የታማኝ በየነ የጌድኦ ጉብኝት (ቪዲዮ በሸዋንግዛው ወጋየሁ)

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቀለው የሚገኙ ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም ማቀዱን ዓለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት የተሰኘው በጎ አድራጊ ድርጅት መስራቾች እና አመራሮች ገለፁ። አመራሮቹ ይህን የገለፁት ዛሬ በደቡብ ክልል ጌዲኦ ዞን ገደብ ወረዳ በመገኘት የተፈናቀሉ ዜጎችን በጎበኙበት ወቅት ነው። በጉብኝቱ ላይ አለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጲዊያን መብት ዳይሬክተር እና የመብት ተሟጋች ታማኝ በየነ የተፈናቀሉ ዜጎች የሚገኙበት ሁኔታ ስሜትን የሚነካ ሆኖ እንዳገኘው ገልጿል። በጌዲኦ ዞን የገደብ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አየለ ማጎ ድርጅቱ በዞኑ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ለሚገኙ ዜጎች ላበረከተው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በዛሬው ጉብኝት ከአለምአቀፍ ትብብር ለኢትዮጲዊያን መብት መስራቾችና አመራሮች በተጨማሪ ወርልድ ቪዥን የተባለው ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ኤድዋርድ ብራውንም መገኘታቸውን በስፍራው የሚገኘው ወኪላችን ሸዋንግዛው ወጋየሁ ዘግቧል። – DW

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.