“በአሁኗ ኢትዮጵያ በፀረ ሽብር ሕጉ ክስ መኖር የለበትም” ዳንኤል በቀለ

1 min read

የሰብአዊ መብት ተሟጋችና ጠበቃ ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) በሂውማን ራይትስ ዋች ውስጥ በተለያዩ ኃላፊነቶች አገልግሏል።
እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ2011 እስከ 2016 የተቋሙ የአፍሪካ ክንፍ ዋና ዳይሬክተር ነበር። ኦክስፋም፣ አርቲክል 19፣ የዓለም ባንክ እና ዩኤስኤድን አማክሯል።

በበርካታ የሲቪል ማኅበራት ውስጥ የሠራው ዳንኤል፤ የ97ቱ ምርጫ ነጻ እንዲሆን እንዲሁም ሰብአዊ መብት እንዳይጣስ ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል። ከምርጫው በኋላ የተፈጠረውን ቀውስ ለማርገብም ሞክሯል። በዚህም ለእሥር ተዳርጎ ነበር።
እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር 2009 ላይ ላይ ‘አሊሰን ደስ ፎርጅስ አዋርድ ፎር ኤክስትራኦርዲነሪ አክቲቪዝም’ የተሰኘ ሽልማት አግኝቷል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የመጀሪያ ዲግሪውን በሕግ፣ ሁለተኛ ዲግሪውን ደግሞ በሪጅናል ዴቨሎፕመንት ስተዲስ አግኝቷል። በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ በሌጋል ስተዲስ ሁለተኛ ዲግሪ የያዘ ሲሆን፤ ፒኤችዲውን በዓለም አቀፍ ሕግ አግኝቷል።
ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ባለፈው ማክሰኞ ሰኔ 25/2011 ዓ. ም. በኢትዮጵያ መንግሥት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ሆኖ ተሹሟል። ይህንን ተከትሎም ከቢቢሲ አማርኛ ጋር ቆይታ አድርጓል፤ እነሆ . . .

እሾማለሁ፤ ያውም ባሰረህ በኢህአዴግ መንግሥት እሾማለሁ ብለህ አስበህ ታውቃለህ? ይህ ቀን ይመጣል ብለህ ታስብ ነበር?
ዳንኤል በቀለ፡ ይህ ቀን ሊመጣ ይችላል ብለህ ታስብ ነበረ ወይ? ለተባለው ኢትዮጵያ ውስጥ የዚህ አይነት ለውጥ ሊመጣ ይችላል ብለህ ታስብ ነበር ወይ? ማለት ከሆነ፤ አስብ ነበር። እንደሚመጣ ይሰማኝ ነበር። እኔ ራሴ ግን ያለሁበትን ሁኔታ ከሆነ ይህንን በተለየ አስቤው አላውቅም።
ይሄኛውን [በኢህአዴግ መንግሥት መሾምን] በጭራሽ አስቤ አላውቅም በእውነት። እመኝ የነበረው ለአገሬ

BBC Amharic