በአዲስ አበባ የኤሌክትሪክ ኃይል ፈረቃ ስርጭት ለውጥ ተደረገ

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

በአዲስ አባና አካባቢው ለሚገኙ ደንበኞች አስቀድሞ በተገለጸው መሠረት በሶስት ፈረቃ (ከማለዳው 11:00 እስከ ረፋዱ 5:00 : ከረፋዱ 5:00 እስከ ቀኑ 10:00 እና ከቀኑ 10:00 እስከ ምሽቱ 4:00 ሰዐት) በነበረው ፕሮግራም ላይ ለውጥ ተደረገ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት እንደገለጸው፤ ይህ ሶስት ፈረቃ ለአሰራር ምቹ ባለመሆኑ በሁለት ፈረቃ ሊደረግ ችሏል።

በዚህም መሰረት በአዲስ አበባና አካባቢው የመብራት ፈረቃው ከማለዳው 11:00 እስከ ቀኑ 8:00 እና ከቀኑ 8:00 እስከ ምሽቱ 4:00 ሰዐት ሆኗል።

ሁለቱ የፈረቃ ሰዐት በመቀያየር አገልግሎት ላይ የሚውሉ መሆኑንም አገልግሎቱ አስታውቋል።

በሌሎች የሀገሪቱ ክልሎችም ያለውን መርሀ ግብር በክልል: በዲስትሪክትና አገልግሎት መስጫ ጽ/ቤቶች አማካኝነት የሚገለጽ ይሆናል ተብሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.