

  Dinaw Demissie ወይስ
  May 21, 2019 at 12:45 pm
  Reply

 8. Corrected

  የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ፕሮግራም እይታ – በወፍ በረር

  “ቤት ለምቦሳ ፥ እምቦሳ እሰሩ” ወይስ ”ያው በገሌ”

  ከስሙ በመነሳት የኢዜማ ትኩረት ዜግነትና ማህበራዊ ፍትህ መሆናቸውን መገመት ይቻላል። ይህም ቢባል ስለፓርቲው ምንነት በበቂ ሁኔታ ለመረዳት ከሁለቱ ጠቋሚ ቃላት በዘለለ ፕሮግራሙን በሙሉ ማንበብ ያስፈልጋል። እኔ ከዚህ ማህበራዊ ገጽ ላይ አግኝቼ አንብቤዋለሁ። እውነት ለመናገር እንደጠበኩት አይደለም። ላስረዳ።

  ኢዜማ ”ዜግነት” የሚለውን መሰረታዊ ሃሳብ ያነሳው የ”ዘር”ፖለቲካን እንደማይቀበል ለማሳየት መስሎኝ ነበር። ፕሮግራሙን ሳየው ግን ያገኘሁት ተቃራኒውን ነው:: የሚከተለውን ከፕሮግራሙ በቀጥታ የተወሰደ ክፍል እንመልከት::

  ”የኢዜማ የፖለቲካ ፕሮግራም በወሳኝ መልኩ ያልተማከለ አስተዳደር (ፌዴራላዊ) ሥርዓትን መከተለን ምርጫው ያደረገ ነው፡፡”

  ይህ ”ምርጫ” ያልተጠበቀ አይደለም። ኢዜማ ምርጫ አደርግሁ ይበል እንጂ ከፌደራሊዝም ሌላ ምርጫ አልነበረውም። ዋናው ጥያቄ ግን ምን አይነት ፌዴራሊዝም የሚለው ነው። ከላይ ያየነው ጥቅስ ይህን ጥያቄ አይመልስም። ይህ ማለት ግን ኢዜማ ሊያቆመው የሚፈልገውን የፌዴራላዚም አይነት በፖለቲካ ፕሮግራሙ ውስጥ አልገልጸም ማለት አይደለም። በጉዳዩ ላይ የሚከተለውን ይላል።

  ”1.1.1. ኢዜማ የሕገ መንግሥት ማሻሻያ መደረግ አለበት ብሎ ያምናል፡፡ሕገ መንግስቱ የግለሰብ መብትን የመብቶች ሁሉ የማእዘን ድንጋይ አድርጎ እንዲወስደው፣ የቡድንና የወል መብቶች ከግለሰብ መብቶች የሚመነጩ መሆናቸውን የሚቀበል፣በዘር ወይም በእምነት ላይ ያልተመሰረተ፣ ያልተማከለ ፌዴራላዊ አስተዳደር እንዲኖር ይስራል”

  አንደገባኝ ከሆነ በስራ ላይ ያለው ህገመንግስት ፌደራሊዝምን ያዋቀረው በ”ብሄር ፥ ብሄረሰቦችና ህዝቦች” አስፋፈር ላይ ስለሆነ የተባለው የሕገ መንግሥ ት ማሻሻያ የሚደረገው በዚሁ ህገመንግስት ላይ ነው ማለት ነው።

  ኢዜማ ያለውን ህገመንግስት መቀበሉ ጥሩ ጅምር ነው። ያለውን ማሻሻል አንጂ ከዚህ በፊት በሰፊው ይባል አንደነበረው በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ተቀባይነት ያለውን ሀገመንግስት አንዳለ ለመተካት መስራት ጊዜና ጉልበት ከማባከን በተረፈ ግጭትን ባባባሰ ነበር። ህገመንግስቱን መቀበል ከህገመንግስቱ ደጋፊዎች ጋር ለመነጋገር፥ ለመደማምጥ፥ አምኖ ለማሳመንና አቅዋም ለማስለወጥ እንዲሁም አብሮ ለመስራት በር ይከፍታል። ይህ ደግሞ መበረታታት ያለበት ተግባር ነው::

  ከላይ 1.1.1. ስር የሰፈረው “የቡድንና የወል መብቶች ከግለሰብ መብቶች የሚመነጩ መሆናቸው” የሚለው በተቃራኒው ይሁን አይሁን ወይም ሁለቱም በአንድ ጊዜና ቦታ ሊከበሩ የሚችሉ ወይም የተለያዩ መብቶች ይሁኑ አይሁኑ ብዙ የንድ ፈሃሳብ ክርክርና ውይይት የተደረገባቸው ወደፊትም ሊደረጉባቸው የሚችሉ ጉዳዩች ናቸው። ይህ አንድ ሰፊ ጥናት ተደርጎበት ለማስተማሪያነትና ለማጣቀሻነት የሚያገለግል ሰነድ ሊዘጋጅበት የሚችል ነገር ነው። ለእንደዚህ አይነት ስራ ኢዜማ አንድ የምሁራን ቡድን ሳያስፈልገው አይቀርም።

  አሁንም አንደገባኝ ከሆነ የኢዜማ ፍላጎት “በዘር” ላይ ያልተመሰረተ ፌዴራሊዚም ማቆም ነው። ይህ ከሆነ በ1.2.1 ስር “የአስተዳደር አካባቢዎች አወቃቀር መርሆዎች — መልከአ ምድራዊ አቀማመጥን፣ የሕዝብ አሰፋፈር ለአጠቃላይ አስተዳደራዊና ለልማት ሥራዎች አመቺነትን፤ ቋንቋ፤ ባህል፥ ስነልቦናዊ ቁርኝት እና ታሪክን፤ የሃብት ስብጥርና ፍትሃዊነት
  ለብሔራዊ መግባባት አመቺ ሁኔታ መፍጠርን፤ መሠረት ባደረገ ሁኔታ ይሆናል” የሚለውን ምን አመጣው?

  ኢዜማ “ዘር” የሚለው ምንን እንደሆነ ግልጽ አስካላደርገ ድረስ በስራ ላይ ያለው ህገመንግስት “ብሄር፥ ብሄረሰብና ህዝቦች” ያላቸውን መሆኑን መገመት ይቻላል። ህገመንግስቱ “ብሄር፥ ብሄረሰብና ህዝቦች” ያላቸውን በአንቀጽ 39 (5) ስር ይተረጉማል።
  ትርጉሙ አንደሚከተለው ይነበባል።

  “ሰፋ ያለ የጋራ ጠባይ የሚያንጸባርቅ ባህል ወይም ተመሳሳይ ልምድ ያላቸው፣ ሊግባቡበት የሚችሉበት የጋራ ቋንቋ
  ያላቸው፣ የጋራ ወይም የተዛመደ ህልውና አለን ብለው የሚያምኑ፣ የሥነ ልቦና አንድነት ያላቸውና ባአብዛኛው
  በተያያዘ መልክዓ ምድር የሚኖሩ ናቸው”

  ሙሉ ለሙሉም ባይሆን ከላይ በቁጥር 1.2.1. ስር የሰፈረው የኢዜማ የአስተዳደር አካባቢዎች መርሆዎች “ቋንቋን፤ ባህልን፥ስነልቦናዊ ቁርኝት እና ታሪክን” አስካነሳ ድረስ በስራ ላይ ካላው ህገመንግስት አንቀጽ 39 (5) ዝርዝር ጋር የሚጋራው ብዙ ነገር አለ። ይህም የ”ብሄር፥ ብሄረሰብና ህዝቦች” ክልላዊ አደረጃጀት በመቀበል ነው። ይህ ከሆነ የ<> ላይ ላልተመሰረተ ፌደራሊዝም አንሰራለን የሚባለው ምንድነው?

  ችግሩ ያለው ህገመንግስቱ ያቆመው በ”ብሄር፥ ብሄረሰብና ህዝቦች” ላይ የተመሰረተ ህገ መንግስት የፈጠረውን ሃገራዊ ጉዳት በፖለቲካ ሃኪምነት አናድናለን በሚል ጉዳት ያሉትን ሀገመንግስት አንዳለ ይዘው ያለውን ጉዳት የሚያባብስ ተጨማሪ አደረጃጀቶ ማምጣታቸው ነው። አነዚህም “መልከአ ምድራዊ አቀማመጥ፣ የሕዝብ አሰፋፈር ለአጠቃላይ አስተዳደራዊና ለልማት ሥራዎች አመቺነትን፤ . . . የሃብት ስብጥርና ፍትሃዊነት ለብሔራዊ መግባባት አመቺ ሁኔታ መፍጠር” የተባሉት ናቸው።

  እግዚኣብሄር ያሳያችህ! በ”ብሄር፥ ብሄረሰብና ህዝቦች” የተዋቀረን ፌደራሊዝም በሚገባ መምራት አቅቶን አየተንገዳገድን ይሀ ፌደራሊዝም አንዳለ ሆኖ ሌሎች አምስት ወይም ስድስት አዲስ የፌደራሊዝም አደረጀጀቶች አክለንበት ተያይዘን ገደል ስንገባ። እነዚህ ተጫማሪ የተባሉ የፌደራሊዝም አደረጃጀቶች እየተዳከመ ያለውን ሃገራዊ መግባባት አጥፍተው በማን አንሼነት ማለቂያ የሌለው ሃገር አቀፍ የማያስፈልግ አተካራና ፍትጊያ በመጨረሻም የሃገርን መፍረስ የሚያስክትሉ ናቸው። እንዲያው ለነገሩ ማን ነው በየትኛው አደረጃጀት ስር የሚገባው? ይህንንስ የሚወስነው ማነው? እንዴትስ ተግባራዊ ይሆናል? በማን? ያልተመለሱ ምናልባትም ሊመለሱ የማይችሉ ጥያቄዎች ይሆናሉ።

  በነገራችን ላይ የቤልጅም ብሄርተኞችን እያወዛገበ ሀገሪቱንም ለማፍረስ በቋፍ ያደረሳት በቋንቋ ፌደራሊዝም ላይ የተጨመሩ ሁለት ማለትም የመሬት አቀማመጥ (ጂኦግራፊያዊና) ማህበረሰባዊ (ኮሙኒቲ) አደረጃጀቶች ናቸው:: ከዚሁ ውዝግብ የተነሳ ቤልጅም ውስጥ አንድ ም እንኳ ሃገራዊ ፓርቲ መመስረት አልተቻለም:: ይህ ብቻ አይደለም – ብሐራዊ ሚዲያ የለም:: ሃገር አቀፍ ምርጫ ተደርጎ መንግስት ለማቆም ችግር ይፈጠራል:: ከምርጫ በኋላ ያለሃገራዊ መንግስት ከአምስት መቶ ቀናት በላይ በመቆየት ቤልጀም ርከርድ ይዛላች:: እኛስ የምንፈለገው እንደቤልጀም መሆን ነው:: አስቡት! ከሰማንያ በላይ ብሄር ብሄረሰብ ባላበት ሃገር የተወሳሰበ ሌላ ፌደራላዊ አደረጃጀት ጨምረብነት የት እንደምንደርስ!

  ኢዜማ በዘር የተመሰረተ ፌዴራላዊ አስተዳደር አልቀበልም – ፕሮግራሜም ተዛብቶ የ”ብሄር፥ ብሄረሰብና ህዝቦች” ፌደራሊዝም አንደምደግፍ ተደርጎ ቀርቦአል የሚል ቢሆን ተጨማሪ መረጃዎች እናቅርብ።

  በፕሮግራሙ 1.3 ስር አሁን በስራ ላይ ያለው ህገ መንግስት ያቆመው የፌደሬሽን ምክር ቤት ያለስም ለውጥ አንደሚኖር እንደሚከተለው ተገልጻል።

  “የፌዴራሽን ምክር ቤቱ በአስዳደር አካባቢዎች በእኩል የሚወከሉበት እና የአስተዳደር አካባቢዎች በሚኖራቸው ብሔረሰቦች ብዛት አነስተኛ ቁጥር ላላቸው ብሔረሰቦች ተጨማሪ ውክልና የሚሰጥ ሆኖ አስፈላጊው ድጋፍ እንዲያገኙ ህጎችን የማመንጨት፤ ሕጎችን የመገምገም፤ አፈፃፀማቸውን የመከታተል ሃላፊነት ይኖርበታል፡፡”

  እዚህ ላይ ፍላጎታችን የምክር ቤቱን አዲስ ስልጣን መመርመር ሳይሆን እንደ ተቋም በአስተዳደርዊ ክልል የሚገኙ <> የሚወከሉበት መሆኑን ማሳየት ብቻ ነው ። ባጭሩ አሁን አእንዳለው የፌደሬሽን ምክር ቤት የ”ብሄረሰቦች” ቤት ነው ማለት ነው። ይህ የሚያሳየው ኢዜማ የ”ብሄር፥ ብሄረሰብና ህዝቦች” ፌደራሊዝም አራማጅ መሆኑን ነው:: ይህ ከሆነ አሁን ያለውን ፈደራሊዝም የ”ዘር” ምናምን እያለ ማጣጣሉ ትርጉም የለውም። ይባስ ብሎ ሌሎች ተጨማሪ አደረጃጀቶች ይዞ ብቅ ማለቱ አሳሳቢ ችግር ነው።

  ይህ ብቻ አይደለም:: አሁን ያለው ህገመንግስት የተቀበለውን ህዝበ ውሳኔ እንደዋነኛ መሳሪያነት እንደሚጠቀምበት በተላይዩ የፕሮግራሙ ክፍሎች ጠቁሟል:: የ”ብሄር፥ ብሄረሰብና ህዝቦች ፌደራሊዝም” የሚቀበል እንደምሆኑ መጠን የመገንጠል ህዝበ ውሳኔንም ይቀበላል ማለት ነው:: ይህ ደግሞ በ 1.1.6. ስር ከሰፈረው ” የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት ሊገሰስ የማይችልና የማይገሰስ መሆኑን” ከሚገልጸው በቀጥታ ይጋጫአል:: “ብሄር፥ ብሄረሰብና ህዝቦች ፌደራሊዝም” እና ህዝበ ውሳኔን ተቀብሎ ስለሀገራዊ የግዛት አንድነት ማውራት አይቻልም::

  ኢዜማ የ”ብሄር፥ ብሄረሰብና ህዝቦች” ፌደራሊዝም አራማጅ እስከሆነና ህዝበ ውሳኔ እስከተቀበለ ድረስ በፕሮግራሙ ውስጥ የጠቀሰው የህገመንግስት ማሻሻል አያስፈልገውም። የቡድንና የወል መብቶች ከግለሰብ መብቶች የሚመነጩም ሆኑ አልሆኑ መብቶቹ ከላይ በቀረበው አይነት ህገመንግስታዊ ተቀባይነት ካገኙ ከብሄርተኞች ጋር ያለው የአደረጃጀት ልዩነት አውነትም ልዩነት አይደለም ማለት ነው። የዜጋ ፖለቲካ የሚባውም ቱሻ ነው ማለት ነው።

  ኢዜማ “ብሄር፥ ብሄረሰብና ህዝቦች” የተደራጀ ፌደራሊዝምን እስከ ህዝበ ውሳኔ ስለሚቀበል ይህን ፖለቲካ የ”ዘር” ፖለቲካ – የመስመሩን አራማጆችን ደግሞ የ “ዘር” ፖለቲከኞች አያለ መጥራት አይኖርበትም። አመራሩም ሆነ አባላቱ አነዚህን ቃላት ክመጠቀም ተቆጥበው ፖለቲካውን የብሄር ፖለቲካ አራማጅቹን ደግም ብሄርተኞች ሊሏቸው ይገባል ባይ ነኝ። አለበለዚያ የአስተሳሰብ ወጥነት የጎደለውና እምነት ሊጣልበት የማይችል ድርጅት ተደርጎ ሊታይ ይችላል።

  ይቀጥላል።

  Dinaw Demissie
  May 21, 2019 at 12:53 pm
  Reply

 9. ቅራቅንቦ ነው። አማራ ነን ከሚሉት በስተቀር በሌሎች ብሄር ብሄረሰብ ዘንድ ተቀባይነት የለውም።

  Oumar
  May 22, 2019 at 5:05 am
  Reply

 10. ካላፈው የቀጠለ –

  አሁን ደግሞ ኢዜማ የመረጠውን ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት እንመልከት:: ይህን ስናደርግ ኢዜማ እንዲኖር የሚፈልገውን ፌደራላዊ ስርዓት የሚመሰረትበትን ማለትም ”መልከአ ምድራዊ አቀማመጥን፣ የሕዝብ አሰፋፈር ለአጠቃላይ አስተዳደራዊና ለልማት ሥራዎች አመቺነትን፤ ቋንቋ፤ ባህል; ስነልቦናዊ ቁርኝት እና ታሪክን፤ የሃብት ስብጥርና ፍትሃዊነት ለብሔራዊ መግባባት አመቺ ሁኔታ መፍጠርን . . . ” በአዕምርዋችን ይዘን መሆን ይኖርበታል:: ምክንያቱም ለዚህ ዓይነት ፌደራሊዝም የሚሻለው ፕሬዝዳንታዊ ወይስ ፓርላሜንታዊ ስርዓት መሆኑ መነሳቱ ስላማይቀር ነው::

  ኢዜማ በፕሮግራሙ መግቢያ ላይ የሚከተለውን ይላል::

  ” ከፍተኛው የመንግሥት ሃላፊነት በሕዝብ ቀጥታ ምርጫ የሚመረጥ ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት እንዲሆን አበክሮ ይሰራል፡፡ ”

  እርግጥ አሁን በሚሰራበት ህገ መንግስት የተቋቋመው የሀገራችን ፓርላሜንታዊ ስርዓት (አንዳንዶች ድብልቅ ይሉታል – ምክንያቱም ጠቅላይ ሚኒስትርም ፕሬዚዳንትም ስላለው) በሚያስፍር ሁኔታ የህዝብን መብት የረገጠ ነበር:: ፓርላሜንታዊ ስርዓት ኖሯቸው እንደኛ የህዝብን መብት የረገጡ – አሁንም እየረገጡ ያሉ ጥቂት የማይባሉ ሃገሮች አሉ::

  የኛና ጥቂት የማይባሉ ሃገሮች ፓርላሜንታዊ አስተዳደር የህዝብን መብቶች በገፍ ቢጥሱም ተመሳሳይ ፓርላሜንታዊ ስርዓት ያላቸው በርካታ ሃገሮች ግን የህዝቦቻቸውን መብቶች አክብረውና ፍላጎቶቻቸውን በሚገባ አሟልተው አስተዳድረውበታል:: አሁንም እያስተዳደሩበት ይገኛሉ:: ለዚህ ማስረጃው የተዋጣለት ፓርላሜንታዊ ስርዓት የሚከተሉ አውስትራሊያ – ካናዳ – ዴንማርክ – ህንድ – ጀርመን – ፊንላንድ – ጣልያን – ግሪስ -ፖርቹጋል – ስዊዘርላንድ የመሰሉ ሃገሮች መኖራቸው ነው::

  ከላይ እንዳየነው ፓርላሜንታዊ ስርዓት እኛና መሰሎቻቸን መብት ረጋጭ ሃገሮች ስለተቀላቀልነው በራሱ የህዝብን መብቶች ለማክብርም ሆነ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት የማያስችል ስርዓት ነው ወደሚል የተሳሳተ መደምደሚያ እንዳያደርስ መጠንቀቅ ያስፈልጋል::

  የሃገራችን ፓርላሜንታዊ ስርዓትም በዲሞክራሲ፥ በህግ የበላይነትና በጠንካራ ነጻ ሚዲያ ከተሟላ ከላይ እንደተዘረዘሩት ሃገሮች ሊሰራ የማይችልበት ምክንያት አይታየኝም:: ስለሆነም ኢዜማ ፕሬዚዳንታዊ ስርአት ያስፈልጋል ሲል አዲስ የተለየ ነገር ለማምጣት ብቻ ብሎ ያደረገው እንዳይሆን መጠንቀቅ ይኖርበት ይሆናል::

  ዝርዝር ውስጥ መግባት ሳያስፈልግ ”ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት” እንደ ፓርላሜንታዊ ስርዓት የህዝብን መብቶች በሚረግጡ እንዲሁም ፍላጎቱን ማሳካት በተሳናቸው እና መብቶች በማክበር በሚታወቁ ሃገሮች የተሞላ ነው:: ከዚህ አጠቃላይ እውነታ የምንረዳው ስርዓቱን በራሱ የጭቆና አስተዳደርን እንደማያስወግድ ወይም እንደማያመጣ ነው:: እንደ ፓርላሜንታዊው ስርዓት ሁሉ የተሟላ እንዲሆን ዲሞክራሲ፥ የህግ የበላይነትና ጠንካራ ነጻ ሚዲያ ያስፈልገዋል::

  ኢዜማ ‘ ‘ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት” የመረጠበትን ምክንያት ወደፊት በሰፊው እንደሚያስርዳ ይጠበቃል:: ዝም ብሎ ፓርላሜንታዊ ስርዓት አልሰራም – ወይም አይሰራም – ስለሆነም ለውጠን እንሞክረው ሊለን አይችልም:: ጊዜው የሙከራ አይደለምና:: በተለይ ዲሞክራሲና የህግ የበላይነት በሃገሪቱ ከሰፈነና ጠንካራ ነጻ ሚዲያ ከተፈጠረ እየተለመደ ከመጣው ከፓርላሜንታዊ ስርዓት በመውጣት ወደ ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት መሄድ ለምን እንደሚያስፈልግ በበቂ ሁኔታ ማሳየት ይኖርበታል::

  ይህ ብቻ አይደለም። ኢዜማ የሚፈልገው ‘ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት” በስራ የሚተርጎመው በፌደራላዊ ሃገር በመሆኑሥርዓቱ ተሞክሮ ከነበረው ፓርላሜንታዊ ስርዓት የተሻለ ውጤት እንደሚያስገኝ በቅድሚያ ማረጋገጥ ይስፈልጋል። ዲሞክራሲ፥ የህግ የበላይነትና ጠንካራ ነጻ ሚዲያ ባልነበረበት ሁኔታ በሀገራችን የተሞከረው ፓርላሜንታዊ ስርዓት የፈጠረው የጭቆና አስተዳደር ነው። እነዚህ ችግሮች ከተወገዱ ያለውን ፓርላሜንታዊ ስርዓት በማስቀጠል የተሻለ ውጤት ማግኘት እንደሚቻል መገመት በአግባቡ ነው። አውስትራሊያ – ካናዳ – ኔዘርላንድስ – ጀርመን – ስዊዘርላንድ የተዋጣለት ፓርላሜንታዊ ና ፌደራላዊ ሃገሮች ናቸው።

  ዲሞክራሲ፥ የህግ የበላይነትና ጠንካራ ነጻ ሚዲያ ባለበት ፓርላሜንታዊ ስርዓት በአጥጋቢ ሁኔታ እንደሚሰራ ሁሉ ‘ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት’ም” ዲሞክራሲ፥ የህግ የበላይነትና ጠንካራ ነጻ ሚዲያ ባለበት በሚገባ ይሰራል።ፓርላሜንታዊ ስርዓትን በሚመለከት እንዳኩት ‘ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓትም” በሃገራችን ፌደራልዝምን ለመተግበር ተስማሚነቱ በጥልቀት መመርመር ይኖርበታል። በተለይ ኢዜማ የሚፈልገው ‘ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት’” ካቀረበው አምስት ወይም ስድስት አይነት የፌደራላዊ አወቃቀር ጋር መሄድ መቻሉና አደጋም ካለው አደጋው ከወዲሁ ታውቆ መፍትሄውም አብሮ መታየት ያስፈልገ ይሆናል።

  ይህን በዚህ ላቆየውና ኢዜማ በፕሮግራሙ ውስጥ ስለ’ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓቱ” አተገባበር ከገላጻቸው በመነሳት አንዳንድ ግምታዊ ሃሳቦች ልሰንዝር:: ለዚህም እንዲረዳ በፕሮግራሙ ቁጥር 1.3 ስር ያሰፈራቸውን እንመልከት::

  ”በዜጎች ቀጥተኛ ምርጫ በሚመረጠው ፕሬዚደንት . . . የጠቅላላውን መራጭ 50%+1 ማግኘት አለበት። በመጀመሪያው ዙር ማንም ተወዳዳሪ ይህንን ማግኘት ካልቻለ በሁለተኛ ዙር ሁለቱ ከፍተኛ ደምጽ ያገኙት ተወዳዳሪዎች ብቻ ተወዳድረው ያሸነፈው የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ይሆናል።”

  ቀጥታ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሚያደርጉ ሃገሮች አሉ:: እንደኛ በብዙ ሚሊዩን የሚቆጠሩ ድምጽ ሰጪዎች ያሏችው ሃገሮች ለምሳሌ ብራዚልና ሜክሲኮ ቀጥታ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ያደርጋሉ:: እነዚህ ሃገሮች ፕሬዚዳንታዊ ስርአት የሚከተሉ ብቻ ሳይሆን ፌደራላዊ ሀገሮችም ናቸው። ይህም ቢሆን ፌደራላዊ ስርአታቸአው እንደኛ “በብሄር ብሄረሰብና በህዝብ” ባለመሆኑ የምርጫ ውጤቱ ሃገራዊ ነው። በእኛ ሁኔታ የሚያሰጋው የፕሬዚዳንታዊ እጩዎች ብሄር እየታየ ድምጽ ሊሰጥ ስለሚችል ሃገሪቱ ሊኖራት የሚችለው ፕሬዚዳንት ሁሌም ከፍተኛ ቁጥር ካለው ብሄር ወይም ብሄሮች ሊሆን መቻሉ ነው። ይህ ደግም ሃገሪቱን ቀውስ ውስጥ የሚከት ችግር ነው። ስለዚህም ነው ጉዳዩን በጥሞና መመርመር የሚያስፈልገው::

  አንዳንድ ሃገሮች ቀጥታ ባልሆነ መንገድ በተመራጮች መራጮች አማካይነት ፕሬዚዳንት ይመርጣሉ:: ለዚህ አንድ ምሳሌ የተባበረችው አሜሪካ ናት:: አሜሪካውያን በቀጥታ ለፕሬዚዳንቱ የሚሰጡት ድምጽ ወደ ተመራጮች መራጮች ተመንዝሮ እነዚህ ተመራጮች ፕሬዚዳንቱን ይመርጣሉ:; ይህን ለምን ሆነ ትሉ ይሆናል። ምክንያቱ ሰፊው ድምጽ ሰጭ በክልላዊ ና ሃይማኖትን በመሰሉ ጉዳዩች በቀላልይ ድምጹን ለአንዱ ወይም ለሌላው ሊሰጣ ስለሚችል በዚህ ሁደት ድምጽ ያገኘን ተመራጭ ለፕሬዚዳንታዊ ሃላፊነት ብቃቱን በቅርብ ለማረጋገጥ ይችላሉ የተባሉ ተመራጮች በድምጻቸው የመጨረሻውን ውስኔ እንዲያደርጉ መጠበቂያ ነው:: ባጭሩ ሃገራቸውን ዝም ብለው ሰፊው ድምጽ ሰጭ ለመረጠው ሰው ላለማስረከብ ነው:: በኛም ሃገር የ ሰፊው ድምጽ ሰጭ ብቃት ጥያቀ ከተነሳበት ቀጥታ ያልሆነ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማድረግ ይቻል ይሆናል:: በህገ መንግስቱ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመረጠው ከህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት በህዝብ ተወካዩች በመሆኑ ቀጥተኛ ያልሆነ ምርጫ ነው::

  ለማንኛውም ”ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት” እና ”ፓርላሜንታዊ ስርዓት”በሚመለከት እንዳልኩት ህዝብ ፕሬዚዳንቱን በቀጥታ ስለመረጠ የተሻለ አስተዳደር ያገኛል – ቀጥታ ባልሆነ መንገድ ከመረጠ ደግሞ ለጭቆና ይዳረጋል ማለት አይደለም:: ሁለቱም ጠቃሚም ጎጂም ገጽታ አላቸው:: ዋናው ነገር ለሃገራችን የትኛው ይሻላል የሚለው ነው::

  ኢዜማ እንደሚለው ምርጫው በቀጥታ ይደርግ ከተባለ ፕሬዚዳንት ለመሆን ስንት በመቶ ይሁን የሚለው ቀጣይ ጥያቄ ይሆናል:: በተመሳሳይ ሁኔታ ፕሬዚዳንቱ ለስንት የምርጫ ዘመን ያገልግል የሚለውም አወያይ ነጥብ ቢሆንም በቀላሉ ሊፈታ የሚችል ይመስላል::

  ይቀጥላል::

  Dinaw Demissie
  May 22, 2019 at 1:00 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.