መቐለ 70 አንደርታ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዋንጫ አሸናፊ ሆነ

Filed under: የዕለቱ ዜናዎች |

የእግር ኳስ ቡድኑ የዋንጫ ባለቤት የሆነው በዛሬው ዕለት በመቐለ በተደረገ ጫወታ ድሬዳዋ ከተማን ሁለት ለአንድ በሆነ ውጤት ካሸነፈ በኋላ ነው። ውድድሩን በአሸናፊነት የማጠናቀቅ ዕድል የነበረው ፋሲል ከነማ ከስሑል ሽረ ተጫውቶ አንድ አቻ ተለያይቷል። ውጥረት ሰፍኖበት የከረመው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውድድር ዛሬ ተጠናቋል።
ቪዲዮ፦ DW (ሚሊዮን ኃይለሥላሴ)

3 Responses to መቐለ 70 አንደርታ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዋንጫ አሸናፊ ሆነ

 1. Congratulations to Mekele-70 Enderta and its supporters! Celebrate it wisely in a sportive manner, no politics please!

  Kedir Setete
  July 7, 2019 at 4:29 pm
  Reply

 2. Tigrai’s soccer team named Mekele Seba Enderta had won Ethiopia’s premier league championship 2019 , because the volunteer slave’s Abiy’s regime is mass arresting other ethnicities.

  Ermias
  July 9, 2019 at 3:23 am
  Reply

 3. አይ ኳስ ድንቄም ትጫወተው! በጉቦና በአድሎ የተዋቀረ አሰራር። እንዲህ ነው ነገሩ። ላለህበት ቡድን ለመሰለፍ ጉቦ በሶስተኛ ሰው በኩል ለአሰልጣኝ መስጠት አለብህ። አፍ አውጥተውም ይጠይቁሃል። መጫወት ከፈለክ ለቡድኑ በእጅ መሄድ ተማር ትባላለህ በደላላ በኩል። ያለዚሃ ወንበር አሟቂ ነው የምትሆነው። በዳኞች በኩል ደግሞ ጣጣው ሌላ ነው። ጦር ሜዳ እንደተላከ ወታደር ለንስሃ አባታቸው ተናዘው ያለ የሌለ ንብረታቸውን ማን ማን እንደሚያገኝ ጽፈው አስቀምጠው ነው የሜዳ ዳኛ የሚሆኑት። ጥቃት ደርሶባቸዋል፤ እየደረሰባቸውም ነው ግን ስርዓት በሌለበት የዘር ፓለቲካ ነፎዝ ባደረጋት ምድር ፍትህ ስፍራ የላትምና ጥቃቱ ከተመልካች፤ ከክልል ፓሊስና ባለስልጣን በኩል ይሰነዘራል።
  እሺ እንደዚህ ከሆነ የመቀለ እንድርታ የዋንጫ አሸናፊ መሆነ የሚገርም ነገር አይደለም። ፋሲል ከነማ ወደ ትግራይ ሲያቀና የገጠመውን ልብ ብሎ ማየት አስፈላጊ ይመስለኛል። ትግራይን ሃገር ናት እያለ የሚለፈው ወያኔ ገና ከጅምሩ ደጋፊዎችንና ተጫዋቾችን በፍተሻ፤ ለሰዓታት ሲያንገላታ ዘጋቢ የአማራ ክልል ጋዜጠኞች ደግሞ ጭራሽ ኳስ ሜዳ እንዳይገቡ አገደ። ይህ በመንገድ በፍተሻና በጸጥታ ስጋት ምክንያት የፋሲል ከነማ ደጋፊንና ተጫዋቾችን ማዋከብ ሆን ተብሎ በስሌት የተደረገ ሴራ ነው። ጫዋታው ሲጀመርም የማሃል ዳኛው ለነፍሳቸው በመፍራት አድሎአዊ የፍጽም ቅጣት ምትም ሆነ እዚህ ግባ በማይባል ጥፋት ሁሉ ፊሽካቸውን በፋሲል ከነማ ላይ መንፋታቸው የልባቸውን ከሳምባ ጋር መገናዘብ ለማወቅ እንጂ ሌላ ጉዳይ አልነበረም። አለሁ ወይስ በድኔ ነው የሚሮጠው የሚለውን ለይቶ ለማወቅ ነው የፊሺካው ጋጋታ! ሰው ለህይወቱ እየፈራ ፍርድ መስጠት አይችልም። ሲጀመር በትግራይ (ወያኔ)መዝሙር የተጀመረው ጫወታ የኢት. ብሄራዊ መዝሙር እንዳይዘመር በመደረጉ እኔ ፋሲል ከነማን ብሆን ጭራሽ ጫዋታውን በመተው በገለልተኛ ሜዳ ላይ ለመጫወት እጠይቅ ነበር። ጫወታው ከተጀመረ በህዋላ ድላው፤ ስድቡ፤ ድንጋይ ውርወራው ሁሉ የተከናወነው ወያኔ ለወጣቶቹ በሰጠው መመሪያ መሰረት እንጂ በግብታዊነት የተደረገ እንቅስቃሴ አይደለም። አሁን አስቸኳይ የፓለቲካ ስብሰባ የጠራው ወያኔ ከሱዳን ጋር ለመቀላቀል ያሰበ ይመስላል። ጭራሹኑ ኢትዮጵያዊነትን ጠልቷል። ወይ የትግራይ ብሄራዊ መዝሙር… አቤት ውስልትና እስቲ ወደ አሻቹሁ ሂድና የፓለቲካ ሸፍጠኝነታችሁ ይራቀን። ዋንጫው የፋሲል ከነማ ነበር። ግን አፈሙዝና ገንዘብ ያለው ወያኔ ዛሬም ከሩቅ እና ከቅርብ ባዋቀራቸው የስለላ መረቡ ሰውን ያምሳል፤ ሃገርን ያፈርሳል፤ ትግራይን ገንጥሎም ሃገር ለመሆን የበረሃ ተስፋውን እንደገና አለምልሞታል። መጥኔ ለዘረኞች። እንዲህም ብሎ ኳስ ጫዋታ የለ። ጦርነትና ኳስ ጉቦና ስፓርት ግፍና መከራ እንደ ፈረደበት የሜዳ ቅሪላ የሚንከባለልባት ሃገር። ያበደ እንጂ ጤናማ ሰው እየጠፋ ሂዷል። የለበሰ ሁሉም ጤነኛ አይደለም፤ ራቁቱን የሚሄድ ሁሉም እብድ አይደለም። የተዘባረቀ ዓለም.. አለሚቱን ለማየት ጸሃይን ማጥፋት የሚሻ ትውልድ!

  Tesfa
  July 9, 2019 at 2:02 pm
  Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This site uses Akismet to reduce spam. Learn how your comment data is processed.