ከድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ ነው!ተክደናል!!!ዋስትና ተሰጥቶን አልተፈፀመልንም!

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

ዋስትና ተሰጥቶን አልተፈፀመልንም! እንደማይፈፅሙልንም እርግጠኞች ነበርን።
የጠየቅናቸው ጥያቄዎችም አልተመለሱልንም! እንደማይመልሱልንም እርግጠኞች ነበርን።
ግቢው የአማራ ልጆችን ወደ ብጥብጥ አስገብቶ ያለጥፋታቸው እርምጃ መውሰድ እንደሚፈልግም ቀድመን ተናግረን ነበር።
ጥያቄያችንን በዘረኝነት እና በአማራ ጠልነት የተጨማለቀው የግቢ አስተዳደር እንደማይመልስ እናውቅ ነበር።
ከላይኛው የግቢ መዋቅር ጀምሮ እስከ ተማሪ ድረስ የተጀራጀ ፀረ አማራ ቡድን እንዳለም እናውቅ ነበር።
በርግጠኝነት ግን አንድ ነገር ልንገራችሁ ይሄን ተማሪ በትንሹ 600 ኪ.ሜ አቋርጦ የመጣው ለትምህርት ብቻ ነው። ቃላችሁን አለመጠበቃችሁ ሳያንስ እራሳቸውን ለመከላከል የወጡ ልጆችን እስር ቤት መክተት በራሱ ፀረ አማራ አመለካከት ነው። አሁንም ያ
ሰራችኀቸውን 10 የአማራ ተማሪዎች ያለ ቅድመ ሁኔታ ልቀቁልን። አይጥ በበላ ዳዋ የሚመታበት ጊዜ አልፏል። ይሄን ሰላማዊ ተማሪ የመረረ ጥላቻ ውስጥ አትክተቱት። 

 


የተማሪ ህብረትና ኩማንድ ፓስት የሚባሉ ትምህርት የማይፈልጉ ተማሪዎች ህብረትን አሳርፏቸው!!!. የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ የሰጡንን ዋስትና አምነን ግቢ በገባን አንድ ወንድማችን በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቶ ወደ አዲስ አበባ ሪፈር. ተፅፎለታል።

ቀድመን ወደቤታችን ሸኙን የመኖር ዋስትና የለንም ብለናችሁ ነበር!!! እናንተ ግን የፓለቲካ ድጋፍ አላችሁ ብላችሁ በቁስላችን ላይ እንጨት ሰደዳችሁ። እኛም ለተማሪያችን ከናንተ በላይ ስለምናስብና የመንገዱ ደህንነት አስጊ ስለሆነ መሄዱን ትተን ግቢ ገባንላችሁ! ይሄው ተቆርቋሪ፣ ጠያቂ የሌለው እና በታላላቆቹ የተካደ ተማሪ አገኘን ብላችሁ የደም ጥማታችሁን አስታግሱበት።

ይሄ ትውልድ ነገ የት እንደሚደርስ አታውቁም!!! ነገር ግን እንደሚበቀላችሁ በርግጠኝነት መናገር እችላለሁ። ፍትህ በድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለምንገኝ የአማራ ተማሪዎች!!!
ዘረኛው እና ፀረ አማራው ግቢ ይፈተሽ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.