ትግራይ ክልላዊ መንግስት 16 ቢሊዮን 700ሚሊዮን ብር በጀት ጸደቅ

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

የትግራይ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ጉባኤ በጀትና አዋጆችን በማጽደቅ ማምሻውን ተጠናቀቀ

የትግራይ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ጉባኤ ለ2012 የስራ ዘመን 16 ቢሊዮን 700 ሚሊዮን ብር በጀትና የተለያዩ አዋጆችን በማጽደቅ ማምሻውን ተጠናቀቀ።

በምክር ቤቱ የበጀትና ኦዲት ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ንጉሰ ለገሰ እንዳስታወቁት በጀቱ የሚሸፈነው ከፌዴራል መንግስት ድጎማ ፣ከተለያዩ የውስጥ ገቢዎችና በብድር ነው።

በጀቱም በዘመኑ ለመደበኛ እና ለካፒታል ፕሮጀክት እንዲሁም ለመጠባበቂያ መደልደሉን ገልጸዋል።

ለካፒታል ፕሮጀክት ከተያዘው በጀት 61 በመቶ የሚሆነው ለድህነት ተኮር እንደሚውል ያመለከቱት አቶ ንጉሰ በዋነኛነትም ለውሃ ሃብትና ለግብርና ስራዎች ቅድሚያ መሰጠቱን አስረድተዋል።

ጉባኤው በተጨማሪም የትግራይ መልሶ ማቋቋም ተቋም ትእምት/ ተጠሪነቱ ለክልሉ ምክር ቤት እንዲሆን የሚደነግገው አዋጅ ጨምሮ የተለያዩ አዋጆች መርምሮ አፅድቋል።

ከዚህ ሌላ የክልሉ ፍርድ ቤቶች አደረጃጀት ስልጣንና ተግባር ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ በክልሉ የፍትህ ተደራሽነት ለማረጋገጥና ለህብረተሰቡ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል መሆኑን በምክር ቤቱ የህግና አስተዳደር ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢው አቶ ሞገስ ታፈረ ገልጸዋል።

የምክር ቤቱ አባላት በዚህ ረቂቅ አዋጅ ላይ ሰፊ ውይይትና ክርክር ካደረጉ በኋላ ግልፅነት የሌላቸውና ከክልሉ ህገመንግስትም ሆነ ከፌዴራሉ አዋጅ ጋር የሚጣረሱ አንቀፆች እንዳሉባት በማመልከት ለቀጣይ ተስተካክሎ እንዲቀርብ በማለት ውድቅ አድረገውቷል።

ለአራት ቀናት በመቀሌ ከተማ ሲካሄድ የቆየው ክልሉ ምክር ቤት አምስተኛ የስራ ዘመን 16 መደበኛ ጉባኤ መረሀ ግብሩን ማምሻውን አጠናቋል።

One Response to ትግራይ ክልላዊ መንግስት 16 ቢሊዮን 700ሚሊዮን ብር በጀት ጸደቅ

  1. Tigrai is on the right track to join the developed African nations.
    TPLF ARE HEROES THAT SAVED TIGRAI!!!!!!

    Kebebu
    July 7, 2019 at 3:13 pm
    Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.