የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስን ከአድርባዮችና ከሆዳሞች ለማጽዳት ለሙያው መስዋት የከፈሉ ሁሉ በየፊናቸው ሊታገሉ ይገባል

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |
የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስን ከመንግስት ፕሬስ ጋር ለመቀላቀል የግል ፕሬሱ ፕሬዝዳንት ነኝ በሚሉት  በመቶ አልቃ ወንድወሰን መኮንንና (አሁን አቶ) በመንግስት ጋዜጠኞች ፕሬዝዳንት  በአቶ መሰረት አታላይ  የመንግስት ጋዜጠኞች ማህበር የተመሰረተበትን 50ኛ ዓመት የመሥረታ ምክንያት በማድረግ ሚያዚያ 29ቀን በተከበረበት ወቅት መገለጹን በግንቦት ወር በወጣው በ«ግዮን» መጽሔት ላይ አንብቤ ነበር።

የነነፃው ፕሬስ ፕሬዝዳንት በአሁኑ ወቅት መሆኑን  የሚያምነው የገዥው ፓርቲ  ከአቶ ክፍሌ ሙላት ይልቅ የቀድሞ መቶ አለቃ የአሁኑ አቶ ወንድወሰን መኮንንን ነው ። በመሆኑም በግል አቶ ወንደወሰንን ይህንኑ በመንተራስ አነጋግሬው ነበር ። በእርግጥ አቶ ወንድወሰንን ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ፕሬስ ውስጥ ከፍተኛ መስዋትነት የከፈለውን እስክንድ ነጋን(የኢትዮፒስ ጋዜጣና የኢትዮጵያ የነፃው ፕሬስ የሥራ አስፈፃሚ አባል የነበረውን) እንዲሁም በስደት ከኢትዮጵያ ውጭ የሚገኙትንና ወደ ኢቱዮጵያ መጥተው እንደኔ ባሉበት ሀገር ኢምባሲ ደንነቶች ሳይታፈኑ ተመልሰው ከመሄዳቸው በፊት ያነጋገርኳቸው በተለይም ለፕሬሱ መስዋትነት ከከፈሉት መካከል በአሜሪካ የሚገኙ እንደ ቢንያም ታደሰ(ሀገሬ ጋዜጣና የቀድሞ የነፃው ፕሬስ ሥራ አስፈፃሚ አባል) እና ሌሎችንም ውጭ ያሉና ኢትዮጵያ ውስጥ በግል ጋዜጣ ላይ ከፍተኛ አስተዋጾ ያደረጉ ጋዜጠኞችን በማነገገር በስደት ያለውና በኢትዮጵያ ያሉ በሁለት ቢለዋ የማይበሉ ጋዜጠኞችን ነበር።  በመሆኑም ኢትዮጵያ ያሉት በግንባር እንዲገኙ ሲደረግ  ሌሎቹ በስደት የሚገኙት ደግሞ በስካይቢ አማካይነት በስብሰባው ላይ ተካፍለው በሰላማዊ መንገድ በሚከናወነው በዚሁ ስብሰባ ላይ ወይ ባለፉት ላይ መጨመር አልያም አዲስ  ምርጫ እንዲከናወን ጋዜጠኞቹን አነጋግሬ ነበር ። በእርግጥ የነፃው ፕሬስ ፕሬዝዳንቶች በሁለት ተከፍሏል በአቶ ክፍሌ ሙላት የሚመራው አብዛኛው የስራ አስፈፃሚ አባላት በስደት የሚገኙ  ናቸው። በአንፃሩ ምክትል ፕሬዝዳንቱ አቶ ታዬ ደግሞ በአሁኑ ወቅት በጥብቅና ሙያ የተሰማሩ ሲሆን ከዚህ በፊት የቀድሞ የጦቢያ ጋዜጣ  አዘጋጅ  ነበሩ  ፤ አቶ ሙልጌታ ሉሌ(በአሁኑ ወቅት በሕይወት የሉም) እና አቶ ስንሻው ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ማህበሩን በመሩበት ወቅት ዋና ፀሐፊ የነበረው እስክንድር ነጋ ና በእነ አቶ ክፍሌ ጊዜ ደግሞ ዋና ፀሐፊ የነበረው (የኢትፕ ጋዜጣና የኢሳት ስራ አስፈፃሚ )የቀድሞ መቶ አለቃ በአሁኑ ወቅት ደግሞ አቶ ሲሳይ አልጌና ኢትዮጵያ ውስጥ ነው የሚገኙት ። በስደት ያሉት አቶ ክፍሌ ሙላት ፤መቶ አለቃ በፍቃዱ ሞረዳ ፤አቶ ታምሩ ገዳ ፤አቶ ሀብታሙ አሰፋ እንዲሁም እራሱን ከሥራ አስፈፃሚነት በፍቃደኝነት ያነሳው አቶ ዘገየና ሌሎችም ለፕሬሱ ከፍተኛ አስተዋጾ በፊት ብቻ ሳይሆን አሁን ድረስ በማድረግ ላይ ያሉ እንደ አቶ ኤልያስ ወንድሙ፤እንደ አቶ ሞገስ ከበደ ፤ እንደ  አቶ ክንፉ አሰፋ ፤ እንደ አቶ ዳዊት ከበደ ወዘተ ያሉ ሕሊናቸውን ሳይሸጡ  ለነፃው ፕሬስ አባላት የታገሉና ከተለያዩ የጋዜጣ መብት ተከራካሪዎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር በመታገል ከፍተኛ አስተዋጾ በማድረግ  ላይ ያሉ ጋዜጠኞች በሚካሄደው አዲሱ  የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውስጥ ተካተውና ሌሎችም ሊሰሩ የሚችሉ ተጨማምረው በተጠናከረ መልኩ ማህበሩ የሚቀጥልበት ሁኔታ

እንዲቀጥል ለማድረግ ከላይ ከጠቀስኳቸው ግለሰቦች ጋር በጉዳዩ ዙሪያ ተነጋግሬ ነበር ። አቶ ወንድወሰን የማህብሩን ማህተምና ሌሎችንም ነገሮች  በአዲስ መልክ ሪፎርም ለሚደረገው በስድትና ሀገር ውስጥ ላሉ የነፃው ፕሬስ ሥራ አስፈጻሚ አባለት ሁሉንም ዶክሜንት ጭምር ለማስረከብ ፍቃደኛ መሆኑን ገልፆልኛል ።አቶ ወንደወሰን እንደሚለው አብዛኛው የነፃው ፕሬስ አባላት በስደት ስለነበር ያለውን ዶክሜንትን ይዤ ከመጠበቅ በስተቀር ሌላ ያደረኩት የለም ብሏል። በእርግጥ አቶ ወንድወሰን ያለፈውን ማህበሩን  በወያኔ  እንዲመታ ለማድረግ  ገዥው ፓርቲ ያቋቋማውን ይህን ማህበር  ለመምራት  መቻሉ ተገቢ  አልነበረም ይህ የማይካድ ሀቅ ነው። ከዚህ ሌላ በአሁኑ ወቅት  ደግሞ አዲስ ዘመን እየሰራ  እያለ የነፃው ፕሬስ ፕሬዝዳንት ነኝ ብሎ መናገሩ ትንሽ  ለህሊና ጭምር የሚከብድ ቢሆንም ሁሉንም የነፃውን  ፕሬስ  ዶክሜንት ለመስጠት ፍቃደኝነቱን  ማሳየቱና  እሺታውን መግለጹ እንደ ወቅቱ  አባባል በፍቅር ከቀድሞ የፕሬስ  አባላት ጋር ለመደመር መዘጋጀቱ የሚያስመሰገነው። ነው።

በሌላ በኩል ወዳጄ ቢንያምም ሆነ  እስክንድር  ነጋ ሀገር ውስጥም ይሁን ከሀገር ውጭ ያሉትን ጋዜጠኞችን በማስተባበር ማህበሩ እንደገና ለማጠናከር ለሚደረገው እንቅስቃሴ የገቡትን ቃል ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ተስፋ አደርጋለው።
  በተረፈ መጽሔቱ ላይ እንዳነበብኩት የግልና የመንግስት ጋዜጠኞችን  ሳይነጣጠሉ አንድ እንዲሆን አንደናደርጋለን በአሁኑ ወቅት መባሉ የሚያስኬድ አይደለም አቶ ወንደወሰን  በፊት የራሱ የግል ጋዜጣ ነበረው ፤እንደሌላው የፕሬስ አባል ተከሷል ታስሯል። ይሁንና በአሁኑ ወቅት ግን የሚሰራው የመንግስት ጋዜጣ  ላይ ነው ስለዚህ የመንግስት ጋዜጠኛ  እንጂ የግል ጋዜጠኛ አይደለም ። በእርግጥ በአሁኑ ወቅት የትኛው ጋዜጠኛ በመንግስት ይደገፋል የትኛው አይደገፍም ብሎ ለመደምደም ይከብዳል።ያም ሆነ ይህ ግን በስደትና በሀገር ውስጥ  ያሉት በአቶ ክፍሌና በአቶ ታዬ የሚመራው የኢትዮጵያ ነፃ ጋሼጠኞች ማህበር ሪፎርም ተደርጎ በስደት ብዙ  ሲደክሙና ሲሰሩ የነበሩ ከላይ ያነሳዋቸውና ያላነሳዋቸው ጋዜተኞች  ተካተው ይበልጥ የሚጠናከርበት መንገድ ሊፈለግ ይገባል እላለው።በተለይም የኢትዮጵያ  ነፃ ፕሬስን ከአድርባዮችና ከሆዳሞች ለማጽዳት ለሙያው መስዋት የከፈሉ ሁሉ  በየፊናቸው ሊታገሉ ይገባል ባይ ነኝ። ሰላም።

One Response to የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስን ከአድርባዮችና ከሆዳሞች ለማጽዳት ለሙያው መስዋት የከፈሉ ሁሉ በየፊናቸው ሊታገሉ ይገባል

  1. የመገናኛ ብዙሃን ሰዎች የማወቅ መብታቸውን የሚያስጠብቅ የሰው ልጅ መብት ጥበቃ ለዛሬው ዘመን ብቃት ይደርስ ዘንድ የሚታገል ክቡር ሙያ ነው:: በደርግ ዘመን ግፎችን በልጅነቴ ለጋርዲያን ከመላክ ጀምሮ በመገናኛ ብዙሃን ተከታታይነትና ቆይቶ ተባባሪነት የምወደው ሙያ ሲሆን በሃገራችን የሙያ ማህበራቱ ኢነጋማና ኢጋማ ብለው መከፋፈላቸውን ባልወድም ከሁለቱም በነበሩ ጋር ትብብር ነበርኝ:: የማስተባብረው መንፈሳዊ ጋዜጣ በውጭ ስለሚታተም በህጋዊነት ፈቃድ ማግኘት ባልችልም በብዙዎቹ ጉዳዮች ስሳተፍ ቆይቼ በአክራሪዎች ዛቻ ለስደት ብዳረግም ከመብት አስጠባቂዎቹ ጋር የወገኖች አፈና ይቆም ዘንድ ስታገል ቆይቻለሁ ወደፊትም ክንዴን እስከምንተራስ ድረስ ቀጥላለሁ::በስደት አለም በማህበራዊና በህትመት ሚዲያዎች ኣመደኛ ሆኘ ያን አፋኝ አገዛዝ ስፋለም የነበረ ሲሆን ለጋዜጠኖች መብት ለሚታገለው CPJ ብዙ ጊዜ በማሳሰብ ቆይቼ ወደውጭ ለስደት ብበቃም በየማህበራዊ ሚዲያ ዛሬም በመሳተፍ ላይ ነኝ:: የጋዜጠኞች ማሀባሩ ኢጋማና ኢነጋማ ብለው መከፋፈላቸውን ሳልቀበል በሁለቱም ከሚገኙ ወዳጆቼ ጋር ስተባበር ቆይቻለሁ:: አፋኙ ወያኔም ዋና አሳታሚያችን በውጭ ሃገር በመሆኑ ፈቃድ ከልክሎኝ ነበር:: ይህ የሚዲያ ሰዎች ህብረት በጣም ተፈላጊ የሚሆነው የተጀመረው በጎ ለውጥ ለውጥ በትክክለኛ መንገድ ይሄድ ዘንድ ስለሚረዳና ግፉ ካገረሸም በህብረት ለመታገል ይጠቅማልና በርቱ:: የአውስትራሊያው ካሳሁን ሰቦቃ የጦማር አዘጋጅ የነበረው የኢሳት ትንታግ ርእዮትንም የዘሃበሻው በሳል ጋዜጠኛ ሄኖክና በዳያስፖራ ያሉት የሚዲያ ሰዎችንም አትርሱ::

    Degome Moretew
    May 25, 2019 at 10:12 pm
    Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.