የአድናቆት ቀን ለመምህራን በአዲስ አበባ

1 min read

በሃገራችን በጎ የሰራን ማመስገን  መልካም ባህላችን ሲሆን ይህን የማያደርግና ብድራቱን የማይመለስ ውለታ ቢስ ተብሎ እንደሚወቀስ የሃገራችን መልካም ባህል ያስተምረናል::

በሃገራችን ኢትዮጲያ መምህራን  ያደረጉት ገንቢ አስተዋጽኦ በጣም ከፍተኛ ሲሆን በተለይ ያ ትውልድ በሚባለው ዘመን በነበረው የፖለቲካ ልዩነት ታስረው ሳይቀር ብዙዎችን በማስተማር ዛሬ በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሃገር ለከፍተኛ ትምህርትና ሃላፊነት የበቁ ብዙዎች ይገኛሉ::

በከርቸሌ በነበረው የሁለተኛ ደረጃ የነበረውን ትምህርት ያስጀምሩና ያስፋፉ:-                                                     1. ዶ/ር አበራ ገይድ

  1. መምህር አማረ በዳዳ
  2. መምህር ይልማ ኪዳነ ማርያም
  3. መምህር ሰራዊቱ እና ሌሎቹም በህይወት ያሉትን በመጭው የገና በአል ዋዜማ በሃገር ቤት ለመዘከር ሃሳብ ስለቀረበ በዚህ መሳተፍ የምትፈልጉ  ለዚህ ሸክም ላላቸው አስተባባሪዎች በኢሜይል በደብዳቤ ታስታውቁን ዘንድ በ ትህትና እንጠይቃለን::

ግልባጭ ለኢትዮጲያዊያን ሚዲያዎች ሁሉ

Former Teachers Appreciation Task Force

ethiopiancommunityomaha@gmail.com

C/O  Ethiopian Amercan community

3314 s 44th Avenue

Omaha NE 68105

USA

 

2 Comments

  1. የዚህ አይነቱ የእውቅን ፕሮግራም ይበል የሚያስኝ በጎ ጅምር ነው፡፡ አዎን መምህራን በሀገራችን ውስጥ ትምህርት እንዲዳረስ ፤ እንዲስፋፋና እንዲሁም በአጠቃላይ ለሀገራችን እድገት ከፍተኛ አስተዋጾ አበርክተዋል እያበረከቱም ይገናሉ፡፡ ወደፊትም ያበረክታሉ፡፡ ስለዚህ መምህራን ሊደነቁና ዕውቅና ሊሰጣቸው ይጋባል፡፡ በመሆኑም “የአድናቆት ቀን ለመምህራን በአዲስ አበባ” በሚል ርዕስ ለሀጋራችን ትምህርት ዕድገትና መስፋፋት የላቀ አስተዋጾ ያበረከቱት መምህራንን ዕውቅና ለመሰጥት ለወጠኑትና ፕሮግራሙን ለሚያዘጋጁት ሰዎችም ሆኑ ድርጅቶች ያለኝን ከፍተኛ ምስጋናና አክብሮት ለመግለጽ እወዳሉ፡፡ በዚህ አጋጣሚ ግን የዚህ አይነት የእውቅና ፕርግራም ለእንድ ጊዜ ብቻ ተካሂዶ የሚያቆም ሳይሆን ቀጣይነት አንዲኖረው የሚደረግበት መንገድ ቢቀየስ ጥሩ ይሆናል ብዮ አስተያቴን ለመስጠት እወዳለሁ፡፡ በተጨማሪም የሚዘጋጀው የእውቅና ፕሮግም ርዕስ “የአድናቆት ቀን ለመምህራን በአዲስ አበባ” ከሚል ይልቅ “የአድናቆት ቀን ለኢትዮጰያ መምህራን በአዲስ አበባ” በሚል ርዕስ ቢተካ የሚል የተሻለ ይሆናል የሚል አስተያየቴን መስጥ እወዳሉ፡፡

  2. ወገን ዋሴ ያቀረብከው ሃሳብ ትክክል ነው የተወለድንባት ያደግንባት የተማርንባት ከተማን ታሪክና በየጊዜው ያኔ የሚካሄደው የተማሪዎች ቀን ት ዝታ ይዞን እንጂ ይህ ጉዳይ ሃገራዊ መሆን እንዳለበት የሃሳቡ ደጋፊዎች ስላመንበት የአድናቆት ቀን ለኢትዮጵያ መህራን በአዲስ አባባን ተቀብለናል በግብረሃይሉ ለመሳተፍ ከፈለግህ በኮሚኒቲው ኢሜይል ዝርዝሮችን ላክልን

Leave a Reply

Your email address will not be published.

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.