“ቴዲ አፍሮ ከመወለዱ በፊት እናት እና አባቱን ነው የማውቀው” አለምፀሐይ ወዳጆ

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

ቴ ዲ አ ፍ ሮ
በአለምፀሐይ ወዳጆ

…… ከዛ በኋላ ቴዲን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት አሜሪካን ሀገር ለመጀመሪያ ጊዜ ሲገባ አለምፀሐይ ቤት ውሰዱኝ ይልና ለኔ ማንም ሳይነግረኝ ዲጄ መንጌ ቤትሽ እየመጣሁ ነው አለሽ አለኝ አለሁ አልኩት ሲመጡ ከቴዲ ጋር ናቸው። “ቴዲ እኔ እኮ ትንሽ ሆነህ ነው የማውቅህ መወለድህን የማወቀው ከዛ በቀር አላውቅክም” አልኩት። ቴዲ የጥበብ ሰዎችንና ሌሎች ታላላቆቹንም እንዴት እንደሚያከብር ልናገር ስለፈለኩ ነው ይሄን የምናገረው። ከዛ “አንቺ ለነሙሉቀን ለቴዎድሮስ ታደሰ ግጥም ስትጽፊ ኖርሽ እኔ በእነሱ ዘፈን ነው ያደኩት አንቺን ሳላመሰግን አሜሪካን መድረክ ላይ አልወጣም ብዬ ነው የመጣሁት” አለኝ ደነቀኝ ።
….የኔ ልጅ እዚህ ተወልዳ በሁለት አመቷ እዚሁ ተመልሳ ነው ያደገችው ቴዲን ነው የምታውቀው በቴዲ ፍቅር ያበደች ልጅ ነው ያለችኝ ቤት መጥቶ እሷ ከት/ቤት ስትመለስ “ቴዲ አፍሮ እኮ ነው እማማዬ” አልኳት ቦርሳዋን ወረወረች ስልኩን ጨበጠች “Guess what “እያለች ለመንደሩ ልጆች በሙሉ “Teddy Afro is in our house” ትጩዋለች ትጩዋለች ቤቱ አልበቃ አላት። ቴዲ ጠራና አቀፈ ሳማትና “እንዴ የአንቺ እናት እኮ ከኔ በላይ እውቅ ናት” ሲላት “No way” አለች የማይመስል ነገር አትንገረኝ ማለቷ ነገር ነው እሷ ደሞ የእኔን አታውቅም ቴዲ እኔን አክብሮ ነው የመጣው።
…. ቴዲ ሰው ገደልክ ተብሎ አሜሪካን ሀገር መጥቶ ክሱ ከተመሰረተበት በኋላ አንድ የቤተክርስቲያን ዝማሬ ሰርቶ አለም አዳምጪልኝ አለኝና ምሳ በልተን መኪና ውስጥ እሱን እያዳመጥን ወደ ኤርፖርት እንሄዳለን ወደ አዲስ አበባ ሊመለስ ማለት ነው። ቅር እንዳይለኝ ሳልለው እንዳላልፍ ብዬ “ቴዲ ወያኔ ፋይል ከፍቶብካል ይሄን ታውቃለክ ወጥተህ የምትቀር ስለመሰላቸው ለቀውካል ስትመለስ ግን የሚጠብቅክን ነገር ገምተካል?” አልኩት “አዎ አለም ስንቶቻችን ጠፍተን ተሰደን እንለቅ መሞት ካለብኝ እኔ ሞቼ ይቺ ሀገር ነፃ መውጣት አለባት እኔ አባቴ ያስተማረኝ ኢትዮጵያን የማውቃትን ስለ እሷ እሱን እየተናገርኩ መኖር አለብኝ።” ብሎ ተመለሰ አልቀረለትሞ ታሰረ።
…. ታስሮ ሁሉም አለፈና ለ SEED ሽልማት እዚህ መጣ እንደገና አገኘውትና እኔ ቤት ራት እንበላለን እጄ ላይ ስልክ ተደወለ ከካናዳ ነው የማላውቀው ሰው “ቴዲ interview ሰጥቶ ነበር እንዴ VOA ላይ” ይለኛል” አዎ” አልኩ “በዛ VOA ላይ በሰጠው interview ባለሥልጣኖች ቡና ቤት ውስጥ ሆነው እስቲ እሱ ያላትን ኢትዮጵያ እዚህ መጥቶ ያስረዳናል ሲሉ ስለሰሙ እባክህ ንገር ብለውኝ ነው እንደው ካገኘሽው” አለኝ እኔ ቤት ነው ያለው ቴዲ በዛ ሰዓት ላይ መመለሻው በማግስቱ ነው .. ደነገጥኩ ዝም ብል እንዴት ሰምተሽ ዝም አልሽ ልባል ነው ብናገር ድጋሚ በዛ ጊዜ የተናገርኩትን ነገር ነው የምናገረው እና Kitchen ውስጥ አምለሰትን ጠራዋት “አምለሰት አንድ ሰው ደወለልኝ እና እንዲህ ይለኛል ምን ታስቢያለሽ?” አልኳት “ንገሪው” አለችኝ ጠራነው “ቴዲ” አልኩት “የማላውቀው ሰው ከካናዳ ደወለ VOA ላይ የሰጠከውን ቃለምልልስ የወደዱልህ አልመሰለኝም የሆኑ ባለሥልጣናት ሲፎክሩብህ ነበር መጠጥ ቤት ሆነው ይሄን የሰማ ሰው ነው ንገሪው የሚለው” አልኩት “ውይ አለም እንኳን እኔ ልጠፋ የአንቺ መምጫ እኮ ደረሰ። ” አለኝ። … ሀገሬ ስገባ ከሁለት ቀን በኋላ ደወለ “ቴዲ ነኝ አለም እንኳን ደህና ገባሽ ልልሽ ነው ” አለኝ “ቴዲ አሁን ማን ያምነኛል እኔ ጥፋ ስልህ አንቺ መምጫሽ ደርሷል ያልከኝን ሰው ያምነኛል ብናገር ” ስለው “እኔ እኮ አይደለሁም እግዚአብሔር ስለፈቀደ ነው።” አለኝ።”

አለምጸሐይ ወዳጆ በአሜሪካን ሀገር ለቴዎድሮስ ካሳሁን የእውቅና ሽልማት ሲበረከት ከተናገረችው የተቀነጨበ።

2 Responses to “ቴዲ አፍሮ ከመወለዱ በፊት እናት እና አባቱን ነው የማውቀው” አለምፀሐይ ወዳጆ

 1. dear editor
  I know very well the father of TEDE –Kasahun

  berhanu kashun
  July 7, 2019 at 12:21 pm
  Reply

 2. “ቴዲ እኔ እኮ ትንሽ ሆነህ ነው የማውቅህ መወለድህን የማወቀው ከዛ በቀር አላውቅክም” አልኩት።
  “ቴዲ ወያኔ ፋይል ከፍቶብካል ይሄን ታውቃለክ ወጥተህ የምትቀር ስለመሰላቸው ለቀውካል ስትመለስ ግን የሚጠብቅክን ነገር ገምተካል?” አልኩት::

  … BEKIDIMIYA, YEAMARIGNAW KEY BOARD YELELEBET COMPUTER LAY HOGNE BEMETSAFE YIQIRTA (EIBET ESKEMIGEBA ALASCHIL BILOGN NEEW)

  BE-EWINET EINEZIH TIKSOCH YE ALEMTSEHAY WEDAJO NACHEWINI? KEHONU BEAMARIGNACHIN MEBELASHET BEYE TV EINA FILMOCH LAY SAYKER TAWAKI GAZETEGNOCHINA TEWANAY SIBEGNUGN (SIYANADIDUGN) YENORUTIN ETIF-DIRIB YADERGEWAL.

  TIKIS SITSAF, TENAGARIW BETIKIKIL YALEWIN MEHON EINDALEBET EDITERU YITEFAWAL BIYE ALLILIM. YEMINAWKAT ALEM ENDEZIH ADRIGA AMARIGNAWIN MABELASHET JEMIRALECH BIYE LEMAMENIM ALCHILIM. SILEZIH MABRARIYA BISETEGN BETAM DES YILEGNAL.

  GETACHEW ABERA
  July 10, 2019 at 11:19 am
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.