“ይህ ሴራ ሆን ተብሎ የተቀነባበረው አብይ በሚመራው ፓርቲ በኢህአዴግ ነው።” – አቤል ዋበላ

Filed under: ነፃ አስተያየቶች |

አሁን ተሰራ የሚባለው ወንጀል የተቀነባበረ ሴራ እንጂ መፈንቅለ መንግስትም ሆነ የሽብር ስራ አይደለም። ወንጀሉን አቀነባበሩ የተባሉ ግለሰቦችም የሴራው ተጠቂ እንጂ የድርጊቱ ፈፃሚዎች አይደሉም። ይህ ሴራ ሆን ተብሎ የተቀነባበረው አብይ በሚመራው ፓርቲ በኢህአዴግ ነው።
አከተመ!
~~
አላማው፦
1. የአማራ ህዝብ አማራ ነኝ ብሎ በመደራጀቱ እየተጠናከረ መሆኑ ስላስፈራው ትግሉን ለማኮላሸትና ህዝቡ ዳግመኛ አይደለም መታገል አማራ ነኝ ብሎ መናገር እንኳ እስኪፈራ ድረስ ተሸማቆ እንዲቀር በፀረ አማራ አቋም የታሸ ሴራ ነው።
2. የአማራ ህዝብ ከሚደርስበት ተደጋጋሚ ብሄር ተኮር ጥቃት ራሱን መከላከል እንዳይችል ሲባል ለራሱ ደህንነት ሲል የሚያሰለጥነውንና ያሰለጠነውን ሚሊሻ፣ ልዩ ሃይልና አድማ በታኝ በሽብርተኝነት ከስሶ ለማሰር፣ አመራሮቹን ለማሰር (አንዳንዶቹንም ለመግደል)፣ የክልሉን ህዝብ ትጥቅ በማስፈታት ወረራን ፈፅሞ መመከት እንዳይችልና ያለምንም ስጋት ወራሪው ወረራውን እንዲፈፅም ለማስቻል ነው።
3. በትግራይና በአማራ ክልል መካከል ያለውን አለመግባባት ለማባባስና ሁለቱ ህዝቦች እርስ በርስ የበለጠ እንዲካረሩ፤ እንዲሁም የአማራን ህዝብ ለመውረር በሚደረግ እንቅስቃሴ ውስጥ ከትግራይ ጋር የሚፈጠረው መካረር እንዲያግዝ፤ ብሎም የክልሉ ሃይልም ሆነ ህዝብ በሁሉም አቅጣጫ ጥቃት እንዲከፈትበትና እንዲበታተን በማድረግ የወረራ አላማውን ለማሳካት ነው።
ለዚህም ሲባል ነው ኦሮሞ ያልሆኑ ጀነራሎችን ወይም ትግሬ የሆኑ ጀነራሎችን (ጀ/ል ሰዓረንና ጀ/ል ገዛኢን) በመምረጥ በራሱ በመንግስት ሴራ በመግደል ገዳይ ተብዬው ለመረጃ እንዳይተርፍ በመግደልና ‘ራሱን አጠፋ’ በሚል ክህደት በመፈፀም የትግራይ ህዝብ በአማራ ህዝብ ላይ ቁጣን ለመቀስቀስ የተሞከረው።
የትግራይ ህዝብም ይህን እንዳይጠረጥር የሴረኛው መንግስት መሪ ባለፈው ወደ አክሱም በመሄድ ከህወሃቶች ጋር እርቅ አውርዶና ሴራን ሸርቦ መመለሱን እናስታውሳለን። በእኔ እምነት የጀነራሎቹን ሰለባነት የህወሀት መሪዎችም ያውቃሉ። ከህወሃት ተለይተው ከአብይ ጋር በመወገናቸው በህወሀት እንደ ጠላት የሚታዩ መሆናቸውን እናውቃለን፤ ግድያው ለሰዓረ እንጂ ለገዛኢ እንዳልነበረም የምናውቀው ጉዳይ ነው።
4. ሌላው በክልሉ አመራሮች ላይ የተደረገው ግድያ በማንም ሊሳበብ እንዳይችል ተደርጎ የክልሉ አመራርና ህዝብ እንዲከፋፈል፤ እንዲሁም እርስ በራሱ እየተጋጨ እንዲዳከም ለማድረግ ነው።
5. የአዲስ አበባን ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ የሚከታተለው የአማራ ህዝብ ስለሆነ፤ እንዲሁም ከእስክንድር ነጋ ጎን በመቆሙና እስክንድርም የመጀመሪያ ስብሰባውን እንዲያደርግ ከባህር ዳር በመጋበዙ፤ አዲስ አበባን የማወረሙ ስራ ያለምንም እንቅፋት እንዲሳካ፤ ባልዴራስ በአጭሩ እንዲቀጭና ምናልባትም እስክንድር ነጋን በተቀነባበረ ክስ ከተፈበረከው የመፈንቅለ መንግስት ዜና ጋር በማያያዝ ለማሰር ወይም ለመግደል ታቅዶ ነው።
~~
ማስረጃ፦
1ኛ. የሴረኛው መንግስት መሪ በግልፅ ከእስክንድር ነጋ ጋር የማያቋርጥ መገዳደል ውስጥ እንገባለን ብሎ ዝቶ የነበረ መሆኑ፤
2ኛ. የኦፒዲኦ ህዝብ ግንኙነት የሆነው አዲሱ አረጋ “ባላደራ እና ባለተራ የሚለውን ሃይል በቅርቡ ስርዓት የማስያዝ ስራ እንሰራለን” ብሎ አዳማ በነበራቸው ስብሰባ ላይ ከተናገረ ገና ሳምንት እንኳን ያልሞላው መሆኑ፤
3ኛ. ከሳምንታት በፊት የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ሃላፊ የነበረው ጀነራል አሳምነው ፅጌ “የፌደራል መንግስት የአማራ ሃይሎችን አፍኖ ለመውሰድ ባህር ዳር ገብቶ ነበር” ሲል በክልሉ መገናኛ ብዙሃን የተናገረ መሆኑ፤
4ኛ. የሴረኛው መንግስት መሪ ደሴ ባደረገው ንግግር “ለክልሉ የምንበጅተውን በጀት ሚሊሻ ለማሰልጠን ከዋለ ልማት ከየት ይመጣል?” የሚል ነገር ካነሳ ገና አንድ ሳምንት ያስቆጠረ በመሆኑ፤
5ኛ. ችግሩ እንደተፈጠረ ከመቅፅበት፣ ያለምንም ማጣራትና ምርመራ፣ መፈንቅለ መንግስት እንደተደረገ እና አቀነባባሪውም ጀነራል አሳምነው ፅጌ ነው የሚል መግለጫ መውጣቱ፤
6ኛ. መፅሃፍ “አህዛብ በልፍለፋቸው ብዛት የሚሰሙ ይመስላቸዋል” እንዳለ ወዲያውኑ የሴረኛው ኢህአዴግ ሴሎች እየተቀባበሉ ያስተጋቡት መሆኑና ምንም አይነት የማጣሪያ ስራ ሳይሰራ ቀጥታ ወደ እርምጃ መገባቱ፤
7ኛ. ህዝብ ሳይረጋጋና ካለበት የመደናገጥ ስሜት ሳይወጣ የታቀዱ ፀረ አማራ እርምጃዎች ባናት ባናት እየተወሰዱ መሆኑ፤ (ለምሳሌ የአማራ ክልል ሰላምና ደህንነት ሃላፊ ተገድሏል፣ የአማራ ልዩ ሃይል ዋና አዛዥ ጀነራል ተፈራ ማሞ መታሰሩ፣ የክልሉ ፀጥታ ሃላፊ ጀነራል አበረ አዳሙ መታሰሩ፣ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ እየተመታ መሆኑ፣ ….)።
8ኛ. የአማራ ህዝብ በማንኛውም ህዝብ እንዲጠላና በጥርጣሬ እንዲታይ በተቀናጀና በተባበረ መልኩ በመንግስት መዋቅርም ሆነ በብዙሃን መገናኛ ሚዲያዎች ሰፊ ዘመቻ እየተደረገ መሆኑ፤
9ኛ. ምንም አይነት የመፈንቅለ መንግስት መልክ የሌለውን ድርጊት ቀድሞ ለታቀደው ሴራ ግብዓት እንዲሆን ታስቦ በማንኛውም መስፈርት ለማይገናኝ ድርጊት የማይገናኝ ስም መሰጠቱ፤
10ኛ. ከላይ በተዘረዘሩ ምክንያቶች ሁሉም የኢህአዴግ መዋቅሮች በአማራ ህዝብ ላይ የተጀመረውን የስም ማጥፋት ዘመቻ ተቀብለው ማራገባቸውም ብቻ ሳይሆን የህግ የበላይነትን ለማስጠበቅ በሚል የሚወሰደውን የዘር ፍጅት መደገፋቸው፤
11ኛ. ምንም ትስስር የሌለውን የነ ሰዓረን ሞት አሳማኝ ባልሆነ ሁኔታ ባ/ዳር ከተደረገው ሴራ ጋር ለማገናኘት መሞከሩ፤
12ኛ. በርካታ የባላደራው ምክር ቤት አባላቶች መንግስት ነኝ በሚለው አካል ተጠራርገው መታሰራቸው፤ … ወዘተ።
~~
መደምደሚያ!
~~
እየሆነ ያለው ፀረ አማራዎቹ እንዲሆን እንደፈለጉት ነው። ስለዚህ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት አዴፓ አቅም እንዳያንሰውና ሙሉ በሙሉ በኦነግ መራሹ ኢህአዴግ እንዳይዋጥ በአማራነት አለት ላይ በፅናት እንዲቆም ልናግዘው ይገባል። ሆነም ቀረም በአዴፓ ይሁንታ ብዙ ውሳኔዎችና እርምጃዎች ሊወሰዱ ይችላሉ። በዚህ ፈታኝ ወቅት የአዴፓ አማራዊ አቋም እጅግ ወሳኝ ነው። በተለይ ድርጅቱ የእነ አብይ ሴራና ተንኮል እስኪገባው ድረስ ሊነገረው ይገባል።
~~
ከዚህም በተጨማሪ ሁሉም የአማራ ወጣት የአብይን የውሸት ቅሌትና በአማራ አመራሮች እንድሁም በመላው የአማራ ህዝብ ላይ ላሳየው ድፍረት አንድ ሆኖ መነሳት አለበት። የአብይ የሴራ ፖለቲካ መጋለጥና የአማራ ህዝብ አንድ ሆኖ የአብይን ፀረ አማራ እንቅስቃሴ መመከት እንዲችል መስራት አለበት።
አለቀ ።
አቤል ዋበላ

17 Responses to “ይህ ሴራ ሆን ተብሎ የተቀነባበረው አብይ በሚመራው ፓርቲ በኢህአዴግ ነው።” – አቤል ዋበላ

 1. ማን ይመስክር የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ በሚለው የሃገራችን ብሂል የወያኔ ኢህአዲግን ግፍ በድፍረት በብሎገርነት ያጋለጠው አቤል ዋበላ የኢሃአዲግ ኦህዲድን ሴራዎች የማጋለጥ ሙሉ ብቃት ይኖረዋል:: የአብይ አህመድ እርካብ ንድፈሃሳብ በተግባር የተሞከረው የኣማአራ ብሄረተኛነት ብሎ ኣአብይ ያለኣአግባብ ባጋነነው ይልቁንስ የኣአረመኔው ኦነግጨፍጫፊዎች ድሮ በሃረር በኣአርሲ ከገደል የወረወሩት ቤቱን ያቃጠሉበት ኣአማራ ላይነው::የአሮጌው ኢሃአዲግ ግፍ ሳይረሳ አዲሱ ኢሃዲግ በማታለል ስብከቱ እየነዳ ስንቶቹ ይህን አይን ያወጣ ቅጥፈት መቀበላቸው የሚያነቁዋቸውን መስደባቸው በጣም ያሳዝናል ሞኝነታቸው ያስቃል::ዛሬ በአጣየ በከሚሴ የተካሄደውን ጭፍጨፋ ያካሄዱት የተደበቁት ኦነጎች መሆናቸውን አባ ገዳ ሰንበቶ መስክረዋል:: ስለዚህ ይህ በመፈንቅለ ስም የተሳበበውን የአማራ ጭፍጨፋ ልናጋልጥ ልንመክት የግድ ነው::ዛሬ ለወገኖቻችን ስንሰዋ እንደጦፍ ብንቀልጥምነገ በክብር ታሪካችን ህያው ሆኖ ይኖራል ሆዳሞቹ በበሉበት የሚጮሁ ኢሃአዲግ ኦህዲድን የሚመርቁ ደግሞ ለዘላለም ዘርማንዘራቸው generation succession በከሃዲነታቸው ሲያፍር ሲሸማቀቅ ይኖራል::

  Tadesse Gebre Yesus Ejeta
  July 3, 2019 at 9:50 pm
  Reply

 2. This is really shame for Abiy.

  bitew tilahun
  July 4, 2019 at 12:53 am
  Reply

 3. Dear Editor,

  Are you sure the above article is written by Abel Wabela? I don’t think so. I am not referring the content, even the phrasing tells the article is not from Abel.

  I am curious.

  Jemal Ababiya
  July 4, 2019 at 2:11 am
  Reply

  • INSTEAD OF TRYING TO SHADE SOME DOUBT ON THE WRITER, WHY DO NOT YOU TELL US WHY THE CONTENT OF THE ARTICLE IS DOUBTFUL/WRONG?

   LET ME ASK YOU THE CONNECTIONS B/N THE KILLINGS IN BAHIRDAR AND ADDIS ABABA?

   ON THE DAY OF THE MURDER, WHY ABIY`S MESSAGE WAS BROADCASTED ON AMHARA TV INSTEAD OF EBC?

   WHAT IS THE REASON FOR THE INCONSISTENT EXPLANATION ON THE STATUS OF THE SO-CALLED KILLER OF THE CHIEF-OF-STAFF?

   HOW COMES DEMEKE MEKONNEN WAS NOT INFORMED ABOUT THE SITUATION IN BAHIRDAR BEFORE HE BOARDED ETHIOPIAN TO WASHINGTON DC (BOARDING TIME IS ALMOST MID-NIGHT WHILE THE MURDER OCCURRED ALMOST SIX HOURS BEFORE)?

   WHY ALL OF A SUDDEN THE LOVE AFFAIR BETWEEN WOYANES AND OLFITES/OPDO?

   WHY IS THE SILENCE AGAINST BANK ROBER OLFITES, JO-WAR MENCHA AND THE WILD AND UNCIVILIZED KERO BUT AN AGGRESSIVE CAMPAIGN AGAINST THE INNOCENT HUMAN RIGHT ACTIVIST ESKINDER?

   WHY ALL GOVERNMENT POSITIONS AT FEDERAL GOVERNMENT, ADDIS ABABA, MILITARY AND SECURITY ARE ALL FILLED BY OLFITES/OPDO?

   meseret
   July 4, 2019 at 11:06 pm
   Reply

   • Dear Meseret,
    I think you get me wrong. I already mentioned in my comment I didn’t question the content of the article. Anyone can write the article but Abel Wabela. I read he articles on different issues. In light of this the above article is not up to his standard and level of maturity.

    Jema
    July 5, 2019 at 4:18 am
    Reply

    • I got you,man/lady.

     What you are trying to say is that this article should be written by an immature person? What made you think so? I do not care if you support/worship abiy ahmed. However, as a former supporter of this guy (as he was parroting about Ethiopia and Ethiopianism), I know how it feels when your “great leader” was criticized. However, although late, I realized how I was fooled.

     Further evidences in support of what Abel wrote:

     The response of abiy ahmed to a lady from Gedeo ( “you will go back home when I step down from office”) who told him that the forced displacement started on the day he came to power.

     His speech in response to the military coup that took place last year. “The oromos in burayou and its environs were to come to the palace to defend their government”. This statement indicates that the government does not belong to Addis Ababans.

     When thousands of Ethiopians were displaced from their homes at burayou and its environs by OLFites, “our great leader” said he was not aware of these illegal, barbric and inhuman acts.

     Meseret
     July 5, 2019 at 3:00 pm
     Reply

     • Meseret, I am not defending Abiy (Dr.). I was rather talking about Abel Wabela. you misread me, buddy

      Jemal Ababiya
      July 9, 2019 at 3:33 am

 4. Is this meant to be a conspiracy theory, or “fact”? Anyways, the መደምደሚያ is premature, simplistic and, above all, unhelpful!

  To Zehabesha editor/moderator:
  I am not media or legal expert, but I do not believe this is “freedom of expression”, nor it is an “opinion” piece. It is a mere agitation of dangerous consequences. You have the responsibility of verifying the merits/demerits (PLS READ THE መደምደሚያ again) before posting them. You cannot argue by saying “..it is the “opinion” of the writer only….”. If you argue as such, then I owe an apology to “Tigrai online”.

  Thank you!

  Kedir Setete
  July 4, 2019 at 2:29 am
  Reply

 5. ታሪክ ራሱን ይደግማል!!! የኦዴፓ/ኦነግ-ሸኔ/ጁሃራውያን የሴራ፣ የዘረኝነት እና የተረኝነት ፖለቲካ አማራን ለማጥፋት ????

  ህወሃት የትግራይ ሕዝብን ከጎኑ ለማሰለፍ የፈፀማቸው ሴራዎች፡
  የሃውዜንን ሕዝብ በደርግ ጀቶች አስጨፍጭፈዋል፣
  የአይደር ት/ቤትን በሻዕቢያ ቦንብ አስመትተዋል፣
  አሁን ደግሞ ጄ. ሰዐረን አስገደልዋል፡፡

  እኔ የታዘብኳቸው የተረኛው የኦዴፓ/ኦነግ-ሸኔ (የቀን ጅቦችን ያባረረው የራበው ጅብ) ጣምራ አገዛዝ ሴራ ደግሞ፡
  1. በኢትዮጵያውያን ላይ ወንጀል ሲያስፈጽም የነበረውን ጌታቸው አሰፋን ያላሰረበት ምክንያት ኦዴፓ ኦነግ በአማራው ላይ ሊፈጽመው ስላቀደው ወረራ እና አፈና ህወሃት አጋር እንዲሆኑት እንዳይከፉበት፣
  2. ከሕገ-መንግሥቱ ውጭ ታከለ ኡማን በአዲስ አበባ ም/ከንቲባነት ሾሟል፣ ታሪካዊና በቅርስ የተመዘገቡ ቦታዎች እንዲፈርሱ አስደርጓል፣
  3. በቡራዩ ንጹሃን ዜጎችን የጨፈጨፉትን ለሕግ አላቀረበም፣
  4. ዳቡስ ወንዝ ፍተሸ ጣቢያ ላይ የካማሽ ዞን 4 አመራሮችን ግድያ የፈፀሙትን ለሕግ አላስቀረበም፣
  5. ኦነግን ለማጠናከር ባንክ እንዲዘርፉ አመቻችቶላቸዋል፣ ከዘረፉም በኋላ በሕግ እንዲጠየቁ አላዳረገም፣
  6. በሻሸመኔ ዜጋን ዘቅዝቀው የገደሉትን ለሕግ አላስቀረበም፣
  7. በፌዴሬሽን ምክር ቤት የደቡብ ክልል የሚኖረውን የውክልና ቁጥር ለመከፋፈል የሲዳማ እና የሌሎች ብሔሮች ክልል የመሆን ጥያቄ እንዲያነሱ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፣
  8. መለስ ዜናዊ መስረቅም ሥራ ነው ብሎ አውጆ ለህወሃት/ትግሬዎች የዘረፋ ዕድል እንዳመቻችላቸው ሁሉ፤ አቢይ አህመድም የሕዝብ መፈናቀል ይኖራል እያለ በተደጋጋሚ በማወጅ የአክራሪ ኦሮሞ የተስፋፊነት ህልማቸውን በውስጠ ወይራ ንግግር አውጇል፣ ውጤቱንም ስናየው ኢትዮጵያ በሕዝብ ተፈናቃይ ቁጥር ከዓለም ቀዳሚውን ስፍራ እንድትይ አስችሏል፤ ከዚህ ውስጥ ደግሞ አብዛኛው ተፈናቃይ ቁጥር ከኦሮሚያ ክልል ጋር በተያያዘ
  9. ለሜንጫው አብዮተኛ እና ስውሩ ጠ/ሚ ጁሃር መሃመድ ለሚመራው አክራሪ፣ ፀረ-ኢትዮጵያዊ እና ፀረ-አማራ የ OMN ቴሌቪዥን ጣቢያ ማጠናከሪያ ራሳችን ከከፈልነው ግብር ላይ 58 ሚ ብር በአዳነች አቤቤ አማካኝነት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቼክ ቁጥር No CD 5926285 በቀን 14/9/11 እንዲሰጥ አስደርጓል፣
  10. አዋሽ ባንክ ይሠሩ የነበሩ ኦሮሞዎች በማምጣት ብሔራዊ ባንክን እንዲቆጣጠሩ አድረጓል፣ ንግድ ባንክ በየክልሉ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ ሲያደርግም፤ ለአማራ ክልል ተፈናቃዮች እጅግ ያልተመጣጠነ አነስተኛ ድጋፍ እንዲያገኙ እና እንዳይቋቋሙ አስደርጓል፣
  11. የጌዲዮ ብሔር ተወላጆች እጅግ ከመጠን ባለፈ እንዲፈናቀሉ፣ እርዳታ እንኳ እንዳያገኙ ዜናው ታፍኖ እንዲቆይ እና በረሃብ እንዲሰቃዩ አስደርጓል፣
  12. የጠ/ሚ አቢይን/ኦዴፓ/ኦነግ ጥምር አገዛዝ ሴራ የሚያጋልጡትን የኢሳት ጋዜጠኞች እንዲቀነሱ አስደርጓል፣
  13. ኦነግን የመከላከያ ልብስ አስለብሶ፣ የመከላከያ ተሸከርካሪ እና የመሣሪያ ትጥቅ በጄ.ብርሃኑ ጁላ ኣማካይነት እንዲታጠቁ አስደርጎ – የወሎ አማራዎች ላይ ጥቃት እንዲፈጸም አስደርጓል፣
  14. የሰሜን ተራሮች ፓርክ በየአቅጣጫው እሳት እንዲለኮስበት ሲደረግ – ምንም ትንፍሽ አላለም፣

  የተረኛው (የቀን ጅቦችን ያተካው እና ሁሉንም የኛ የሚለው የራበው ጅብ) ዘረኛ የኦሮሞ ክፍል ጥምር የአገዛዝ በአማራ ሕዝብ፣ በኢትዮጵያዊነት እየፈፀመ ያለው ሴራ፡
  በኦዴፓ አማካኝነት የማዕከላዊ መንግሥቱን ቁልፍ ቦታዎች ተቆጣጥሯል፣ የኦነግን አክራሪ ተገንጣይ፣ አስገንጣይ ኦሮሞዎችን ሳይቀር በዓለም አቀፍ ቦታዎች ላይ ሰይሟል፡፡
  በሜንጫው አብዮተኛ እና ስውሩ ጠ/ሚ ጁሃር መሃመድ በሚመራው የ OMN ቴሌቪዥን አክራሪ፣ ፀረ-ኢትዮጵያዊነት፣ ፀረ-አማራነት ፕሮፖጋንዳ ያሠራጫል፣ የገንዘብ ችግር እንዳይገጥመው እኛው (መላው ኢትዮጵያውያን) ከከፈልነው ግብር ላይ፣ በገቢዎች ሚኒስትሯ በአዳነች አቤቤ አማካኝነት 58 ሚ ብር እንዲሰጠው ተደርጓል፡፡ ይህም ከጠ/ሚ አቢይ/ኦዴፓ ጋር አንድ እንደሆኑ ማሳያው ነው፡፡
  በ ኦነግ አማካይነት ፀረ-ኢትዮጵያዊነት፣ ፀረ-አማራነት ሽብር ያስፈጽማል፣ ኢትዮጵያን የመገንጠል ህልሙን ለማሳካት በኦሮሚያ ውስጥ የሚኖሩ ሌሎች ብሔሮች እንዲፈናቀሉ ያስደርጋል፡፡ ለዚህም በጠ/ሚ አቢይ/ኦዴፓ አመራር ወታደራዊ ትጥቅ እና ስንቅ የበጀት ድጋፍ በቀጥታ አደረገ እንዳይባል ባንክ እንዲዘርፍ ሁኔታዎች ተመቻችቶለታል፣ ተጠያቂም አልተደረገም፡፡
  አሁን ደግሞ በኦሮሞ ስም የተደራጁትን የፖለቲካ ድርጅቶች አንድ አድርጎ የኦነግን ወታደራዊ ክንፍ አናውቀውም፣ እኛን አይወክለንም የሚል የሽፋን መግለጫ በማውጣት በአደራ አስቀምጦታል፡፡ አልፎ አልፎም ትጥቅ አስፈታን እያለ የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ይሠራል፡፡
  ኢትዮጵያውያንን ሲያሳስር፣ ሲያስደበድብ፣ ጥፍር ሲያስነቅል፣ በግብረ ሰዶማውያን ሲያስደፍር፣ ሲያኮላሽ፣ ሲያስገድል የነበረውን ጌታቸው አሰፋን ተደጋጋሚ የፍርድ ቤት መጥሪያ ቢወጣበትም እስካሁን ያላሳሰረበት ምክንያትም፤ የኦዴፓ/ኦነግ/ጁሃር ጥምር አገዛዝ ለሚፈጽመው ፀረ-አማራ እንቅስቃሴው ህወሃትን እንደ ስትራቴጂካዊ አጋር በመቁጠር ነው፡፡
  የጠ/ሚ ፀረ-አማራነት እርምጃው ህወሃት ከ አንድ ሚሊዮን በላይ ልዩ ሃይል አና ሚሊሻ፣ ኦዴፓም በየ 3 ወሩ ልዩ ሃይል ሲያስመርቁ ምንም ትንፍስ ሳይል፤ አማራ ልዩ ሃይል በማስመረቁ በጀቱን ለሚሊሻ ማሰልጠኛ አዋሉት ብሎ በቁጭት በመናገር ብቻ አላቆመም፡፡ አማራውን ዳግም እንዳይነሳ አድርጎ ለማጥፋት ረጅም ጊዜ ተወስዶ፣ በጥንቃቄ ተጠንቶ እና ታቅዶ የተሠራ የሽብር ሴራውን ፈፀመ፡፡ የሴራው አካሄድም፡
  • መከላከያ በ 5 ዕዝ (ሰሜን፣ ደቡብ፣ ምሥራቅ፣ ምዕራብ እና ማዕከላዊ ዕዝ) ተብሎ የነበረውን ወደ 4 ዕዝ በማውረድ ባሕርዳር ላይ የነበረውን ማዕከላዊ ዕዝ በመበተን መቀመጫውን መቀሌ ባደረገ ጄ. ብርሃኑ ጁላ በሚመራው የሰሜን ዕዝ እንዲጠቃለል፣ ባሕር ዳር የነበረውን ሠራዊት አንስቶ ትግራይ ውስጥ በነበረ ሌላ ሠራዊት ቀደም ብሎ ተተክቶ ቦታውን እንዲይዝ አደረገ፤
  • ሰኔ 15 ቀን በአቢይ አህመድ በተመራ የተቀነባበረ ሴራ እና ሽብር፣ የአማራ ልዩ ሃይል ዩኒፎርም በለበሱ የመከላከያ ሠራዊት አማካይነት በፈፀመው ክልላዊ መፈንቅለ ስልጣን ጄ. አሳምነውን እና የአዴፓ አመራሮችን አሳፍኖ አስገደለ፤ ራሱ የመራውን የሴራ ሽብር ጄ. አሳምነው ጽጌ እንደፈጸመው ተደርጎ መፈንቅለ መንግሥት ብሎ በመሰየም ዜና እንዲሠራ አስደረገ፣
  o በዚህም ሰበብ አማራ ራሱን የሚከላከልበት ሃይል እንዳይኖረው ልዩ ሃይሉን ማጥፋት፣
  o አማራን አንድ አድርጎ የሚመራው አመራር እንዳይኖር ተገዳዳሪ አመራሮችን ገድሎ በአድርባዮች መተካት እና የአማራን አንድነት መበተን፣
  o ወጣቱ በአማራነቱ እንዳይደራጅ በጅምላ ማሠር፣ ማሳደድ እና አማራውን የሚያደራጀውን አብንን ቢችል ማጥፋት፣ ካልቻለ ማዳከም፣
  o በአዲስ አበባ ላይ የይገባኛል ጥያቄ እንዳይነሳ የባልደራሱ ባላደራ ምክርቤት ባሕርዳር ላይ ሰኔ 16 ሊያደርገው የነበረውን ጉባኤ ማጨናገፍ፣ የአዲስ አበባ ኬኛን ትርክት ያለተቀናቃኝ ለማስፈፀም የባላደራ ምክር ቤት አባላቱን ማሰር፣
  o የጠ/ሚ/ኦዴፓ/ኦነግ/ጁሃር ሴራዎችን የሚያጋልጥ ሜዲያ እንዳይኖር ቀድሞ የኢሳት ጋዜጠኞች እንዲባረሩ አስደርጓል፣ በዚህ ሽብር ሰበብ ደግሞ የአሥራት ሜዲያን ለመክሰስ ጋዜጠኞቹን እና መሥራቾቹን ማሠር ወዘተ …. ጉልህ ማሳያዎቹ ናቸው፡፡

  Meyisaw
  July 4, 2019 at 9:01 am
  Reply

 6. Really is this analyst Abel ? shame on u. there is something wrong in ur mental this days.

  tesfata
  July 4, 2019 at 3:52 pm
  Reply

 7. በምንም አይነት መስፈርት ዶ/ር አብይ በሴራ ፓለቲካ ይሳተፋሉ የሚል እምነት የለኝም። ግን የሃገራችን ፓለቲካ በሸር እና በዘር የተሰመረ በመሆኑ አፍጦ የቆመን እውነት እንኳን ለማመን ሰዎች አልቻሉም። ችግሩ የመነጨው ገና ከጅምሩ ነው። ኢንጂኒየር ስመኘው ሲገደሉ፤ ከዛም ቀደም ብሎ የናይጀሪያው ኩባኒያ ሥራ አስካሄድ ከነሾፌራቸውና ረዳታቸውን ጨምሮ በጥይት ሲመቱ እንዲህ ነው ለማለት መንግሥት ባለመከጀሉ ሁሉን ነገር ጥርጣሬ ላይ ጥሎታል። በሃገሪቱ የቆየ ታሪክ እንደ ዶ/ር አቢይ ያለ ህዝብ ወዳድ መሪ ተነስቶ አያውቅም። በየሄደበት ሃገር ሁሉ ዘርና ቋንቋን ሳይተግን የታገቱትን ያስፈታ፤ የእምነት ግጭት ላይ የነበሩትን ያስታረቀ፤ ወያኔ ለዘመናት በእስር ጨለማ ቤት ያጎራቸውን የለቀቀ፤ በጎረቤት ሃገርና በሌላም ስፍራ የነበሩ ጠበንጃ አንጋች ተቃዋሚዎችንና ጀሌዎችን ኑ ሃገር ግቡ በማለት ነገርን ያረገበ ጀግና መሪ ነው።
  የሃበሻው ፓለቲካ ግን ጠንጋራ ነው። በሙሉ ዓይን ነገርን ማየት አይችልም። በስልጣን ላይ ያሉት ሰዎች እንዴት ያስተዳድራሉ ከማለት ይልቅ ከእነ ማን ወገን ናቸው ብሎ አሰላለፍን ማሳመር ይወዳል። የዶ/ር አብይ ከኦሮሞ ህብረተሰብ መውጣት እስይ የሚያሰኝ እንጂ የሚያዘልፋቸው አይደለም። ግን በጠ/ሚሩ የአመራር ስልት ያኮረፉ የወስላታ መንጋ የውሸት ጥሩንባ እየነፉ እኛን ስሙን በማለት በውጭና በሃገር ውስጥ ሰውን ያማታሉ። እውነቱ ግን እውነት እንደሆነ ይኖራል። ዶ/ር አቢይ ጄኔራል ጻረ መኮነንና ሌሎችን አስገደለ ብሎ መወንጀል የወያኔ ርዝራዦችና የተባራሪ የፓለቲካ ትራፊዎች ወሬ ነው። ይህ ሴራ ጠ/ሚሩን እጅ ከወርች አስሮ ብለናችሁ ነበር ምንም ማድረግ አይችልም ለማለት የተተለመ ዘመቻ ነው። አቶ ለማ መገርሳም ሆነ ጠ/ሚሩና የአስተዳደር ባልደረቦቻቸው ለሃገር አንድነትና ለህዝቦች ውህደት አይሰሩም ብሎ ማሰብ ራስን መካድ ነው። ዝብ ብሎ በስማ በለው በተናፈሰ የፈጠራ ወሬ ከመደናበርና በዘር ከመሰለፍ ይልቅ የጠ/ሚሩን አመራር በመደገፍ ለአንዲትና ለተጠቃለለች ሃገራችን እንስራ። ሌላው ወሬ ሁሉ የወስላቶች ፓለቲካ ነው!

  Tesfa
  July 4, 2019 at 5:45 pm
  Reply

 8. FANO killed Asaminew , Ambachew and the other 40 + people in Gondar while the Tigre heiress killed the two generals in Addis Ababa with their bodyguards and few days later killed another General Abraham Woldemariam making this similar to the events of the 70’s declaring war against the older generations .

  This recent events/coup were not ethnic
  fights but signs of the begining of the intergenerational fights, performed by the young generations against the older generations same as the 1970’s young Ethiopian students who killed tens of thousands of the older Ethiopians in the 70’s.

  Abiy is the middle aged “sandwich generation” who is between the old generation and the young generation yet unable to bring the young to stop it’s actions against the old.

  FetaAsmechiw
  July 4, 2019 at 11:52 pm
  Reply

 9. What a wonderful inside information with irrefutable evidence. You think you know everything, Abel. Your contempt for Dr. Abiy is well taller than your height. Chiba.

  Genene Wagne
  July 5, 2019 at 1:14 pm
  Reply

 10. ውድ አቤል
  ያንተን ትንተናዎች በጣም አከብራቸው ነበር፡፡ በዚህ ትንተናህ ግን አልስማማም፡፡ በየትኛውም መለኪያ አንተ ያቀረብካቸውን ማሳመኛዎች እንኳን እኔ አንተም የምታምንባቸው አይመስልም፡፡

  Assefa
  July 8, 2019 at 1:08 am
  Reply

 11. ሁሉም ስራ ውጤታማ ሊሆን የሚችለው በተገቢው ባለሞያ ሲሰራ ነው ለምሳሌ ልህክምና ወደ ሐኪም ዘንድ የሄደ ህመምትኛ ህክምና ሊደርግለት የሚገባው ጉዳዩ በሚመለከተው ሐኪም እንጂ በሐኪም ቤቱ አትክልተኛ ወይም ሾፌር ሊሆን አይችልም በትመሳሳይ ሁኔታ ማናቸውም አይነት ጥፋት ወይም ወንጅል ሲሰራ ሊመረመር የሚገባው በተገቢው ባላሞያ ሊሆን ይገባዋል የዚህ ፅሁፍ አቅራቢ የምርመራ ባለሞያ ስለመሆኑ ምንም ማስረጃ አላቀረበም የምርመራ ባለሞያ እንኩዋን ቢሆን ምን ዓይነት የምርመራ ዘዴዎችን እንደተጠቀመ ለምን እንዚህን ዘዴዎች እንደመረጠ ምን ውጤት እንዳገኘ የምርመራ ግኝቶቹን በተጨባጭ ማስረጃ አላስደገፈም ማስረጃ ተብለው የቀረቡት ነጥቦች ከግል ግምትና መላምት ያልዘለሉ ናቸው ከህግ አንፃርም አንድን ሰው ወይም ቡድን ወንጀለኛ ውይም ነፃ ብሎ የመበየን ስልጣን ያለው ፍርድ ቤት ብቻ እንጂ አንድ ዜጋ ሌላውን ዜጋ በግል ስሜት ተነሳስቶ ወንጀለኛ ወይም ሴረኛ የማለት መብት የለውም ማንም ሰው የማንንም ሰው ሃሳብ ምክንያታዊ በሆነ ክርክር መቃወም መብቱ ነው ባልተጨበጠ መረጃ ስም ማጥፋት ግን ህገ ወጥም ነውርም ነው በመጨረሻም ጠንካራ ኢትዮጵያ ልትኖር የምትችለው ሁሉም ዜጎች ጠንካራ ሲሆኑ ብቻ ነው ጠንካራ አማራ ጠንካራ ትግሬ ጠንካራ ኦሮሞ ጠንካራ ሶማሌ ጠንካራ አፋር ጠንካራ ብሔሮችና ክልሎች ሳይኖሩ ጠንካራ ኢትዮጵያ ልትኖር አትችልም ማንኛውንም ብሔረሰብ ማሽመድመድ መላው ኢትዮጵያን ማሽመድመድ ነው ከእንግዲህ ወዲያ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ከዱሞክራሲ እና እኩልነት ውጪ የማንኛውም ብሔር ወይም ቡድን የበላይነት ሊታሰብ የማይችል ያበቃለ እና የሞተ በመሆኑ በዚህ የሞተ ሃሳብ ተድፍቃችሁ ያላችሁ ወግኖች ካላችሁ ከዚህ ህይወት አልባ ተረት ተላቃችሁ በተጨባጩ ዓለም ላይ ካለው እውነታ ጋር ታርቃችሁ በቀሪ የህይወት ዘመናችሁ ትውልድ ተሻጋሪ ስራ እንድትሰሩ እና መጪው ትውልድ በፍቅር እና በአርአያነት እንዲያስባችሁ ታደርጉ ዘንድ በአክብሮት እጠይቃችሁአለሁ ሁሉም አላፊ ነው ሀገርና ህዝብ ግን ዘለዓለማዊ ናቸው
  ልዑል እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቡን ይባርክ!
  አሜን!

  ታሜ
  July 8, 2019 at 5:25 am
  Reply

  • It is reasonable to comment on the writer`s contribution. However, your comment is not balanced as you seem to trust what the government of abiy said. As is well known, the security, media and bureaucracy of the woyane regime is still intact except that the top TPLF cadres were replaced by narrow nationalist opdo cadres. If we say the media propaganda of the last 27 years were all lies, how can we then trust the media propaganda of the oromo government?

   meseret
   July 8, 2019 at 10:00 pm
   Reply

 12. ይሄ እንዴት ማስረጃ ተብሎ ይቀርባል ። ተራ ኢሉዥን ከመሆን ያለፈ አይደለም ።

  visionary
  July 10, 2019 at 7:52 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.