ከገባንበት የፖለቲካ አጣብቂኝ እንዴት እንላቀቅ!! – አቶ አንዷለም አራጌ

1 min read
አቶ አንዷለም አራጌ የኢዜማ ምክትል መሪ
አቶ አንዷለም አራጌ የኢዜማ ምክትል መሪ

“”እስከ ዞንና ወረዳ በዘለቀ መልኩ ውይይት በማድረግ አገሪቱ ከገባችበት አጣብቂኝ እንድትወጣ ማድረግ ይቻላል ብየ አምናለሁ። ይህንን ማድረግ ባለመቻላችን ለውጡ ባለበት ቆሟል””

አቶ አንዷለም አራጌ የኢዜማ ምክትል መሪ።
-=-

በአፍሪካ የምጣኔሀብት ኮሚሽን ፅ/ቤት አዳራሽ በጠቅላይ ሚንስትሩ ፅ/ቤት አዘጋጅነት ለአምስተኛ ጊዜ ዛሬ በተደረገው ውይይት ላይ ነው አቶ አንዷለም አራጌ ያዘጋጁትን የጥናት ወረቀት ሲያቀርቡ ይህንን የተናገሩት።
-=-=-

ውይይት ማድረጉ መልካም ነው። ከአሁን በዃላ በውይይት ብቻ የሚፈታ ችግር ይኖራል ብየ ግን አላምንም። ችግሩ ሊፈታ የሚችለው ተገቢና የማያዳግም ፍትሀዊ ውሳኔ በመስጠት ብቻ ነው።
-=-=-

ውሳኔ አንድ:
-=-=-=-=-=-

በባንቱስታኒስትና አፓርታይዲዝም ቀመር ህወሐትና ኦነግ በሳሉት ካርቶግራፊ ላይ ተመስርቶ በ2/3 ኛው የሀገሪቱ ህዝብ ጉሮሮ ላይ የቆመውን ፌዴራሊዝም አፍርሶ ፍትሀዊ የሆነና ለአስተዳደር የሚበጅ የፌደራል ስርዓት መመስረት።
-=-

ውሳኔ ሁለት፡
-=-=-=-=-=-

2/3 ኛውን የሃገሪቱ ህዝብ ባገለለ መልኩ በህወሐት እና ኦነግ የተደረሰውን “ህገ መንግስት” ቀዳዶ በመጣል ሁሉም ዜጎች በእኩልነት ተወክለው የተሳተፉበት እና አርቅቀው ያፀደቁት ህገ መንግስት ማዘጋጀት።

ይሄው ነው።
-=-=-

ከዚህ ውጭ ያለው ውይይትና እስከአምስት ሚሊዮን ብር የወጣበት የእራት ግብዣ ያለፈውን ፋሽስት የህወሐት ቅኝ ግዛታዊ ስርዓት ለማስቀጠል የሚደረግ ከንቱ ድካም ነው።
-=-=-

ጠቅላይ ሚንስትሩ በተደጋጋሚ እንደገለጡት ያሳለፍነው 27 አመት በኢትዮጵያ ሃገራዊ ነባራዊነት በጨለማ ዘመንነቱ በታሪክ የሚመዘገብ አሳዛኝ ክስተት ነው።
-=-=-

ከጨላማው ዘመን መላቀቅ የሚቻለው ደግሞ የጨለማውን ዘመን ታሪክ ከነጨለማው አዳፍኖ አዲስ ታሪካዊ የብርሀን ዘመንን በመሻት ነው።
-=-=-

ፌደራሊዝሙን አፍርሶ አዲስ ህገመንግስት ማፅደቅ ለምንመኘው የብርሃን ዘመን ያለምንም ቅደመሁኔታዎች ሊተገበር የሚገባው የመጀመሪያ ስራ ነው።
-=-=-

ከዚህ ውጭ ያለው ከንቱ ድካም እኔን እስከሚገባኝ ድረስ የራሱን የወደፊት ዕጣ ፋንታ በዕራሱ እጆች ለመፃፍ ቆርጦ የተነሳውን የአማራ ብሄርተኝነት ለማሰናከልና ለማዘናጋት የታለመ እኩይ ሴራ ነው።
-=-=-

7 Comments

 1. ከገባንበት የፖለቲካ አጣብቂኝ እንዴት እንላቀቅ?

  The answer is: That will be when you go back to Kalitti again. Things got out of control after you and Eskender were released.

 2. “2/3 ኛውን የሃገሪቱ ህዝብ ባገለለ መልኩ በህወሐት እና ኦነግ የተደረሰውን “ህገ መንግስት” ቀዳዶ በመጣል ሁሉም ዜጎች በእኩልነት ተወክለው የተሳተፉበት እና አርቅቀው ያፀደቁት ህገ መንግስት ማዘጋጀት።”

  ጭባ, MORON, ኦነግ በህገ መንግስቱ አልተሳተፈም: ያንተው ብአድን ነው የተሳተፈው::

  “አፓርታይዲዝም” there is no word like this. It’s Apartheid. You are like: “little knowledge is dangerous.”

 3. VIVA ANDINET ARAGAW. You have said the truth but no one of them to listen & understand it .
  One Nation & One country.

 4. Truth be told most people including me are trying our best to shy away from the radical ethnic political lifestyle . We are also trying to shy away from both radical ethnic social lifestyle and radical ethnic economical lifestyle which we led for more than three decades.

  No matter how hard we try we seem to be unable to break free from the radical ethnic lifestyle addiction. Quiet to the contrary the harder we try to break free from the radical ethnic lifestyle addiction, the more radicalized we find ourselves getting.

 5. Here is a corrected verson of an opinion you might have problem reading elsewhere.

  የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) ፕሮግራም እይታ – በወፍ በረር

  ”ቤት ለምቦሳ ፥ እምቦሳ እሰሩ” ወይስ ”ያው በገሌ”?

  ከስሙ በመነሳት የኢዜማ ትኩረት ዜግነትና ማህበራዊ ፍትህ መሆናቸውን መገመት ይቻላል። ይህም ቢባል ስለፓርቲው ምንነት በበቂ ሁኔታ ለመረዳት ከሁለቱ ጠቋሚ ቃላት በዘለለ ፕሮግራሙን በሙሉ ማንበብ ያስፈልጋል። እኔ ከዚህ ማህበራዊ ገጽ ላይ አግኝቼ አንብቤዋለሁ። እውነት ለመናገር እንደጠበኩት አይደለም። ላስረዳ።

  ኢዜማ ”ዜግነት” የሚለውን መሰረታዊ ሃሳብ ያነሳው የ”ዘር”ፖለቲካን እንደማይቀበል ለማሳየት መስሎኝ ነበር። ፕሮግራሙን ሳየው ግን ያገኘሁት ተቃራኒውን ነው:: የሚከተለውን ከፕሮግራሙ በቀጥታ የተወሰደ ክፍል እንመልከት::

  ”የኢዜማ የፖለቲካ ፕሮግራም በወሳኝ መልኩ ያልተማከለ አስተዳደር (ፌዴራላዊ) ሥርዓትን መከተለን ምርጫው ያደረገ ነው፡፡”

  ይህ ”ምርጫ” ያልተጠበቀ አይደለም። ኢዜማ ምርጫ አደርግሁ ይበል እንጂ ከፌደራሊዝም ሌላ ምርጫ አልነበረውም። ዋናው ጥያቄ ግን ምን አይነት ፌዴራሊዝም የሚለው ነው። ከላይ ያየነው ጥቅስ ይህን ጥያቄ አይመልስም። ይህ ማለት ግን ኢዜማ ሊያቆመው የሚፈልገውን የፌዴራላዚም አይነት በፖለቲካ ፕሮግራሙ ውስጥ አልገልጸም ማለት አይደለም። በጉዳዩ ላይ የሚከተለውን ይላል።

  ”1.1.1. ኢዜማ የሕገ መንግሥት ማሻሻያ መደረግ አለበት ብሎ ያምናል፡፡ሕገ መንግስቱ የግለሰብ መብትን የመብቶች ሁሉ የማእዘን ድንጋይ አድርጎ እንዲወስደው፣ የቡድንና የወል መብቶች ከግለሰብ መብቶች የሚመነጩ መሆናቸውን የሚቀበል፣በዘር ወይም በእምነት ላይ ያልተመሰረተ፣ ያልተማከለ ፌዴራላዊ አስተዳደር እንዲኖር ይስራል”

  አንደገባኝ ከሆነ በስራ ላይ ያለው ህገመንግስት ፌደራሊዝምን ያዋቀረው በ”ብሄር ፥ ብሄረሰቦችና ህዝቦች” አስፋፈር ላይ ስለሆነ የተባለው የሕገ መንግሥ ት ማሻሻያ የሚደረገው በዚሁ ህገመንግስት ላይ ነው ማለት ነው።

  ኢዜማ ያለውን ህገመንግስት መቀበሉ ጥሩ ጅምር ነው። ያለውን ማሻሻል አንጂ ከዚህ በፊት በሰፊው ይባል አንደነበረው በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ተቀባይነት ያለውን ሀገመንግስት አንዳለ ለመተካት መስራት ጊዜና ጉልበት ከማባከን በተረፈ ግጭትን ባባባሰ ነበር። ህገመንግስቱን መቀበል ከህገመንግስቱ ደጋፊዎች ጋር ለመነጋገር፥ ለመደማምጥ፥ አምኖ ለማሳመንና አቅዋም ለማስለወጥ እንዲሁም አብሮ ለመስራት በር ይከፍታል። ይህ ደግሞ መበረታታት ያለበት ተግባር ነው::

  ከላይ 1.1.1. ስር የሰፈረው “የቡድንና የወል መብቶች ከግለሰብ መብቶች የሚመነጩ መሆናቸው” የሚለው በተቃራኒው ይሁን አይሁን ወይም ሁለቱም በአንድ ጊዜና ቦታ ሊከበሩ የሚችሉ ወይም የተለያዩ መብቶች ይሁኑ አይሁኑ ብዙ የንድ ፈሃሳብ ክርክርና ውይይት የተደረገባቸው ወደፊትም ሊደረጉባቸው የሚችሉ ጉዳዩች ናቸው። ይህ አንድ ሰፊ ጥናት ተደርጎበት ለማስተማሪያነትና ለማጣቀሻነት የሚያገለግል ሰነድ ሊዘጋጅበት የሚችል ነገር ነው። ለእንደዚህ አይነት ስራ ኢዜማ አንድ የምሁራን ቡድን ሳያስፈልገው አይቀርም።

  አሁንም አንደገባኝ ከሆነ የኢዜማ ፍላጎት “በዘር” ላይ ያልተመሰረተ ፌዴራሊዚም ማቆም ነው። ይህ ከሆነ በ1.2.1 ስር “የአስተዳደር አካባቢዎች አወቃቀር መርሆዎች — መልከአ ምድራዊ አቀማመጥን፣ የሕዝብ አሰፋፈር ለአጠቃላይ አስተዳደራዊና ለልማት ሥራዎች አመቺነትን፤ ቋንቋ፤ ባህል፥ ስነልቦናዊ ቁርኝት እና ታሪክን፤ የሃብት ስብጥርና ፍትሃዊነት
  ለብሔራዊ መግባባት አመቺ ሁኔታ መፍጠርን፤ መሠረት ባደረገ ሁኔታ ይሆናል” የሚለውን ምን አመጣው?

  ኢዜማ “ዘር” የሚለው ምንን እንደሆነ ግልጽ አስካላደርገ ድረስ በስራ ላይ ያለው ህገመንግስት “ብሄር፥ ብሄረሰብና ህዝቦች” ያላቸውን መሆኑን መገመት ይቻላል። ህገመንግስቱ “ብሄር፥ ብሄረሰብና ህዝቦች” ያላቸውን በአንቀጽ 39 (5) ስር ይተረጉማል።

  ትርጉሙ አንደሚከተለው ይነበባል።

  “ሰፋ ያለ የጋራ ጠባይ የሚያንጸባርቅ ባህል ወይም ተመሳሳይ ልምድ ያላቸው፣ ሊግባቡበት የሚችሉበት የጋራ ቋንቋ
  ያላቸው፣ የጋራ ወይም የተዛመደ ህልውና አለን ብለው የሚያምኑ፣ የሥነ ልቦና አንድነት ያላቸውና ባአብዛኛው
  በተያያዘ መልክዓ ምድር የሚኖሩ ናቸው”

  ሙሉ ለሙሉም ባይሆን ከላይ በቁጥር 1.2.1. ስር የሰፈረው የኢዜማ የአስተዳደር አካባቢዎች መርሆዎች “ቋንቋን፤ ባህልን፥ስነልቦናዊ ቁርኝት እና ታሪክን” አስካነሳ ድረስ በስራ ላይ ካላው ህገመንግስት አንቀጽ 39 (5) ዝርዝር ጋር የሚጋራው ብዙ ነገር አለ። ይህም የ”ብሄር፥ ብሄረሰብና ህዝቦች” ክልላዊ አደረጃጀት በመቀበል ነው። ይህ ከሆነ የ<> ላይ ላልተመሰረተ ፌደራሊዝም አንሰራለን የሚባለው ምንድነው?

  ችግሩ ያለው ህገመንግስቱ ያቆመው በ”ብሄር፥ ብሄረሰብና ህዝቦች” ላይ የተመሰረተ ህገ መንግስት የፈጠረውን ሃገራዊ ጉዳት በፖለቲካ ሃኪምነት አናድናለን በሚል ጉዳት ያሉትን ሀገመንግስት አንዳለ ይዘው ያለውን ጉዳት የሚያባብስ ተጨማሪ አደረጃጀቶ ማምጣታቸው ነው። አነዚህም “መልከአ ምድራዊ አቀማመጥ፣ የሕዝብ አሰፋፈር ለአጠቃላይ አስተዳደራዊና ለልማት ሥራዎች አመቺነትን፤ . . . የሃብት ስብጥርና ፍትሃዊነት ለብሔራዊ መግባባት አመቺ ሁኔታ መፍጠር” የተባሉት ናቸው።

  እግዚኣብሄር ያሳያችህ! በ”ብሄር፥ ብሄረሰብና ህዝቦች” የተዋቀረን ፌደራሊዝም በሚገባ መምራት አቅቶን አየተንገዳገድን ይሀ ፌደራሊዝም አንዳለ ሆኖ ሌሎች አምስት ወይም ስድስት አዲስ የፌደራሊዝም አደረጀጀቶች አክለንበት ተያይዘን ገደል ስንገባ። እነዚህ ተጫማሪ የተባሉ የፌደራሊዝም አደረጃጀቶች እየተዳከመ ያለውን ሃገራዊ መግባባት አጥፍተው በማን አንሼነት ማለቂያ የሌለው ሃገር አቀፍ የማያስፈልግ አተካራና ፍትጊያ በመጨረሻም የሃገርን መፍረስ የሚያስክትሉ ናቸው። እንዲያው ለነገሩ ማን ነው በየትኛው አደረጃጀት ስር የሚገባው? ይህንንስ የሚወስነው ማነው? እንዴትስ ተግባራዊ ይሆናል? በማን? ያልተመለሱ ምናልባትም ሊመለሱ የማይችሉ ጥያቄዎች ይሆናሉ።

  በነገራችን ላይ የቤልጅም ብሄርተኞችን እያወዛገበ ሀገሪቱንም ለማፍረስ በቋፍ ያደረሳት በቋንቋ ፌደራሊዝም ላይ የተጨመሩ ሁለት ማለትም የመሬት አቀማመጥ (ጂኦግራፊያዊና) ማህበረሰባዊ (ኮሙኒቲ) አደረጃጀቶች ናቸው:: ከዚሁ ውዝግብ የተነሳ ቤልጅም ውስጥ አንድ ም እንኳ ሃገራዊ ፓርቲ መመስረት አልተቻለም:: ይህ ብቻ አይደለም – ብሐራዊ ሚዲያ የለም:: ሃገር አቀፍ ምርጫ ተደርጎ መንግስት ለማቆም ችግር ይፈጠራል:: ከምርጫ በኋላ ያለሃገራዊ መንግስት ከአምስት መቶ ቀናት በላይ በመቆየት ቤልጀም ርከርድ ይዛላች:: እኛስ የምንፈለገው እንደቤልጀም መሆን ነው:: አስቡት! ከሰማንያ በላይ ብሄር ብሄረሰብ ባላበት ሃገር የተወሳሰበ ሌላ ፌደራላዊ አደረጃጀት ጨምረብነት የት እንደምንደርስ!

  ኢዜማ በዘር የተመሰረተ ፌዴራላዊ አስተዳደር አልቀበልም – ፕሮግራሜም ተዛብቶ የ”ብሄር፥ ብሄረሰብና ህዝቦች” ፌደራሊዝም አንደምደግፍ ተደርጎ ቀርቦአል የሚል ቢሆን ተጨማሪ መረጃዎች እናቅርብ።

  በፕሮግራሙ 1.3 ስር አሁን በስራ ላይ ያለው ህገ መንግስት ያቆመው የፌደሬሽን ምክር ቤት ያለስም ለውጥ አንደሚኖር እንደሚከተለው ተገልጻል።

  “የፌዴራሽን ምክር ቤቱ በአስዳደር አካባቢዎች በእኩል የሚወከሉበት እና የአስተዳደር አካባቢዎች በሚኖራቸው ብሔረሰቦች ብዛት አነስተኛ ቁጥር ላላቸው ብሔረሰቦች ተጨማሪ ውክልና የሚሰጥ ሆኖ አስፈላጊው ድጋፍ እንዲያገኙ ህጎችን የማመንጨት፤ ሕጎችን የመገምገም፤ አፈፃፀማቸውን የመከታተል ሃላፊነት ይኖርበታል፡፡”

  እዚህ ላይ ፍላጎታችን የምክር ቤቱን አዲስ ስልጣን መመርመር ሳይሆን እንደ ተቋም በአስተዳደርዊ ክልል የሚገኙ <> የሚወከሉበት መሆኑን ማሳየት ብቻ ነው ። ባጭሩ አሁን አእንዳለው የፌደሬሽን ምክር ቤት የ”ብሄረሰቦች” ቤት ነው ማለት ነው። ይህ የሚያሳየው ኢዜማ የ”ብሄር፥ ብሄረሰብና ህዝቦች” ፌደራሊዝም አራማጅ መሆኑን ነው:: ይህ ከሆነ አሁን ያለውን ፈደራሊዝም የ”ዘር” ምናምን እያለ ማጣጣሉ ትርጉም የለውም። ይባስ ብሎ ሌሎች ተጨማሪ አደረጃጀቶች ይዞ ብቅ ማለቱ አሳሳቢ ችግር ነው።

  ይህ ብቻ አይደለም:: አሁን ያለው ህገመንግስት የተቀበለውን ህዝበ ውሳኔ እንደዋነኛ መሳሪያነት እንደሚጠቀምበት በተላይዩ የፕሮግራሙ ክፍሎች ጠቁሟል:: የ”ብሄር፥ ብሄረሰብና ህዝቦች ፌደራሊዝም” የሚቀበል እንደምሆኑ መጠን የመገንጠል ህዝበ ውሳኔንም ይቀበላል ማለት ነው:: ይህ ደግሞ በ 1.1.6. ስር ከሰፈረው ” የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት ሊገሰስ የማይችልና የማይገሰስ መሆኑን” ከሚገልጸው በቀጥታ ይጋጫአል:: “ብሄር፥ ብሄረሰብና ህዝቦች ፌደራሊዝም” እና ህዝበ ውሳኔን ተቀብሎ ስለሀገራዊ የግዛት አንድነት ማውራት አይቻልም::

  ኢዜማ የ”ብሄር፥ ብሄረሰብና ህዝቦች” ፌደራሊዝም አራማጅ እስከሆነና ህዝበ ውሳኔ እስከተቀበለ ድረስ በፕሮግራሙ ውስጥ የጠቀሰው የህገመንግስት ማሻሻል አያስፈልገውም። የቡድንና የወል መብቶች ከግለሰብ መብቶች የሚመነጩም ሆኑ አልሆኑ መብቶቹ ከላይ በቀረበው አይነት ህገመንግስታዊ ተቀባይነት ካገኙ ከብሄርተኞች ጋር ያለው የአደረጃጀት ልዩነት አውነትም ልዩነት አይደለም ማለት ነው። የዜጋ ፖለቲካ የሚባውም ቱሻ ነው ማለት ነው።

  ኢዜማ “ብሄር፥ ብሄረሰብና ህዝቦች” የተደራጀ ፌደራሊዝምን እስከ ህዝበ ውሳኔ ስለሚቀበል ይህን ፖለቲካ የ”ዘር” ፖለቲካ – የመስመሩን አራማጆችን ደግሞ የ “ዘር” ፖለቲከኞች አያለ መጥራት አይኖርበትም። አመራሩም ሆነ አባላቱ አነዚህን ቃላት ክመጠቀም ተቆጥበው ፖለቲካውን የብሄር ፖለቲካ አራማጅቹን ደግም ብሄርተኞች ሊሏቸው ይገባል ባይ ነኝ። አለበለዚያ የአስተሳሰብ ወጥነት የጎደለውና እምነት ሊጣልበት የማይችል ድርጅት ተደርጎ ሊታይ ይችላል።

  ይቀጥላል።

 6. Revised.

  ካላፈው የቀጠለ –

  አሁን ደግሞ ኢዜማ የመረጠውን ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት እንመልከት:: ይህን ስናደርግ ኢዜማ እንዲኖር የሚፈልገውን ፌደራላዊ ስርዓት የሚመሰረትበትን ማለትም ”መልከአ ምድራዊ አቀማመጥን፣ የሕዝብ አሰፋፈር ለአጠቃላይ አስተዳደራዊና ለልማት ሥራዎች አመቺነትን፤ ቋንቋ፤ ባህል; ስነልቦናዊ ቁርኝት እና ታሪክን፤ የሃብት ስብጥርና ፍትሃዊነት ለብሔራዊ መግባባት አመቺ ሁኔታ መፍጠርን . . . ” በአዕምርዋችን ይዘን መሆን ይኖርበታል:: ምክንያቱም ለዚህ ዓይነት ፌደራሊዝም የሚሻለው ፕሬዝዳንታዊ ወይስ ፓርላሜንታዊ ስርዓት መሆኑ መነሳቱ ስላማይቀር ነው::

  ኢዜማ በፕሮግራሙ መግቢያ ላይ የሚከተለውን ይላል::

  ” ከፍተኛው የመንግሥት ሃላፊነት በሕዝብ ቀጥታ ምርጫ የሚመረጥ ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት እንዲሆን አበክሮ ይሰራል፡፡ ”

  እርግጥ አሁን በሚሰራበት ህገ መንግስት የተቋቋመው የሀገራችን ፓርላሜንታዊ ስርዓት (አንዳንዶች ድብልቅ ይሉታል – ምክንያቱም ጠቅላይ ሚኒስትርም ፕሬዚዳንትም ስላለው) በሚያስፍር ሁኔታ የህዝብን መብት የረገጠ ነበር:: ፓርላሜንታዊ ስርዓት ኖሯቸው እንደኛ የህዝብን መብት የረገጡ – አሁንም እየረገጡ ያሉ ጥቂት የማይባሉ ሃገሮች አሉ::

  የኛና ጥቂት የማይባሉ ሃገሮች ፓርላሜንታዊ አስተዳደር የህዝብን መብቶች በገፍ ቢጥሱም ተመሳሳይ ፓርላሜንታዊ ስርዓት ያላቸው በርካታ ሃገሮች ግን የህዝቦቻቸውን መብቶች አክብረውና ፍላጎቶቻቸውን በሚገባ አሟልተው አስተዳድረውበታል:: አሁንም እያስተዳደሩበት ይገኛሉ:: ለዚህ ማስረጃው የተዋጣለት ፓርላሜንታዊ ስርዓት የሚከተሉ አውስትራሊያ – ካናዳ – ዴንማርክ – ህንድ – ጀርመን – ፊንላንድ – ጣልያን – ግሪስ -ፖርቹጋል – ስዊዘርላንድ የመሰሉ ሃገሮች መኖራቸው ነው::

  ከላይ እንዳየነው ፓርላሜንታዊ ስርዓት እኛና መሰሎቻቸን መብት ረጋጭ ሃገሮች ስለተቀላቀልነው በራሱ የህዝብን መብቶች ለማክብርም ሆነ ፍላጎቶቻቸውን ለማሟላት የማያስችል ስርዓት ነው ወደሚል የተሳሳተ መደምደሚያ እንዳያደርስ መጠንቀቅ ያስፈልጋል::

  የሃገራችን ፓርላሜንታዊ ስርዓትም በዲሞክራሲ፥ በህግ የበላይነትና በጠንካራ ነጻ ሚዲያ ከተሟላ ከላይ እንደተዘረዘሩት ሃገሮች ሊሰራ የማይችልበት ምክንያት አይታየኝም:: ስለሆነም ኢዜማ ፕሬዚዳንታዊ ስርአት ያስፈልጋል ሲል አዲስ የተለየ ነገር ለማምጣት ብቻ ብሎ ያደረገው እንዳይሆን መጠንቀቅ ይኖርበት ይሆናል::

  ዝርዝር ውስጥ መግባት ሳያስፈልግ ”ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት” እንደ ፓርላሜንታዊ ስርዓት የህዝብን መብቶች በሚረግጡ እንዲሁም ፍላጎቱን ማሳካት በተሳናቸው እና መብቶች በማክበር በሚታወቁ ሃገሮች የተሞላ ነው:: ከዚህ አጠቃላይ እውነታ የምንረዳው ስርዓቱን በራሱ የጭቆና አስተዳደርን እንደማያስወግድ ወይም እንደማያመጣ ነው:: እንደ ፓርላሜንታዊው ስርዓት ሁሉ የተሟላ እንዲሆን ዲሞክራሲ፥ የህግ የበላይነትና ጠንካራ ነጻ ሚዲያ ያስፈልገዋል::

  ኢዜማ ‘ ‘ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት” የመረጠበትን ምክንያት ወደፊት በሰፊው እንደሚያስርዳ ይጠበቃል:: ዝም ብሎ ፓርላሜንታዊ ስርዓት አልሰራም – ወይም አይሰራም – ስለሆነም ለውጠን እንሞክረው ሊለን አይችልም:: ጊዜው የሙከራ አይደለምና:: በተለይ ዲሞክራሲና የህግ የበላይነት በሃገሪቱ ከሰፈነና ጠንካራ ነጻ ሚዲያ ከተፈጠረ እየተለመደ ከመጣው ከፓርላሜንታዊ ስርዓት በመውጣት ወደ ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት መሄድ ለምን እንደሚያስፈልግ በበቂ ሁኔታ ማሳየት ይኖርበታል::

  ይህ ብቻ አይደለም። ኢዜማ የሚፈልገው ‘ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት” በስራ የሚተርጎመው በፌደራላዊ ሃገር በመሆኑሥርዓቱ ተሞክሮ ከነበረው ፓርላሜንታዊ ስርዓት የተሻለ ውጤት እንደሚያስገኝ በቅድሚያ ማረጋገጥ ይስፈልጋል። ዲሞክራሲ፥ የህግ የበላይነትና ጠንካራ ነጻ ሚዲያ ባልነበረበት ሁኔታ በሀገራችን የተሞከረው ፓርላሜንታዊ ስርዓት የፈጠረው የጭቆና አስተዳደር ነው። እነዚህ ችግሮች ከተወገዱ ያለውን ፓርላሜንታዊ ስርዓት በማስቀጠል የተሻለ ውጤት ማግኘት እንደሚቻል መገመት በአግባቡ ነው። አውስትራሊያ – ካናዳ – ኔዘርላንድስ – ጀርመን – ስዊዘርላንድ የተዋጣለት ፓርላሜንታዊ ና ፌደራላዊ ሃገሮች ናቸው።

  ዲሞክራሲ፥ የህግ የበላይነትና ጠንካራ ነጻ ሚዲያ ባለበት ፓርላሜንታዊ ስርዓት በአጥጋቢ ሁኔታ እንደሚሰራ ሁሉ ‘ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት’ም” ዲሞክራሲ፥ የህግ የበላይነትና ጠንካራ ነጻ ሚዲያ ባለበት በሚገባ ይሰራል።ፓርላሜንታዊ ስርዓትን በሚመለከት እንዳኩት ‘ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓትም” በሃገራችን ፌደራልዝምን ለመተግበር ተስማሚነቱ በጥልቀት መመርመር ይኖርበታል። በተለይ ኢዜማ የሚፈልገው ‘ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት’” ካቀረበው አምስት ወይም ስድስት አይነት የፌደራላዊ አወቃቀር ጋር መሄድ መቻሉና አደጋም ካለው አደጋው ከወዲሁ ታውቆ መፍትሄውም አብሮ መታየት ያስፈልገ ይሆናል።

  ይህን በዚህ ላቆየውና ኢዜማ በፕሮግራሙ ውስጥ ስለ’ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓቱ” አተገባበር ከገላጻቸው በመነሳት አንዳንድ ግምታዊ ሃሳቦች ልሰንዝር:: ለዚህም እንዲረዳ በፕሮግራሙ ቁጥር 1.3 ስር ያሰፈራቸውን እንመልከት::

  ”በዜጎች ቀጥተኛ ምርጫ በሚመረጠው ፕሬዚደንት . . . የጠቅላላውን መራጭ 50%+1 ማግኘት አለበት። በመጀመሪያው ዙር ማንም ተወዳዳሪ ይህንን ማግኘት ካልቻለ በሁለተኛ ዙር ሁለቱ ከፍተኛ ደምጽ ያገኙት ተወዳዳሪዎች ብቻ ተወዳድረው ያሸነፈው የሀገሪቱ ፕሬዜዳንት ይሆናል።”

  ቀጥታ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የሚያደርጉ ሃገሮች አሉ:: እንደኛ በብዙ ሚሊዩን የሚቆጠሩ ድምጽ ሰጪዎች ያሏችው ሃገሮች ለምሳሌ ብራዚልና ሜክሲኮ ቀጥታ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ያደርጋሉ:: እነዚህ ሃገሮች ፕሬዚዳንታዊ ስርአት የሚከተሉ ብቻ ሳይሆን ፌደራላዊ ሀገሮችም ናቸው። ይህም ቢሆን ፌደራላዊ ስርአታቸአው እንደኛ “በብሄር ብሄረሰብና በህዝብ” ባለመሆኑ የምርጫ ውጤቱ ሃገራዊ ነው። በእኛ ሁኔታ የሚያሰጋው የፕሬዚዳንታዊ እጩዎች ብሄር እየታየ ድምጽ ሊሰጥ ስለሚችል ሃገሪቱ ሊኖራት የሚችለው ፕሬዚዳንት ሁሌም ከፍተኛ ቁጥር ካለው ብሄር ወይም ብሄሮች ሊሆን መቻሉ ነው። ይህ ደግም ሃገሪቱን ቀውስ ውስጥ የሚከት ችግር ነው። ስለዚህም ነው ጉዳዩን በጥሞና መመርመር የሚያስፈልገው::

  አንዳንድ ሃገሮች ቀጥታ ባልሆነ መንገድ በተመራጮች መራጮች አማካይነት ፕሬዚዳንት ይመርጣሉ:: ለዚህ አንድ ምሳሌ የተባበረችው አሜሪካ ናት:: አሜሪካውያን በቀጥታ ለፕሬዚዳንቱ የሚሰጡት ድምጽ ወደ ተመራጮች መራጮች ተመንዝሮ እነዚህ ተመራጮች ፕሬዚዳንቱን ይመርጣሉ:; ይህን ለምን ሆነ ትሉ ይሆናል። ምክንያቱ ሰፊው ድምጽ ሰጭ በክልላዊ ና ሃይማኖትን በመሰሉ ጉዳዩች በቀላልይ ድምጹን ለአንዱ ወይም ለሌላው ሊሰጣ ስለሚችል በዚህ ሁደት ድምጽ ያገኘን ተመራጭ ለፕሬዚዳንታዊ ሃላፊነት ብቃቱን በቅርብ ለማረጋገጥ ይችላሉ የተባሉ ተመራጮች በድምጻቸው የመጨረሻውን ውስኔ እንዲያደርጉ መጠበቂያ ነው:: ባጭሩ ሃገራቸውን ዝም ብለው ሰፊው ድምጽ ሰጭ ለመረጠው ሰው ላለማስረከብ ነው:: በኛም ሃገር የ ሰፊው ድምጽ ሰጭ ብቃት ጥያቀ ከተነሳበት ቀጥታ ያልሆነ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ማድረግ ይቻል ይሆናል:: በህገ መንግስቱ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመረጠው ከህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት በህዝብ ተወካዩች በመሆኑ ቀጥተኛ ያልሆነ ምርጫ ነው::

  ለማንኛውም ”ፕሬዝዳንታዊ ሥርዓት” እና ”ፓርላሜንታዊ ስርዓት”በሚመለከት እንዳልኩት ህዝብ ፕሬዚዳንቱን በቀጥታ ስለመረጠ የተሻለ አስተዳደር ያገኛል – ቀጥታ ባልሆነ መንገድ ከመረጠ ደግሞ ለጭቆና ይዳረጋል ማለት አይደለም:: ሁለቱም ጠቃሚም ጎጂም ገጽታ አላቸው:: ዋናው ነገር ለሃገራችን የትኛው ይሻላል የሚለው ነው::

  ኢዜማ እንደሚለው ምርጫው በቀጥታ ይደርግ ከተባለ ፕሬዚዳንት ለመሆን ስንት በመቶ ይሁን የሚለው ቀጣይ ጥያቄ ይሆናል:: በተመሳሳይ ሁኔታ ፕሬዚዳንቱ ለስንት የምርጫ ዘመን ያገልግል የሚለውም አወያይ ነጥብ ቢሆንም በቀላሉ ሊፈታ የሚችል ይመስላል::

  ይቀጥላል::

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.