ደቡብ ሱዳን 39 ኤምባሲዎቿን ልትዘጋ ነው

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

ደቡብ ሱዳን በሌሎች ሃገራት የሚገኙ 39 ኢምባሲዎቿን በፋይናስ እጥረት ምክንያት ልትዘጋ መሆኑን አስታውቃለች፡፡

የሃገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ማዊን ማኮል አገሪቱ በውጭ አገር የሚገኙ ኤምባሲዎችዋን ለማስተዳደር አስቸጋሪ ሆኖባታል ብለዋል፡፡

ቃል አቀባዩ ኤምባሲዎቹ በቅርብ ግዜ እንደሚዘጉም አስታውቀዋል፡፡

አገሪቱ ከዚህ ቀደም ስራቸውን በአግባቡ አልተወጡም ያለቻቸውን 40 ዲፕሎማቶች ከስራ ማሰናበትዋ ይታወሳል፡፡

በነዳጅ ምርት ላይ ኢኮኖሚዋ የተጠነጠለው ደቡብ ሱዳን በ2013 በጀመረው የእርስ በእርስ ጦርነት ምክንያት የነዳጅ ምርትዋን መቀነሱ እና የዋጋ ንረት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ይገለፃል፡፡

በአገሪቱ ሙስና መስፋፋቱ እና የፖለቲካ አለመረጋጋት የፋናንስቀውስ ማስከተሉንም ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡- ዘ ኢስት አፍሪካ/ ኢዜአ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.