ኤርሚያስ ለገሰ የባላደራ ም/ቤቱን ከ ሀላፊነት ጋር ተቀላቀለ – ህብር ራዲኦ

1 min read
6

አቶ ኤርሚያስ ለገስ በአዲስ አበባ ጉዳይ ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ባለአደራ ኮሚቴን በም/ል ሀላፊነት እንዲያገለግል ተሾመ፣ቁርጠኝነቱንም በደስታ ገለጸ።

በጋዜጠኛ እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ እስክንድር ነጋ የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ ባለ አደራ ኮሚቴ (ባልድራስ) ዛሬ በሰሜን አሜሪካ አትላንታ ከተማ በቨርጂኒያ ጎዳና በሚገኘው ቦሌ ሬስቶራንት በ ወቅታዊ ጉዳዬች ዙሪያ በተጠራው የምክክር መድረክ ላይ የምክር ቤቱ ዋና ሰብሳቢ የሆነው እስክንድር ነጋ ከአ/አ በቪዲዬ ባስተላለፈው ምልእክቱ ኤርሚያስ ለገሰ ም/ቤቱን ከውጪ ሆኖ በሁሉም ዘርፍ እንዲያገለግል መሾሙን ገልጿል።

ኤርሚያስ ባህር ማዶ(አሜሪካ)ሆኖ የባላደራ ም/ቤቱን እንዲመራ ለምን አስፈለገ?ለሚለው የበርካቶች ጥያቄ ጋዜጠኛ እስክንድር በሰጠው ምላሽ”በአሁኑ ወቅት በም/ቤቱ አመራሮች እና አባላት ላይ ከፍተኛ የማዋከብ እና የእስራት ዘመቻ በመክፈት ላይ በመሆኑ ኤርሚያስ ም/ቤቱን ከውጪ ሆኖ እንዲረዳ እና አዲስ አበባ ለነዋሪዎቿ የሚለውን አላም እንዲያስቀጥል በማሰብ ነው”ብሏል።

የኢሳት ባልደረባ የነበረው እና “በመርህ ልዩነት” ድርጅቱን ለቀው ከወጡ ጋዜጠኞች ጋር ኢትዬ 360 ቻናልን በመክፈት ከሚንቀሳቀሱት መካከል አንዱ የሆነው ኤርሚያስ ለገሰም ከእስክንድር ነጋ እና ከባልድራስ የቀረበለትን ሀላፊነት በጥልቀት ከመረመረው በኃላ በደስታ መቀበሉን ገልጿል።

በቀደመው ጌዜ (እኤእ ከ2009 በፊት) በ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የአቅም ግንባታ ኃላፊ፣ በአ/አ የኢሕአዲግ የህዝብ ግኑኝነት እና የአባላት ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ፣ በአ/አ አስተዳደር የምክር ቤት አባል እና የ መንግስት የኮምንኬሽን ጉዳይ ጽ/ቤት በምክትል ሚኒስትርነት ያገለገለው ኤርሚያስ ለገሰ በስደቱ አለም የመለስ ቱርፋት(ባለቤት አልባ ከተማ) እና የመለስ ልቃቂት የሚሉ ሁለት ተወዳጅ መጻሕፍቶችን ለንባብ ማቅረቡ ይታወሳል።

በተለይ ደግሞ የመለስ ቱርፋት፣ባለቤት አልባ ከተማ በሚለው ባለ 400 ገጽ መጽሐፉ ውስጥ የቀድሞው ጠ/ሚ/ር አቶ መለስ ዜናዊ ከምርጫ 97 በፊት ሆነ በሁዋላ ብዛት ያለው የአዲስ አበባ ከተማ መሬትን በኢንቨስትመንት ስም እንዴት ለህዋት ደጋፊዎች ሸንሽነው እንዳከፋፈሉት በተቃራኒው ለዘመናት ከአ/አ ከተማ ጋር የተቆራኘው ነዋሪዋን ለቤት አልባነት እና የጎዳና ላይ ተዳዳሪነት እንደዳረጉት ኤርሚያስ በመጽሐፉ ውስጥ በግልጽ አስቀምጦታል። መጽሐፉም በወቅቱ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ታግዷል።
ከቀደመ ዘርፈ ብዙ ልምዱ እና ከቁርጠኝነቱ አኳያ ኤርሚያስ ለገሰ የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት አላማዎችን እና እንቅስቃሴዎችን በማሳካት ረገድ ጉልህ ሚና ሊጫወት ይችላል ተብሎ በስፋት ይጠበቃል።

ህብር ራዲኦ